Nhatty Man - Senay - ናቲ ማን - ሰናይ -New Album 2023 - አዲስ አልበም 2015 e.c

Описание к видео Nhatty Man - Senay - ናቲ ማን - ሰናይ -New Album 2023 - አዲስ አልበም 2015 e.c

አልበሙን በመግዛት ድጋፎን ማሳየት ከፈለጉ
https://realnhattyman.bandcamp.com/al...

Supported by the Australian Government through the Australia Council for the Arts, its arts funding and advisory body.

፰ ሰናይ

ውብ ልበ ተራራ የሰው ልክ እያሉ
ሲያደንቁ ሲያገኑሽ አንቺን ያዩ ሁሉ
ጉጉቴ እንዳልናረ እንድያ እንዳልጨመረ
የልቤ በሞላ አፍፌ መሰከረ

የኔ ሴት ሰናይ ካሉኝም በላይ ሙሉ
የኔ ሴት ሰናይ አምሳለ እናት ጀግና ኩሩ

የእውነት ደስተኛ ማነው እንደኔ የታደለው
እመር ድመቅ ተብሎ በፍቅር የተሸለመው
ካሉኝም ከሰማሁት ሁሉ በላይ
ሆነሽ በልጠሽ ተገኝተሽ _
ሃሳቤን ጣልኩ አንቺው ላይ
ሆነ ሰመረለኝ ሞላ የልቤ
ፍቅርን ስጋራ ካንችው ቀርቤ
እንዲህ ነኝ እንዲያ ነኝ ብለሽ ሳታዎሪ
ተግባርሽ ይቀድማል ሆኖ ምስካሪ

ያሳደጏት የሚኮሩባት
ያመኗት የሚመኩባት
የእናቷ ልጅ ሙሉ
እንደ እናቴ ኩሩ
ያሳደጏት የሚኮሩባት
ያመኗት የሚመኩባት
የእናቷ ልጅ ኩሩ
እንደ እናቴ ሙሉ
ጀግና ሴት

Комментарии

Информация по комментариям в разработке