Emerging Technology chapter 5 Augmented Reality |virtual and Mixed Realyበአማርኛ

Описание к видео Emerging Technology chapter 5 Augmented Reality |virtual and Mixed Realyበአማርኛ

📑Course -Introduction to #Emerging Technology

📚Chapter Five

#Augmented_Reality (AR)

በዚህ ምዕራፍ ድንቅ የሆነውን🤩 AR - Augmented Reality ምን እንደሆነ እንዲሁም ተያያዥ ነገሮች ተንትነን እናያለን። ተከታተሉ🙌

በመጀመሪያ Augmented Reality ምንድነው❓

📸Augmented Reality is a general term for a collection of technologies used to blend computer generated information with the viewer's natural senses.
አጉሜንትድ ሪያሊቲ (AR) ማለት ይህን የሚታየውን አለም (Real World) እና ዲጂታል የሆነውን አለም አንድ ላይ በማቀናጀት የተሻለ እይታ (Experience) የሚሰጠን የቴክኖሎጂ አይነት ነው።
ለምሳሌ ብዙዎቻችሁ ለፎቶ📸 የምትጠቀሙትን እንደነ "Snapchat" ያሉትን አፖች ብትወስዱ ልክ በካሜራ ጊዜ የሚጨመሩትን Filter ኦች (ማሳመሪያዎች) ብንወስድ አንዱ የAR አሪፍ ምሳሌ ሊሆን ይችላል።

🙌ከዚሁ ጋር ተያይዞም "VR - Virtual Reality" ሲባል ሰምታችሁም ሊሆን ይችላል። ይህ (VR🤿) ከ AR- Augmented Reality ያለው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ወይም አርቲፊሻል አለም/Environment ውስጥ ነው የሚያስገባችሁ። Augmented Reality ግን አሁን ያለው Environment ላይ ሌላ ዲጂታል ነገር ይጨምርበታል።

📻Augmented Reality adds virtual content to a predominantly real environment, whereas Augmented Virtuality adds real content to a predominantly virtual Environment.

ልዩነቱን በደንብ አያችሁ አደል🫣 AR እና AV ~ የመጀመሪያው ከላይ ያየነው ነው። Augmented Virtuality ደግሞ ቨርቿል (የማይታየው - ዲጂታል) አለም ላይ Real የሆነ፣ የሚታይ ነገር መጨመር ማለት ነው። ለምሳሌ ሄድሴቱን ወይም ግላሱን🤿 (ይህ በኢሞጂ ላይ የሚታየውን አይነት) የእግር ኳስ ቪድዮ ጌም እየተጫወታችሁ ከሆነና በእውኑ አለም እግራችሁን ወደላይ ስታነሱ በቪድዮ ጌሙ ላይ ኳሱን የምትጠልዙት ከሆነ - ዲጂታል የነበረው ጌም ላይ ሪል የሆነውን እግራችሁን ወደ ላይ ስታነሱ በጌሙ ኳሱን ስለመታችሁት የ"Augmented Virtuality" አሪፍ ምሳሌ ሊሆን ይችላል። በሌላ መንገድ ደግሞ ቤታችሁ ሶፋ የሌለ ቢሆንና ሶፋ ሲገባበት ምን እንደሚመስል (ሶፋ ከመግዛታችሁ በፊት) ማየት ከፍለጋችሁ የAR headset🤿 አድርጋችሁ ወይም በAR አፖች ቤታችሁ ሶፋ ሲገባ ምን እንደሚመስል ማየት ትችላላችሁ። ይህ ደግሞ ዲጂታል በሪል አለም ላይ ስለተጨመረ "Augmented Reality" አሪፍ ምሳሌ ነው።😚

እስኪ ቀጥለን የሚከተሉትን የሶስቱን ልዩነት በስፋት እንመልከት🙌

#Virtual_Reality, Augmented Reality and Mixed Reality

1⃣Virtual Reality [VR]: is fully immersive, which tricks your senses into thinking you're in a different environment or world apart from the real world.
ይህ ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ አለም የሚወስደን (fully immersive) ቴክኖሎጂ ነው። ሌላ አለም ውስጥ እንደሆናችሁ የሚያሳስባችሁ ነው🤿።

Using Head-Mounted display🤿 (HMD) or headset, you'll experience a computer-generated world of imagery and sounds.
በፎቶ ከታች እንደምትመለከቱት ራስ ወይም አይን ላይ በሚደረግ ትንሽ ማሽን ወይም 🎧ሄድሴት ሌላ አለም ውስጥ እንደገባችሁ ይሰማችኋል።😁 ከኮምፒዩተር ጋር የተገናኘውን ሄድሴት ካደረጋችሁት በኃላ የምታዩትና የምትሰሙት ነገር በኮምፒውተር ላይ የተከፈተውን ነው። ለምሳሌ በስልካችሁ ወይም በኮምፒውተር የምትጫወቱትን የመኪና ጌም በVR የምትጫወቱት ቢሆን መኪናውን እራሳችሁ እየነዳችሁ ነው የሚመስላችሁ😴፥ ስትጋጩ ምናምን ያለው ድንጋጤ በእውኑ (real) አለም የተፈጠረ ነው የሚመስላችሁ።

🙌Virtual reality is also called computer-simulated reality.
ይህም ማለት ቅድም እንዳልነው እንደ ሄድሴት🤿 ያሉትን ከኮምፒውተር ጋር አገናኝተን እውን (real የሆነ Environment - realistic sounds, images) ወይም ምናባዊ አለም (Imaginary world) የምንፈጥርበት ነው።

📸HTC Vive, Oculus rift (Manufactured by Facebook Company), Google Cardboard and Gear VR (manufactures by Samsung) are some of the VR devices that transport users into imaginary world.
ከላይ የተጠቀሱትን አራቱን መሳሪያዎች ከታች በፎቶ (photo2) ተመልከቷቸው። ለVR የምንጠቀማቸውን ማሽኖች በጠቅላላ በሶስት እንከፍላለን።

1. Tethered headsets: በገመድ (Cable) ከኮምፒውተር ጋር የሚገናኝ ነው። ስለዚህ የVR Experience ወይም Imaginary World ከPCው ወደኛ የሚተላለፈው በገመዱ በኩል ነው።
ለምሳሌ HTC VIVE, Ocular rift

2. Stand-alone Headsets
እነዚህ ደግሞ በራሳቸው (ያለ ኬብል) ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ሄድሴት🤿 ናቸው። እነዚህ ጥሩ ናቸው። ወጪ ቆጣቢ ናቸው በተጨማሪም ደግሞ ምቾት (freedom of movement) ይሰጣሉ አንዴ Glassኡን 🤿 አይናችሁ ላይ ካረጋችሁት እንደ "Tethered" ኬብሉ ከPcው ላይ ተነቀል አልተነቀል ምንም አያሳስባችሁም።
ለምሳሌ Samsung gear, Oculus Quest 2.

3. Smartphone headsets
ይህ ደግሞ እጆቻችን ላይ የሚገኙትን ስማርት ስልኮች ከሄድሴቱ ጋር አገናኝተን VR Experience የምንፈጥርበት ነው። እነዚህ ከስልክ ጋር ሊገናኙ የሚችሉ😮 የVR Glass/Headset🤿 ናቸው።
ለምሳሌ Google cardboard, Ocular rift.

ቀጣዩን ደግሞ ኮሜንት ላይ ተመልከቱ አንብቡ በዛውም ሀሳባችን አስቀምጡ
TAg
augmented realityemerging technologyvirtual realityEmerging technology chapter 5

Комментарии

Информация по комментариям в разработке