"ጋዜጠኝነትስ እንደጳውሎስ"የተባለለት የጳውሎስ ኞኞ የሕይወት ታሪክና ስራዎቹ

Описание к видео "ጋዜጠኝነትስ እንደጳውሎስ"የተባለለት የጳውሎስ ኞኞ የሕይወት ታሪክና ስራዎቹ

ጳውሎስ ኞኞ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከሴቶች አምድና ከልጆች ገፅ ባለፈ በምክትል ዋና አዘጋጅነትና የተወሰኑ አምዶችን በዋና አዘጋጅነት ሰርቷል፡፡ "ለሳቅ ለጨዋታ" እንዲሁም
‹‹አንድ ጥያቄ አለኝ›› የሚሉ አምዶች እንደነበሩት የሕይወትጨታሪኩ የተከተበበት መጽሐፍ ያስረዳል። ይሁን እንጂ በብዙ ሰዎች ዘንድ የተወደደለትና የታወቀበት አንድ ጥያቄ አለኝ የሚለው አምዱ ነበር። በዚህ አምድ ጳውሎስ ከተለያዩ አንባቢዎች በደብዳቤ የሚላኩለትን ጥያቄዎች ይመልስበት ነበር፡፡ የሚሰጣቸው መልሶችም አንዳዶች ትክክለኛ አንዳንዶቹ ደግሞ ቀልድና ለዛን የተላበሱ ሀሳቦችን ይገልጽባቸው ነበር።በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያ ታሪክ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ፀሃፌ ተውኔት፣ ሰዓሊ፣ የታሪክ ፀሐፊው የጳውሎስ ኞኞ ስም ሲነሳ ወደ አብዛሃኛው ሰው ዓዕምሮ የሚመጣው በቀለም ትምህርት ብዙም ሳይገፋ በድፍን ኢትዮጵያ ዝነኛና ተወዳጅ ለመሆን ያበቃው የጋዜጠኝነት ስራው ነው፡፡ በዘመናዊ ትምህርት አራተኛ ክፍልን ያልተሻገረው ጳውሎስ፣ በተፈጥሮ የታደለው የማንበብ፣ የመጠየቅና የመመራመር ተሰጥኦ በጋዜጠኝነት ሙያው አንቱታን አትርፎለታል፡፡
በኢትዮጵያ ድምፅ ጋዜጣ፣ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲሁም በኢትዮጵያ ራዲዮ ሲሰራ ‹‹ጋዜጠኝነትስ እንደጳውሎስ!›› ተብሎለታል ፣ በርካታ መፅሐፍትንና ትያትሮችንም ለአንባቢያን አበርክቷል፡፡
👉▰▰▰▰▰▰▰▰
ጳውሎስ ኞኞ ከጻፋቸው መጽሐፍቶች መካከል ‹‹የሴቶች አምባ››፣ ‹‹አጤ ምኒልክ››፣ ‹‹አጤ ቴዎድሮስ››፣ ‹‹አስደናቂ ታሪኮች››፣ ‹‹የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት››፣ ‹‹አጤ ምኒልክ ከውጭ ሀገራት ጋር የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች››፣ ‹‹አጤ ምኒልክ ከሀገር ውስጥ የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች››፣ ‹‹አራዳው ታደሰ››፣ ‹‹የኔዎቹ ገረዶች››፣ የጌታቸው ሚስቶች››፣ ‹‹ቅይጥ››፣ ‹‹ምስቅልቅል››፣ ‹‹እንቆቅልሽ››፣ ‹‹ድብልቅልቅ››፣ ‹‹እውቀት››፣ … ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ለሕትመት ከበቁት ስራዎቹ በተጨማሪ፣ ያልታተሙት ስራዎቹም በርካታ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ‹‹የአጤ ዮሐንስ ታሪክ››፣ ‹‹የአዲስ አበባ ታሪክ››፣ ‹‹የኢትዮጵያ ኢንሳይክሎፒዲያ››፣ ‹‹ሰዎቹ››፣ ‹‹የልጅ ኢያሱ ታሪክ›› እና ‹‹አዜብ›› የተሰኙ የጽሑፍ ስራዎቹም ይጠቀሳሉ፡፡

Комментарии

Информация по комментариям в разработке