የ8 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የአዲስ አበባ የጎርፍ አደጋ | Flood in Addis Ababa cost 8 lives

Описание к видео የ8 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የአዲስ አበባ የጎርፍ አደጋ | Flood in Addis Ababa cost 8 lives

በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው ዕለት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከፍተኛውን ጉዳት ያስተናገደው፤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከተማ ጀርመን አደባባይ አካባቢ የሚገኘው የመካነየሱስ ሴሚናሪ ነው። በጎርፍ አደጋው የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል።

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች እና የሴሚናሪው ሰራተኞች ትላንት ምሽቱን ጭምር ባደረጉት አሰሳ የሰባቱን አስክሬን ማግኘት ችለዋል። በዛሬው ዕለት እኩለ ቀን ገደማ ደግሞ የአንድ ሟች አስክሬን በፍለጋ ተገኝቷል።

በመካነየሱስ ሴሚናሪ ላለፉት 20 ዓመታት በሁለገብ ሰራተኝነት ያገለገሉት አቶ አለሙ ክብሩ፤ በክረምት ወንዝ ሞልቶ ጎርፍ መከሰቱ ያለ ቢሆንም እንዲህ አይነት የከፋ አደጋ ግን አይተው እንደማያውቁ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ትላንት ወደ አስር ሰዓት ተኩል ገደማ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ፤ በሴሚናሪው ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ አምስት የሰራተኞች መኖሪያ ህንጻ ላይ ከፍተኛ የሚባል ጉዳትን አስከትሏል።

የትላንቱ አደጋ ያደረሰውን ጉዳት በቦታው ተገኝቶ የተመለከተው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ፤ የሴሚናሪው ሰራተኞችን እና የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሰለሞን ፍስሃን አነጋግሯል። የዘጋቢውን ጥንቅር ከቪዲዮው ይመልከቱ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ http://ethiopiainsider.com​
ፌስቡክ ፦   / ethiopiainsider  
ትዊተር ፦   / ethiopiainsider  

Комментарии

Информация по комментариям в разработке