መተማመን እንዴት? Wie man vertraut?

Описание к видео መተማመን እንዴት? Wie man vertraut?

Generation und Regierung womit kombiniert? ትውልድ እና መንግሥት በምን ይጣመሩ?
በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተሻለ ዕድል ያገኘው ክስተት #ጭካኔ እና #አረማዊነት ነው። ሰውኛ እና ተፈጥሯዊነት ተሰደዋል ወይንም ተሰውረዋል። ገዢው ጭካኔ ሆኗል። ለጭካኔ እና ለአረማዊነት መሃንዲሱ ደግሞ #አናርኪዝም ነው። ኢትዮጵያ እንደ እኔ ዕይታ በተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩት አገሮች በተፃፈ ህገ - መንግሥት ስትተዳደር፤ እንዲሁም ባልተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩት አገሮችም ባልተፃፈ ህግ ትተዳደራለች። አሁን በኢትዮጵያ እኔ በምታዘበው ልክ ሁለቱም ሥራ ላይ ለማዋል ጋዳ እየሆነ ነው። #ያቃሰተ !#ማቃት ነው እኔ እማስተውለው።
ይህ ሁኔታ አዲስ የተለዬ ፍፁም ጨዋ በሆነ፦ እራሱን ዝቅ አድርጎ በትሁት መንፈስ የሚተዳደር ሥርዓት ባለው ህግን በሚያከብር ግብረ ኃይል ወይንም ቲም ካልተመራ ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ የኢትዮጵያ ህልውናም አደጋ ላይ ይወድቃል። በተለይ ህፃናት፤ አዛውንታት፤ ህሙማን፤ ሴቶች፤ ታዳጊ ወጣቶች እጅግ ይጎዳሉ። አሁን ከምናደምጠው በላይ። ጉዳቱ ዘመን ሊጠግነው የማይችል ይሆናል።
ቸር አስበን ቸር እንሁን። ቅን አስበን ቀና እንሁን።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке