ETHIOPIA | የስኳር ህመምተⶉች ምን እንዲመገቡ ይመከራል?

Описание к видео ETHIOPIA | የስኳር ህመምተⶉች ምን እንዲመገቡ ይመከራል?

ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች በስኳር ህመም በከፍተኛ ተጠቂ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በሀገሪቱ እስከ 3 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ከህመሙ ጋር ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል።

በመላው ዓለም ከ600 ሚሊየን በላይ ህዝብ የስኳር ህመምተኛ መሆኑም መረጃዎች ያመለክታሉ።

🍎 የስኳር ህመም ምንድን ነው… ?

የስኳር ህመም የሚከሰተው ሰውነታችን ለኑሮም ሆነ ለእድገት የሚያስፈልገውን ስኳር በትክክል ለመጠቀም ሳይችል ሲቀር ነው፡፡

አንድ ሰው የስኳር ህመም አለው የምንለው በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ ነው፤ በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ከመጠን በላይ ከፍ ብሎ የሚገኘው ደግሞ ቆሽት የተባለው የሰውነት ክፍል ኢንሱሊን የተሰኘው ሆርሞን በበቂ ሁኔታ ወይም ደግሞ ጭራሹኑ ማመንጨት ሲያቅተው ነው፡፡

የስኳር ህመም በሽንት ይበልጥ ደግሞ በደም ምርመራ ሊታወቅ ይችላል፤ የስኳር ህመም አንዴ ከያዘ በባህላዊ ሆነ በሳይንሳዊ የህክምና ዘዴ የማይድን የዕድሜ ልክ ህመም ቢሆንም ክትትልና ቁጥጥር ከተደረገበት ግን እንደማንኛውም ሰው ጤናማ ኑሮ ሊያስኖር የሚችል ነው፡፡

በተቃራኒው ደግሞ በተገቢው መንገድ ክትትልና ቁጥጥር ካልተደረገበት የተለያዩ ጠንቆችን ያስከትላል፡፡

🍎 የስኳር ህመም ማንን ይይዛል… ?

የስኳር ህመም እድሜ፣ ጾታና የኑሮ ደረጃ ሳይል በሁሉም ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል ህመም ነው።

የስኳር ህመም በማንኛውም ሰው ላይ ሊከስት የሚችል ቢሆንም፤ እድሜያቸው ከ4ዐ ዓመት በላይ የሆኑ፣ የሰውነት ክብደታቸው ከፍተኛ የሆኑ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማያደርጉ ለህመሙ ታጋላጭ ናቸው።

እንዲሁም በቤተሰባቸው ውስጥ የስኳር ህመም ያለባቸው፣ የደም ግፊት ያለባቸው፣ በደም ውስጥ የቅባት መጠኑ /ኮሌስትሮል/ ከፍ ያለባቸው ሰዎች፣ ከዚህ ቀደም በእርግዝና ጊዜ የስኳር ህመም የታየባቸውና ከዚህ ቀደም ክብደታቸው ከአራት ኪሎ ግራም በላይ የሆኑ ህጻናትን የወለዱ ሴቶች ይበልጥ ለስኳር ህመም የተጋለጡ ናቸው፡፡

ከእነዚህ ሁኔታዎች መካከል አንዱ እንኳን የታዩባቸው ሰዎች ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የስኳሩን ሁኔታ ለማየት የደም ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

🍎 የስኳር ህመም ምልክቶች… ?

በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ሲጨምር ግልጽና የማያሻሙ ምልክቶች ያሉት ሲሆን፥

እነዚህም፦ ከፍተኛ የውኃ ጥም፣ ቶሎ ቶሎና ብዙ መሽናት፣ ከፍተኛ የረሀብ ስሜት፣ ድካም፣ ኃይል ማጣት፣ ምክንያቱ ያልታወቀ የክብደት መቀነስ ናቸው፡፡

ሌሎች ምልክቶች ደግሞ የማየት ችሎታ ላይ ብዥታ መፈጠር፣ የእግርና የእጅ መደንዘዝ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አለመቻል ሰውነት ሲቆረጥ፣ ሲቆስል፣ ሲያብጥና ሲያሳክክ ቶሎ ያለመዳን፣ በሴቶች ላይ ደግሞ ማህፀን አከባቢ ማሳከክና ነጭ ፈሳሽ መውጣት፤ አልፎ አልፎ የሰውነት መቆነጣጠጥና ውስጥ ውስጡን የሚሄድ የሆነ ነገር የሚሄድ ዓይነት ስሜት መስማት ሁኔታዎች ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ በአንዳንድ የስኳር ህመምተኞች ላይ ምንም ዓይነት የህመም ምልክቶች አይታዩባቸውም፡፡

እነዚህ ምልክቶች ሲታዩ ፈጥኖ ወደ ህክምና ባለሙያ በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

#Ethiopia #Eyoha #Diabetes

Комментарии

Информация по комментариям в разработке