የሥንብት አደራ |አዲስ የኅብረት ነሺዳ | የከውኑ ሞገስ 5 ምርኩዝ 26| BEST ETHIOPIA NEW NESHID | Minber Records ሚንበር ሪከርድስ

Описание к видео የሥንብት አደራ |አዲስ የኅብረት ነሺዳ | የከውኑ ሞገስ 5 ምርኩዝ 26| BEST ETHIOPIA NEW NESHID | Minber Records ሚንበር ሪከርድስ

የሥንብት አደራ
"ሰዎች ሆይ፣ ንግግሬን ስሙ። ምን አልባትም ከዚህ ዓመት በኋላ በዚህ ቦታ ላይ ዳግም ላላገኛችሁ እችላለሁ።
አዋጅ .... ከኔ በኋላ ነብይ የለም። ከናንተ በኋላም ዑምማ የለም!! ሰዎች ሆይ ...."


ጀንበር ላትፈግግ ሊያይል ሃዘኑ ሌቱ ላይነጋ፣
ሰው አራዊቱን ሃዘን ሊወርሰው ልቡ ላይረጋ፣
ባልመጣ ብለን የተመኘነው ደረሰ ወቅቱ፣
የዓለሙ ብርሃን የከውኑ ሞገስ ሊሰናበቱ፣
የዓለሙ ብርሃን የከውኑ ሞገስ ሊሰናበቱ።

ያ ሃቢበላህ
ያ ኸይረል ወራ
እኛም ደርሶናል
ያንቱ አደራ

ያ ረሱለላህ
ያ ኸይረል ወራ
ደርሷል አማናው
ለኛም በተራ

ዘመናት አልፎ ተሻግሮ
ሃዘኑ እንዳዲስ ዛሬም ያባባል፣
ከርስዎ መለየት ወረት የለውም
እስከ ዓለም ማብቂያ ያስነባል።
መለየት ዋዜማው ደርሶ
አደራው ሲናኝ በዛች ቀን፣
ዓለምን ሃዘን ሸፈናት
ልብ ሁሉ ሞላው ሰቀቀን።

ሶሃባው በአምባው ታድሞ
መልዕክቶን እያደመጠ፣
ማን ችሎ ይቁም በፅናት
በሃዘን እየተናጠ፣
መሸቃው ቢያይል ቢከፋ
መሸከም ለሰው አይከብድም፣
የስንብትዎ ህመሙ
ዳኢም ነው መቸም አይጠግም።

አማናው ለዓለም ሊዳረስ
ልሳንዎ ቃሉን ሲያፈልቀው፣
ተሰማኝ የነበርኩ ያህል
አህዋሉን ሁሉ የማውቀው።
ያደራ ቃልዎን አትሜ
ባኖርም ከልቤ ላይ፣
ስንብትዎ ግን አሳሳኝ
እንዴት ነው ችዬ የማይ።

ሰላሚ ዓላ
ማረፊያ ላይኔ
ለከውኑ ሞገስ
ለጦይባው ዘይኔ

ሰለላህ ዓለይክ
ያ ኸይረል ወራ
ምስክሮች ነን
ላንቱ አደራ

ሰላሚ ዓላ
ማረፊያ ላይኔ
ለከውኑ ሞገስ
ለጦይባው ዘይኔ

ሰለላህ ዓለይክ
ያ ኸይረል ወራ
ምስክሮች ነን
ላንቱ አደራ

የቆምኩ ያህል ይሰማኛል ከሶሃቦቹ ጎራ፣
የስንብት ቃልዎ ሲናኝ አማናዎ ሲዘራ፣
ምን ባጎድል አደራዎን ባይሳካልኝም፣
አልሰማሁም የምልበት አንደበት ግን የለኝም።

ከተሰጡት ምን ቀርቶብኝ ካንቱ ምን አጥቼ፣
በጨለማ የምባክን ብርሃንዎን ትቼ፣
የስንብት ህያው ቃልዎ ደርሷል ከኔም ደጅ፣
ምስክር ነኝ ባደባባይ ነቢ የኔ ወዳጅ።

ያ ሃቢበላህ
ያ ኸይረል ወራ
እኛም ደርሶናል
ያንቱ አደራ

ያ ረሱለላህ
ያ ኸይረል ወራ
ደርሷል አማናው
ለኛም በተራ
****

አዝማች (2)

ጀንበር ላትፈግግ ሊያይል ሃዘኑ ሌቱ ላይነጋ፣
ሰው አራዊቱን ሃዘን ሊወርሰው ልቡ ላይረጋ፣
ባልመጣ ብለን የተመኘነው ደረሰ ወቅቱ፣
የዓለሙ ብርሃን የከውኑ ሞገስ ሊሰናበቱ፣
የዓለሙ ብርሃን የከውኑ ሞገስ ሊሰናበቱ።

ያ ሃቢበላህ
ያ ኸይረል ወራ
እኛም ደርሶናል
ያንቱ አደራ

ያ ረሱለላህ
ያ ኸይረል ወራ
ደርሷል አማናው
ለኛም በተራ

ሲሳነው ቃል መዝራት ልሳን
ሲለጎም ደፍሮ ልክ እንደባዳ፣
ሲጨልም ቀን ሲዘነበል
ያመኑት እግር ደርሶ ሲከዳ፣
ምን ነበር ይህን ቀን ሳላይ
በሄድኩኝ እኔው ቀድሜ፣
ምን አሻኝ ከንግዲህማ
ብርሃኔ ርቆኝ ዓለሜ።

