የድሬዳዋ “ሳልቫጅ ተራ” በቃጠሎ ወደመ | Dire Dawa | market | fire | Ethiopia Insider

Описание к видео የድሬዳዋ “ሳልቫጅ ተራ” በቃጠሎ ወደመ | Dire Dawa | market | fire | Ethiopia Insider

በድሬዳዋ ከተማ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 25፤ 2016 የተነሳው የእሳት ቃጠሎ፤ በተለምዶ “ሳልቫጅ ተራ” ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ “ሙሉ በሙሉ” እንዳወደመ የከተማው ከንቲባ ከድር ጁሀር ተናገሩ። ለአምስት ሰዓታት የዘለቀው ቃጠሎ “ሩዝ ተራ” እና “ማሽላ ተራ” የተባሉ አካባቢዎችን እንዳወደመ ከንቲባው ለከተማው የቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጸዋል።

በተለምዶ አሸዋ ተብሎ በሚጠራው ዋነኛ የንግድ አካባቢ “ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ” የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎ፤ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ እኩለ ቀን ስድስት ሰዓት ድረስ መቆየቱን የድሬዳዋ ከተማ የመንግስት ኮምዩንኬሽን ቢሮ አስታውቋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች፤ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ እሳቱ ሙሉ ለሙሉ አለመክሰሙን ገልጸዋል።

የእሳት አደጋ ማጥፊያ ምሽቱን ጭምር ወደ ስፍራው ሲመላለሱ እና ውሃ ሲረጩ እንደነበር ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። የከተማይቱ ፖሊስ ነዋሪዎች አደጋው ወደ ደረሰበት ስፍራ እንዳይጠጉ ጥበቃ ሲያደርግ መመልከታቸውንም የዓይን እማኞቹ አክለዋል።

በዛሬው የእሳት ቃጠሎ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ለመኖሩ በድሬዳዋ ከተማ ከንቲባም ሆነ በአስተዳደሩ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ሆኖም ቃጠሎው “ሳልቫጅ ተራ” እና “ማሽላ ተራ” የተባሉት አካባቢዎች “ሙሉ በሙሉ” ማውደሙን ከንቲባ ከድር ለድሬ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ቃጠሎው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ይስፋፋል በሚል ስጋት በአቅራቢያው የነበሩ ነዋሪዎች ንብረቶቻቸውን ሲያሸሹ ተስተውለዋል።

ቃጠሎው በደረሰበት አቅራቢያ ያሉ ስፍራዎች “በከፊል” መትረፋቸውን ከንቲባ ከድር አመልክተዋል። የእሳት ቃጠሎውን ለመቆጣጠር የድሬዳዋ እና የሐረር ከተሞች የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና ሌሎችም አካላት ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ከንቲባው ጨምረው ገልጸዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
-----------------------------------------------------------------------------------------
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ http://ethiopiainsider.com​
ፌስቡክ ፦   / ethiopiainsider  
ትዊተር (ኤክስ) ፦   / ethiopiainsider  
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaInsiderNews
ቲክቶክ፦   / ethiopiainsider  

Комментарии

Информация по комментариям в разработке