የሃዲያ ሰበከ የወጣቶች ኮንፍራንስ በጊምቢቹ

Описание к видео የሃዲያ ሰበከ የወጣቶች ኮንፍራንስ በጊምቢቹ

በፍቅር አይኖች ተመልከትና
ከሸለቆዬ ፈጥነህ አውጣኝና
በደሌን ምረህ ወደልቤ ና
ባክህ አምላኬ ህይወቴን አቅና
ጆሮህን ስጠኝ እነግርሃለሁ
አልደብቅህም አዋይሃለሁ
አታልፍምና የልቤን አይተህ
ደግመህ አስበኝ እድልን ሰጥተህ
ናልኝ ና ኢየሱስ ናልኝ ና
ናልኝ ና ውዴ ናልኝ ና
ድካሜን በሃይልህ ሽረህ
በመንፈስህ ተቆጣጥረህ
የእኔ የምለው ላይኖረኝ
የግልህ ገንዘብህ አድርገኝ
ተጭኖኝ ክብድ ያለኝን
ሌተቀን ሚታገለኝን
ከአንተ ይልቅ የለም የሚረዳኝ
በሃይልህ ባክህ ደግፈኝ
ናልኝ ና.....
ውሰደው/2× ድካሜን ውሰደው
ይምጣልኝ/2× ሞገስህ ያግኘኝ

1- ለአዲስ ኪዳን በሚሆነው በመታጠብ አዳንከኝ
በቅዱሱ እስትንፋስህ በመንፈስህ አደስከኝ
በስራዬና በፅድቄ አይደለም የሆነልኝ
እርዳታዬ ከአርያም ከአንተ ነው የመጣልኝ
ፅድቅ የለኝም ምታመነው ባንተ ነው እኔ የምመካው
ብቻዬን አትልቀቀኝ አምላኬ በቃ ያዘኝ
ከመጣ ክብርህ በላዬ ይቀየራል ማንነቴ
ከምንም ጊዜውም የሚበልጥ ግሩም ሃይል ዛሬ ይለቀቅ
ግሩም ሃይል ዛሬ ይለቀቅ/2×

2- ለኃጢአት ስጋዬ ሞቶ ለፅድቅህ ንቁ አድርገኝ
ከእኔ አትለይ አትሽሽ ቅረበኝ አትራቀኝ
በመንፈስህ ቀምመህ መዓዛዬ ይቀየር
አምላኬ አንተን የማይፈራ አይኑረኝ አንድም ነገር
ውሰደው......
ምረኸኝ አቅርበኝ ፊትህን አትሰውር
ናልኝ ፈልግሃለሁ ምራኝ እከተልሃለሁ
ህይወቴን ሰጥቼሃለሁ ልጄ በለኝ እሰማለሁ
ከእንግዲህ የራስህ ልሆን ለራሴ ቃል ገብቻለሁ
የእኔ እውቀት የእኔ ውጥን አይጠቅመኝም አውቀዋለሁ
አባ ናልኝና ምራኝ በቃ የአንተን እሰማለሁ
ያክብርህ ለእኔም ይታየኝ
ግርዶሹም ከአይኔ ይነሳልኝ
ያየህልኝን ከፍታ አድርሰኝ እባክህ ጌታ
ና ና ህይወቴን ልትቀድስ ና
ና ና ህይወቴን ልትሰራው ና
ና ና ፈልጌ መጥቻለሁ(ክብርህን ናፍቄአለሁ) ና ና

Комментарии

Информация по комментариям в разработке