Logo video2dn
  • Сохранить видео с ютуба
  • Категории
    • Музыка
    • Кино и Анимация
    • Автомобили
    • Животные
    • Спорт
    • Путешествия
    • Игры
    • Люди и Блоги
    • Юмор
    • Развлечения
    • Новости и Политика
    • Howto и Стиль
    • Diy своими руками
    • Образование
    • Наука и Технологии
    • Некоммерческие Организации
  • О сайте

Скачать или смотреть የየካቲት 9 ሥንክሳር

  • kesisephrem
  • 2026-02-15
  • 218
የየካቲት 9 ሥንክሳር
  • ok logo

Скачать የየካቲት 9 ሥንክሳር бесплатно в качестве 4к (2к / 1080p)

У нас вы можете скачать бесплатно የየካቲት 9 ሥንክሳር или посмотреть видео с ютуба в максимальном доступном качестве.

Для скачивания выберите вариант из формы ниже:

  • Информация по загрузке:

Cкачать музыку የየካቲት 9 ሥንክሳር бесплатно в формате MP3:

Если иконки загрузки не отобразились, ПОЖАЛУЙСТА, НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если у вас возникли трудности с загрузкой, пожалуйста, свяжитесь с нами по контактам, указанным в нижней части страницы.
Спасибо за использование сервиса video2dn.com

Описание к видео የየካቲት 9 ሥንክሳር

ስንክሳር ዘወርኀ የካቲት 9

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ዘጠኝ በዚች ቀን የከበረ በሶርያ አገርላሉ መነኰሳት አባት የሆነ ታላቁ አባ በርሱማ አረፈ ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ሳሚሳጥ ከሚባል አገርሰዎች ውስጥ ናቸው አንድ በዋሻ ውስጥ የሚኖርሰው በእርሱ ላይ ትንቢትን ተናገረ ከመወለዱ አስቀድሞ ለአባቱ እንዲህ አለው የትሩፋቱ ዜና በሶርያ ሀገር ሁሉ የሚሰማ ጣዕም ያለው ፍሬ ከአንተ ይወጣል ከእርሱ የሚሆነውንም አስረዳው ።

ተወልዶም አድጎ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ በደረሰ ጊዜ ከወላጆቹ ሸሽቶ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ደርሶ በዚያ ስሙ አብርሃም ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጠ እርሱም ወላጆቹን ስለፈራ ከዚያ ገዳም ሰደደውና ሒዶ በአለት ውስጥ ኖረ በዚያም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ወሬውም በሶርያ አገሮች ሁሉ በተሰማ ጊዜ ብዙዎች ደቀመዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ የዚያ ቦታ ውኃ ግን እጅግ መራራ ነበር በላዩ በጸለየ ጊዜ ተለውጦ ጣፋጭ ሆነ ።

እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ ከእርሳቸውም በአንዲት ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከበአቱ ርቆ ሳለ የፀሐይ መግቢያ ሰዓት ተቃረበ የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ወደ በአቱም እስቲደርስ ያን ጊዜ ፀሐይን አቆመለት ።

በሌላ ጊዜም እንዲህ ሆነ ረዓም የምትባል አገርነበረች ስዎቿም ከሀዲዎች ናቸው ። በላያቸውም ዝናብ ተከለከለ በተጨነቁም ጊዜ ወደ ከበረ አባ በርሱማ መጥተው ለመኑት እርሱም ገሠጻቸው እንዲህም አላቸው ከክህደታችሁ ተመልሳችሁ በእግዚአብሔር ብታምኑ እርሱ ብዙ ዝናብን ያዘንብላችኋል እነርሱም እናምንበታለን አሉት ። በዚያን ጊዜ ጌታችንን ለመነውና ብዙ ዝናብ ዘነበላቸው የሀገር ሰዎችም ሁሉ በጌታችን አመኑ ።

እንዲሁም ሰዎቿ ከሀድያን የሆኑ ሌላ ሀገር ነበረች እነርሱንም ገሥጾ መክሮ አስተምሮ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የጣዖቶቻቸውንም ቤቶች አፈረሰ ። ይህም ቅዱስ ለራሱ ቦታ አዘጋጅቶ በዚያ ሳይቀመጥ ሃምሣ አራት ዓመት ቁሞ ኖረ ከመትጋት የተነሣ ሲደክመው ከናሱ ግድግዳ ላይ ተደግፎ ያሸልባል በየሰባት ቀንም ይጾማል ።

የከበረ አባ ስምዖን ዘዓምድ ሊያየው ወዶ ወደርሱ ላከ የትሩፋቱንና የቅድስናውን ዜና ከብዙዎች ሰዎች ሰምቶ ነበርና እርሱም ወደ አባ ስምዖን መጥቶ እርስበርሳቸው በረከትን ተቀባበሉ ከዚህም በኋላ ወደ ገዳሙ ተመለሰ ።

በሶርያ አገርም አስተማረ በፊታቸው ተአምራትን በአደረገ ጊዜ በትምህርቱ ብዙዎች አመኑ ። ዳግመኛም ወደ ታናሹ ቴዎዶስዮስ ንጉሥ ሒዶ በቀናች ሃይማኖት አጸናው ንጉሡም ብዙ ገንዘብን ሰጠው እርሱ ምንም ምን አልወሰደም በአንጾኪያም አገር በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዲኖረው

ንጉሥ ጻፈለትና ኀቲም ቀለበቱን ሰጠው ።

በከሀዲው ንስጥሮስ ምክንያት ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት በኤፌሶን ከተማ በተሰበሰቡ ጊዜ ከእሳቸው ጋር ይህ ቅዱስ አለ ። ከእርሳቸውም ጋርንስጡርን አወገዘው ዳግመኛም በአንጾኪያ አገር ያሉ መኳንንት መሳፍንት ሹማምንት ሁሉም ይታዘዙለት ዘንድ ንጉሥ ደብዳቤን ጻፈለት እርሱም በጎ ሥራ እንዲሠሩ በሃይማኖት እንዲጸኑ የሚያዝዝ ደብዳቤ በመጻፍ በንጉሥ ኀቲም ቀለበት እያተመ ለሀገሮች ሁሉ የሚልክ ሆነ ።

ክፋዎች ሰዎችም ጠሉት በንጉሥም ዘንድ ነገርሠሩበት እንዲህም አሉት እነሆ አባ በርሱማ እንደ ዓለም ሰው ሁኖ ይበላል ይጠጣል መልካም ልብስንም ይለብሳል ንጉሥም ሰለ አባ በርሱማ የተነገረውን ያረጋግጥ ዘንድ ከባለሟሎቹ አንዱን ላከ

የንጉሡም ባለሟል ወደ አባ በርሱማ በደረሰ ጊዜ በእርሱ ላይ ከተነገረው ምንም ምን ያገኘው የለም ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ወሰደው ንጉሥም ቀድሞ ከሚያውቀው ከመንፈሳዊ ሥራው ልውጥ ሆኖ ያገኘው ነገር የለም ንጉሡም ታላቅ ክብርን አከበረው ወደ ቦታውም መለሰው ።

መናፍቁ ንጉሥ መርቅያንም የኬልቄዶንን ጉባኤ በሰበሰበ ጊዜ የንጉሥ አማካሪዎች አባ በርሱማን እንዳያስመጣ ንጉሡን መከሩት እንደማይፈራና እንደማያፍር ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ተከራክሮ

ረትቶ እንደሚያሳፍራቸውም ስለሚያውቁ ነው ።

አንዱን ክርስቶስን ወደ ሁለት የከፋፈሉበት ይህ ጉባኤ በተፈጸመ ጊዜ የከበረ አባ በርሱማ ተጣላቸው ነቀፋቸው ቃላቸውንም በመሻር አወገዛቸው እነርሱም ወደ ንጉሥ ወንጅለው በጽሑፍ ከሰሱት ንጉሡም ልኮ ወደርሱ አስቀረበው ግን በላዩ ስለ አደረ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሊቃወመው አልቻለም በሊቁ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ ሰለ አደረገችው ክፋት ንግሥቲቱን ረገማት ከጥቂት ቀንም በቀርአልኖረችም በክፉ አሟሟትም ሞተች ።

ከዚህም በኋላ መናፍቃን የሚቃወሙት ሆኑ ምእመናን እንዳይታዘዙለት ወደ ሀገሮች ሁሉ ጽፈው የሚልኩ ሆኑ እነርሱ ግን አልተቀበሏቸውም ለእርሱ መታዘዛቸውንም አልተዉም ። ዳግመኛም በጐዳና ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ ሁለት መቶ መናፍቃን ሰዎች ከመናፍቃን ኤጴስቆጶሳት ጋርተስማምተው ወደ እርሳቸው እንዲመጣና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሔዱ ሁነው ላኩበት መጥቶም አብሮ በተጓዘ ጊዜ ደንጊያዎችን አንሥተው ጣሉበት ደንጊያዎቻቸውም ወደ ራሳቸው የሚመለሱ ሆኑ በፍርሃትም ከእርሱ ሸሹ ።

እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም እሥረኛነት ሊአወጣው በወደደ ጊዜ መልአኩን ወደርሱ ልኮ ከአራት ቀን በኋላ ከዓለም እንደሚፈልስ ነገረው በዚያንም ጊዜ በዙሪያው ወዳሉ አገሮች ምእመናንን ያጽናናቸው ዘንድ ረድኡን ላከው እርሱም ሲዞር የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ ወደምትኖርበት ቦታ ደረሰና

የከበረች የቅዱስ ዮሐንስን ራስ እጅ ነሣት ስለ ከሀዲው ስለ ንጉሥ መርቅያን በማልቀስ ለመነ ።

እንዲህ የሚልም ቃል ከመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ወጣ አባ በርሱማ ወደ እግዚአብሔር ስለ ከሰሰው ያ መርቅያን ሙቷልና አትፍራ ። የከበረ አባ በርሱማ ረድኡን ባረከውና በሰላም አረፈ ።

ከበአቱም ደጃፍ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን መሰሶ ተተክሎ ታየ ። ምእመናንም ሁሉ ከሩቅ አይተው ወደርሱ መጡ አርፎም አገኙት ። ከሥጋውም ተባረኩ በላዩም አለቀሱ ከእርሱም ስለመለየታቸው እጅግ አዘኑ እንደሚገባም አየዘመሩና እያመሰገኑ ገንዘው በመቃብር አኖሩት ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን

በዚችም ቀን የከበረ ሰማዕት ጴጥሮስ መታሰቢያው ነው ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን ።

የካቲት ፱ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኰሳት ሁሉ አባት)

፪.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊ የመነኰሱበት በዓል

፫.ቅዱስ ጳውሎስ ሶርያዊ ሰማዕት

፬.ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት

፩."፫፲፰ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ

፪.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን

፫.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ ኢትዮዽያዊ

፬.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት

ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ሰው ሆይ ፥ መልካሙን ነግሮሃል ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው ፍርድን ታደርግ ዘንድ ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን

ሚክ. ፮፥፮-፰
‪@Fewus_Menfesawi_Aba_Gebrekidan‬ ‪@yekidusantarik‬ ‪@Donkeybego‬

Комментарии

Информация по комментариям в разработке

Похожие видео

  • 🔴 ለዐቢይ ጾም የተመረጡ የንስሃ መዝሙሮች ስብስብ | Yensha Mezmur Orthodox Ethiopian | Mezmur Orthodox Ethiopian
    🔴 ለዐቢይ ጾም የተመረጡ የንስሃ መዝሙሮች ስብስብ | Yensha Mezmur Orthodox Ethiopian | Mezmur Orthodox Ethiopian
    1 год назад
  • "የዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ ቁጥር ሁለት ሙሉ ዝማሬ" - ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ @-betaqene4118
    3 года назад
  • በዘላለም ኪዳን ቁጥር ፬ (4) -  ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን (Full Album)
    በዘላለም ኪዳን ቁጥር ፬ (4) - ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን (Full Album)
    5 лет назад
  • 🔴 የዐቢይ ጾም ጉዞ ክፍል 1 || እጅግ ድንቅ ትምህርት ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ ስብከት Aba Gebrekidan Girma New 2025
    🔴 የዐቢይ ጾም ጉዞ ክፍል 1 || እጅግ ድንቅ ትምህርት ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ ስብከት Aba Gebrekidan Girma New 2025
    1 год назад
  • 🔴 የንስሃ መዝሙሮች ስብስብ | Yensha Mezmur Orthodox Ethiopian | Mezmur Orthodox Ethiopian - የንስሀ መዝሙር
    🔴 የንስሃ መዝሙሮች ስብስብ | Yensha Mezmur Orthodox Ethiopian | Mezmur Orthodox Ethiopian - የንስሀ መዝሙር
    11 месяцев назад
  • 🛑የዓቢይ ጾም መዝሙራት
    🛑የዓቢይ ጾም መዝሙራት "የተመረጡ የንስሐ መዝሙር " ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ #NEW yeaby tsom mezmurat yetemeretu yenisha
    2 недели назад
  • 🟠
    🟠"ወደ ንስሃ የሚመሩ የማለዳ ዝማሬዎች" #በመንበርከክ #ማነው_እንደኔ #የታል_አንተን_መፍራት #ፍቅር_ነህ #መበርቻዬ_ነህ_መጽናኛዬ #የእውነትን_መንገድ
    1 год назад
  • እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል ‘’ምልክቴ ነሽ’’ ‘’ላመስግንህ የኔ ጌታ’’ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ @21media27
    እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል ‘’ምልክቴ ነሽ’’ ‘’ላመስግንህ የኔ ጌታ’’ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ @21media27
    1 месяц назад
  • የየካቲት 8 ሥንንክሳር #አረጋዊ ስምዖን ጌታን ሲያቀፈው ምን አለ#ነቢይት ሐና#ደጉ ኤልያስ#አመተ ክርስቶስ
    የየካቲት 8 ሥንንክሳር #አረጋዊ ስምዖን ጌታን ሲያቀፈው ምን አለ#ነቢይት ሐና#ደጉ ኤልያስ#አመተ ክርስቶስ
    2 недели назад
  • የየካቲት 28 ሥንክሳር#ሰማዕቱ ቴዎድሮስ ሮማዊ#kduse tewodros semaetu#ortodoxawi history #አማኑኤል አምላክ
    የየካቲት 28 ሥንክሳር#ሰማዕቱ ቴዎድሮስ ሮማዊ#kduse tewodros semaetu#ortodoxawi history #አማኑኤል አምላክ
    7 часов назад
  • የድንግል ማርያም መዝሙሮች / አጽናኝ አረጋጊ የማርያም መዝሙሮች / Yedngil maryam mezmuroch
    የድንግል ማርያም መዝሙሮች / አጽናኝ አረጋጊ የማርያም መዝሙሮች / Yedngil maryam mezmuroch
    6 месяцев назад
  • 🔴👉በዐብይ ጾም መደመጥ ያለበት ልዩ ስብከት❗️መምህር ኢዮብ ይመኑ@Mataniya23
    🔴👉በዐብይ ጾም መደመጥ ያለበት ልዩ ስብከት❗️መምህር ኢዮብ ይመኑ@Mataniya23
    2 недели назад
  • የጥር ድርሳነ ዑራኤል- Archangel St Urael
    የጥር ድርሳነ ዑራኤል- Archangel St Urael
    1 месяц назад
  • የዘማሪት መስከረም ወልዴ ሙሉ አልበም
    የዘማሪት መስከረም ወልዴ ሙሉ አልበም
    3 года назад
  • 🛑 ፍካሬ ኢየሱስ - የዓለም መጨረሻ - Fkare Eyesus | @mahtebmedia21 | #eotc #ethiopia
    🛑 ፍካሬ ኢየሱስ - የዓለም መጨረሻ - Fkare Eyesus | @mahtebmedia21 | #eotc #ethiopia
    1 год назад
  • Ethiopian News¶የካቲት 28/2018 ዓ.ም ከኦሮሚያ ክልል የተሰሙ መረጃዎች ¶March 07/2026#Anchormedia
    Ethiopian News¶የካቲት 28/2018 ዓ.ም ከኦሮሚያ ክልል የተሰሙ መረጃዎች ¶March 07/2026#Anchormedia
    6 часов назад
  • ጾመ ኣርብዓ ብመምህር ኣስመላሽ ገብረ ሕይወት
    ጾመ ኣርብዓ ብመምህር ኣስመላሽ ገብረ ሕይወት
    3 недели назад
  • 🚨СИТУАЦИЯ НАКАЛЯЕТСЯ! Это уже НЕ ПРОСТО УГРОЗЫ. Иран и Азербайджан на ГРАНИ ВОЙНЫ. Разбор от ЮНУСА
    🚨СИТУАЦИЯ НАКАЛЯЕТСЯ! Это уже НЕ ПРОСТО УГРОЗЫ. Иран и Азербайджан на ГРАНИ ВОЙНЫ. Разбор от ЮНУСА
    7 часов назад
  • #ዳናይት የአቤል መክብብ መዝሙሮች - Abel Mekbib Mezmur Collection
    #ዳናይት የአቤል መክብብ መዝሙሮች - Abel Mekbib Mezmur Collection
    10 месяцев назад
  • እግዚአብሔር ‘ያስታረቃቸው’ ቅዱሳን / የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ታሪክ  #Orthodox #Tewahdo #Church
    እግዚአብሔር ‘ያስታረቃቸው’ ቅዱሳን / የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ታሪክ #Orthodox #Tewahdo #Church
    3 недели назад
  • О нас
  • Контакты
  • Отказ от ответственности - Disclaimer
  • Условия использования сайта - TOS
  • Политика конфиденциальности

video2dn Copyright © 2023 - 2025

Контакты для правообладателей video2contact@gmail.com