Aman Kiyamo - Telemenen Music Video

Описание к видео Aman Kiyamo - Telemenen Music Video

New Ethiopian Reggae Music Video
Aman Kiyamo -Telemenen
MV Produced by - Kafu Production
Zyla Records - Ras Alula

Lyrics - Telemenen
ፍቅር በሰው ዘር ላይ
ሠላም በአለም ላይ
ይስፈን ወርዶ ከላይ
መቼም እንዳንለያይ
ፍቅር በሰው ዘር ላይ
ሠላም በአለም ላይ
ይስፈን ወርዶ ከላይ
መቼም እንዳንለያይ
ትበቃችኋለች መሬት ተስማምታችሁ ኑሩ
በኔ ፍቃድ ነው አትጨነቁ ነፃ ነው አየሩ
ብሎ ሳይሰስት የሰጠን እያለ ባለቤቱ
ምን ይሉት ፈሊጥ ነው የሰው ልጅ ተባልቶ መሞቱ
ቀይ ጥቁር ብንሆን ወይም ከነጮቹ
ካንድ ግንድ አይደል ወይ የዛፍ ቅጠሎቹ
ምንም ብንበዛ ከአፈር በላይ ሆነን
ከብደናት አናውቅም ለመሬት አንድ ቀን
ምን ተገኘ ከጦርነት ከብጥብጥ ዋይታ
አይበልጥም ወይ መካፈሉ የፍቅርን ጠብታ
እስከመቼ ለማይረባው አስተሳሰብ ታጥረን
የምንኖር ለዘመናት ፍቅርን ተርበን
መች ይሆን በአለም ላይ ፍቅራችን በርትቶ
ወርቅ አልማዙ ጌጡ ለሠው ልጅ ተረትቶ
ሆኖ ሰውነቱ ለክብሩ መለኪያ
ወዝወዝ የምንለው ያለመታወቂያ
ወዝወዝ ነው ወዝወዝ ነው
ወደግራ ወደቀኝ ነው
ሰሜን ደቡብ አቅጣጫ ነው
መታወቂያ ሠው መሆኔ ነው
ወዝወዝ ነው ወዝወዝ ነው
ወደግራ ወደቀኝ ነው
ምስራቅ ምዕራብ አቅጣጫ ነው
መታወቂያ ሰው መሆኔ ነው
ፍቅር በሰው ዘር ላይ
ሠላም በአለም ላይ
ይስፈን ወርዶ ከላይ
መቼም እንዳንለያይ
ፍቅር በሰው ዘር ላይ
ሠላም በአለም ላይ
ይስፈን ወርዶ ከላይ
መቼም እንዳንለያይ
ኧረ ተው ተው ተው ባክህ ተው
ኧረ ተው ተው ተለመነን ተው
ለሁላችንም አንድ አባት የሆንከው
ፍቅርን ሀ ሁ ብለህ ለእኛ ያስተማርከው
አበጃጅተህ ምድርን ሰተህ ጣልቃ ሳትገባ
ሳታደላ የፈጠርከን አርገህ ውብ አበባ
ስማን ታረቀን ማረን አባባ
ለእኛ ስሜት የላቸው ሆድ የሚባባ
ሦስተኛው አለም እያሉ አሳዩን እምባ
ገቡብን አጥንተው በስስ ጎናችን
አገኙት ቁልፉንም ለድክመታችን
ፈጁን አፋጁን ልብ እስካይራራ
አረጉን አይጣቸው የቤተ ሙከራ
ካጠፋን ልብህ ይራራ
አውጣን ከዚህ መከራ
በንፁኋ መሬት ሆኖ ሰው ሳለ እንግዳ
ሆኑ እነሱ ባለቤት አረጉን ባዳ
ካሮቱን ስሰጥህ ዳቦ ነው ብላ
አሻፈረኝ ካልከኝ አድርጌው ዱላ
ጠርጌ ጠርጌ እየተባልን
መኖሩ መሮናል እኛ አፍሪካውያን
በል ሳበው ሳበው ችግራችንን
ተብትቦ የያዛት አለማችንን
ሰርዘው መጥፎውን ከታሪካችን
አቁመን ዘብ አርገህ ለእናት ምድራችን
አውጣን ከብሄር ከዘር ቆጠራ
መድበን እኛንም ከደጉ ጎራ!!
አሆሆ በል ተለመነን
አሄሄ ተው ተለመነን
አሆሆይ ተው ተለመነን
በል ተለመነን ተው ተለመነን

Комментарии

Информация по комментариям в разработке