ስንቱ ጉድ ተፈራረቀ
የስቃይ ጨለማ ነግሶ፣
የሰው ልጅ ሁሉን ያልፈዋል
በልቡ ኣቅም ታግሶ፣
ቢያቅትም ቢያምም አበሳው
ዱንያ ብታታግልም፣
የምድር የቱም ፈተና
ስንብትዎን አያህልም።

የዘመን ቁስል ህመሟን
አሽረው ያቃኗት ዓለም፣
ተጠጋ ፅልመት ሊወርሳት
ላትፈካ ዳግም ልትጨልም፣
መምጣትዎ ነፃ ቢያወጣት
ካሰራት ደዌ ፈውሶ፣
ተረታች በስንብትዎ
ፀናባት ህመም መልሶ።

ሰላሚ ዓላ
ማረፊያ ላይኔ
ለከውኑ ሞገስ
ለጦይባው ዘይኔ

ሰለላህ ዓለይክ
ያ ኸይረል ወራ
ምስክሮች ነን
ላንቱ አደራ

ሰላሚ ዓላ
ማረፊያ ላይኔ
ለከውኑ ሞገስ
ለጦይባው ዘይኔ

ሰለላህ ዓለይክ
ያ ኸይረል ወራ
ምስክሮች ነን
ላንቱ አደራ

ዓለምን ሃይባ አሳጥቶ
ፋሩቅን ሰይፍ ያስመዘዘ፣
ቢላልን ልቡን ሸርሽሮ
ወደ ሻም ጠቅሎ ያስጓዘ፣
ለትውልድ ሃዘን አውርሶ
ዘመናት ቢፈራረቅም፣
አይሽርም ያንቱ ስንብት
ያሁን ነው እርጅና አያውቅም።

ዓይን አልሻም ከእንግዲማ
ይሰወር ብርሃን ይራቀኝ፣
አንቱን ላያይ ቢንከባለል
ፅልመት ነው በግራም በቀኝ፣
ይህን ብሎ የታወረው
ወዳጅዎ ዓይኑን አፍርጦ፣
ይናፍቃል ዳግም ሊያይዎ
በጀነት ጎንዎ ተቀምጦ።

ያ ሃቢበላህ
ያ ኸይረል ወራ
እኛም ደርሶናል
ያንቱ አደራ

ያ ረሱለላህ
ያ ኸይረል ወራ
ደርሷል አማናው
ለኛም በተራ

ዓለም አንክሳ አቀረቀረች
ዜናው ሠበራት የስንብቱ፣
ምድር ጨለመች ተስፋዋ ተኖ
እያሸበራት መለየት ካንቱ፣
ድንግዝግዝ ሆነ አስፈራ ቀኑ
እንዴት ሊለመድ ያላንቱ መዋል፣
ማን ችሎ ይናገር ይህንን ኸበር 
ነፍስ እንዴት ችሎ ይቀበለዋል።
የማይሽር ህመም ሃዘን ሚያድለን ደረሰ ቀኑ፣
የከውኑ ሞገስ ወደ አላህ ራህመት መርጠው ሲያቀኑ።

"ሰዎች ሆይ ይህ ቀናችሁ፤ በዚህ ወራችሁ እና በዚህ ሃገራችሁ ላይ የተከበረ እና እርም እንደሆነ ሁሉ ደማችሁምና ገንዘባችሁም በናንተ ላይ እርም ነው።  አዋጅ ... የአላህን መጽሐፍና የኔን ሱና ትቼላችኋለሁ። በርሱ ከተመራችሁ መንገድ አትሰቱም። ሰዎች ሆይ ....!


ግጥም
ሙሐመድ ፈረጅ
ሙሐመድ ኢድሪስ ካሣ

ዜማ
በኅብረት

ሙንሺዶች

ነስሩ ኸድር
አስማማው አህመድ
ተውፊቅ ዩሱፍ
ዓሊ አሚን
ፉዓድ በሽር

ድምፅ ቀረፃና ቅንበር
ሙሐመድ ራጅኡ

ፕሮዲዩሰር
ሚንበር ሪከርድስ

ምስጋና
ኑር አዲስ ዲዛይን
አብሬት ኤል ኢዲ ና አልሙኒየም ዲስፕሌይ
ሂራ በጎ አድራጎት
ኤም ኤስ ሊግ
ኑጁም ዩዝ ኤክሰለንሲ እና
ኡሚ በጎ አድራጎት
ፏ ዲኮርና
ፋንሲ ሬዝን አርት
ኢህሳን የሴኪውሪቲ እና የአጀባ አገልግሎት

Timecodes
0:00 - የረሱል (ሰዐወ) አዋጅ
0:28 - የኀብረት ነሺዳ
09:00 - የረሱል (ሰዐወ) አዋጅ መዝጊያ
09:30 - የኀብረት ነሺዳ መዝጊያ አዝማች

MinberTube #neshida #MinberTV #አዲስ_ነሺዳ #neshida  #New_Neshida  #BEST #ሚንበር_ሪከርድስ #MinberRecords#ሚንበር_ቲቪ #minber_tv #ሪከርድስ
ከዚህ በፊት የተሰሩትን ለማየት
   • የትውልድ አደራዎች  | Collection | New Best ...  

ሚንበር ሪከርድስ አዲስ አበባ ዉስጥ የተመሰረተ እና ሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ወደ ህዝብ ከሚያደርሳቸው ሥራዎቹ አንዱ ሲሆን የተለያዩ ኢስላማዊ እሴትን የሚጨምሩ ጥበ ውጤቶችን ከነዚህም መንዙማ፤እንጉርጉሮ እና ነሺዳን የመሳሰሉትን በዋናነት በመስራት ለተመልካች ያቀርባል፡፡

© መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው ፡፡
ሚንበር ሪከርድስ መስከረም 2016 | 1445 ሂ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке