🛑 ናታኔም ነኝ በዘማሪ የአብቃል ደሳለኝ (Natanem negn By Zemari Yeabkal Desalegn)

Описание к видео 🛑 ናታኔም ነኝ በዘማሪ የአብቃል ደሳለኝ (Natanem negn By Zemari Yeabkal Desalegn)

#የመዝሙር ግጥም

የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው
ብዘምርለትም ያንስበታል ይኽው
ከውድቀቴ አንስተህ ድካሜን ያገዝኸኝ
ሰባራውን ድልድይ ገጥመህ ያሻገርከኝ

ሰካራም ዘማዊ ወንበዴ ነበርኩኝ
ያመፀኞች መሪ ደምን ያፈሰስኩኝ
ዛሬ ግን ታሪኬን ጌታ ቀይሮታል
ለኃያሉ ጌታ ምስጋና ይገባል

ጌታ እኮ ነው ይህን ያደረገ
አምላኬ ነው ለኔ የታመነው
በዘመኔ ሁሉ ድንቅን የፈፀመው
ጌታ እኮ ነው ይህን ያደረገ

ሳይከብድብኝ የዓለም ዝና
ተንበርክኬ ልስጥህ ምስጋና
ምክንያት አለኝ ለማዘንበሌ
ናታኔም ነኝ ይህቺ ናት ቃሌ
ደጅ ሆኜ ካንተ በር
ተስፋ አድርጌ ስዘምር
ቆጥረህልኝ እንደ ዋጋ
አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
ናታኔም ነኝ በአገልግሎቴ
አይከፋኝም ታናሽነቴ
እጠርጋለሁ ደጅህን ጌታ
ዝቅ ብዬ ላንተ ውለታ

ህይወት ሰላምን ትቼ
የማይታይ አይቼ
ላንተ ብሰጥ ጀርባዬን
ልተዋወቅ ጠላቴን
የከበበኝ ውጊያ ነው
የተረፈኝ ፀፀት ነው
የሻርክልኝ ቁስለቴን
ተሰቅለህ ነው አባቴ
በዋጋ ገዝተኸኛል እና
ስለእኔ ደም ከፍለሀል እና
በዋጋ ገዝተኸኛል እና
ስለእኔ ደም ከፍለሀል እና
ልሳኔ ያውጃል ክብርህን
አልረሳም ጌታ ውለታህን
ልሳኔ ያውጃል ክብርህን
አልረሳም ጌታ ውለታህን

ቅዱሱን መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ
ምን ይዤ ልምጣና ከአምላኬ ፊት ልስገድ
ወደላይ በሰማይ ወደታች በጥልቀት
አምላኬ የት አለ የምትገኝበት
አምላኬ የት አለ የምትገኝበት

በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
ዓለምና መላው ያንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ ያንተው አይደለም ወይ
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
ዓለምና መላው ያንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ ያንተው አይደለም ወይ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке