Logo video2dn
  • Сохранить видео с ютуба
  • Категории
    • Музыка
    • Кино и Анимация
    • Автомобили
    • Животные
    • Спорт
    • Путешествия
    • Игры
    • Люди и Блоги
    • Юмор
    • Развлечения
    • Новости и Политика
    • Howto и Стиль
    • Diy своими руками
    • Образование
    • Наука и Технологии
    • Некоммерческие Организации
  • О сайте

Скачать или смотреть ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

  • ማኅሌት Mahlet
  • 2020-06-18
  • 10182
ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
  • ok logo

Скачать ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ бесплатно в качестве 4к (2к / 1080p)

У нас вы можете скачать бесплатно ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ или посмотреть видео с ютуба в максимальном доступном качестве.

Для скачивания выберите вариант из формы ниже:

  • Информация по загрузке:

Cкачать музыку ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ бесплатно в формате MP3:

Если иконки загрузки не отобразились, ПОЖАЛУЙСТА, НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если у вас возникли трудности с загрузкой, пожалуйста, свяжитесь с нами по контактам, указанным в нижней части страницы.
Спасибо за использование сервиса video2dn.com

Описание к видео ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

#እንኳን_ለቅዱስ_ሚካኤል_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እነሆ ይህች ዕለት ለቅዱሳን መላእክት አለቃቸው የሆነ፣ የስሙ ትርጓሜ "ማን እንደ አምላክ" የሆነ፣ የመልአከ ምሕረት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመት ዓመታዊ መታሰቢያ ናት፡፡ ፈጣሬ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር ዕፁብ ድንቅ በሆነ በማይመረመር ጥበብ ፍጥረታትን ከፈጠረባቸው ስድስት ዕለታት በመጀመርያዪቱ ዕለት በእሑድ መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ በተሰጣቸው አእምሮ ይመራመሩ ዘንድ ተሠወራቸው፡፡ ታድያ ይህን ጊዜ በመላእክት ዓለም ሁከት ተነሣ፤ ማን እንደፈጠራቸው አላወቁምና፡፡ ሳጥናኤልም ከወደ በላዩ ተመለከተ፤ ከእርሱ በላይ የሆነ ማንንም አላገኘም፡፡ ወደ ታችም ተመለከተ፤ እልፍ አእላፋት መላእክት ፈጣሪያቸው ማን እንደሆነ እየጠየቁ ነው፡፡ ይህን ጊዜ ነበር "እኔ ፈጠርኋችሁ" ብሎ የመጀመርያውን የሐሰት ንግግር የተናገረው፡፡ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ባለንበት እንጽና" ድንቅ ቃል ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ጸንተው ሲቆሙ በሳጥናኤል ነገድ ግን ክሕደት በርክቶ ነበር፡፡ ታዲያ ይህች ቀን ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን ተዋግቶ ያሸነፈባት፣ የማይገባውን አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በከሐዲው ዲያቢሎስ ምትክ ከወገኖቹ ከመላእክት ሁሉ በላይ ሆኖ በሁሉ ቅዱሳን መላእክት ላይ ከልዑል እግዚአብሔር ከክብሩና ከገናናነቱ ጋር ሹመትን ያገኘባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ሹመቱም በአንድ ነገድ ላይ ብቻ አይደለም፤ በሁሉ የመላእክት ነገድ ላይ እንጂ፡፡ እርሱም በመንፈሳዊ ሕይወት የደከሙትን የሚያበረታ፣ አርምሞ ትዕግሥትን የሚወድድ፣ ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን፣ የምሕረትና የመዳኛ፣ የሰላም መልአክ ትሑትና ርኅሩኅ ነው፡፡ ዳግመኛም ይህች ዕለት ንዕድ ክብርት የሆነች ቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ናት፡፡ ቅድስት አፎምያ አንድ ሃይማኖቱ የቀና እግዚአብሔርንም የሚፈራ ስሙ አስተራኒቆስ የተባለ ታላቅ መኰንን ሚስት ነበረች፡፡ ባሏ አስተራኒቆስ ለምስኪናን ምጽዋትን የሚሰጥ፣ በየወሩም ሦስት ጊዜ በዓላትን የሚያከብር ደግ ሰው ነበር፡፡ እነዚህም በዓላት ወር በገባ በ፲፪ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፣ በ፳፩ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እና በ፳፱ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በዓላት ናቸው፡፡ ታዲያ በአንድ ወቅት ይህ ሰው ታመመ፤ የሚሞትበት ጊዜም ደረሰ፡፡ ይህን ጊዜ ሚስቱን አፎምያን እርሱ በሕይወት ዘመኑ ያደርገው የነበረውን መመጽወትን እንዳታስቀር ነገራት፡፡ የበዓላቱን መታሰቢያም አታስታጕል ዘንድ አደራ አላት፡፡ እርሷም ባሏን፣ በቤቷ አኑራ ከሰይጣን ፈተና ትከላከልበት ዘንድ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አሥሎ ይሰጣት ዘንድ ጠየቀችው፤ እርሱም ይህን ካደረገላት በኋላ ዐረፈ፡፡ ከባሏ ማረፍ በኋላ ቅድስት አፎምያ እርሱ ይሠራው ከነበረው በጎ ሥራ ሁሉ አንዳች ሳታጓድል እየሠራች በሃይማኖት ጸንታ ትኖር ጀመር፡፡ የክፋት አባት የሆነው ዲያቢሎስም በጎ ምግባሯን ባየ ጊዜ በቅንዓት ተነሣባት፤ በብዙም ፈተናት፡፡ በመበለት መነኰሳይት ተመስሎ እየመጣ በጣም እንደሚያዝንላት፣ ዕድሜዋ ሳያልቅ ገንዘቧም በምጽዋት ከማለቁ በፊት ብታገባና ልጆች ወልዳ ብትኖር እንደሚሻል ይመክራት ጀመር፡፡ ቀጥሎም፤ "ባልሽ እንደሆነ መንግሥተ ሰማያትን ወርሷል ምጽዋትን አይፈልግም፡፡" ብሎ ሊያሰናክላት ሞከረ፡፡ እርሷ ግን፤ "ከእንግዲህ ከሌላ ወንድ ጋር ላልገናኝ ለእግዚአብሔር የመሐላ ቃሌን ሰጥቻለሁና አላደርገውም፡፡" ብላ መለሰች፡፡ "ርግቦችና ቁራዎች ስንኳ ባላቸው ከሞተ ሌላ ባል አያውቁም፡፡ በአርአያ እግዚአብሔር ለተፈጠሩ ሰዎችማ ይህን ማድረግ እንዴት ይገባል?" አለችው፡፡ ምንም ያህል ቢጥርም እንኳን ነገሩን እንዳልተቀበለችው ባየ ጊዜ መልኩን ለውጦ ዛሬ ባይቻለውም እንኳን በሌላ ቀን መጥቶ ሃሳቡን እንድትቀበል እንደሚያደርጋት በመናገር ጮኸ፤ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ኀፍረትን አከናንባ አዋርዳ አጠፋችው፡፡ በሰኔ ፲፪ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ቀን ዲያቢሎስ ዳግመኛ ሊፈትናት ብርሃናዊ መልአክ መስሎ የብረት ዘንግ ይዞ በሌሊት ወደ እርሷ መጣ፡፡ ስለ በጎ ሥራዎችዋ ስለ መልካምነቷ ከክፉ እንዲጠብቃት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ እንደመጣ ነገራት፡፡ ስሙን ብትጠይቀው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ዋሽቶ ነገራት፡፡ "እነሆ ገንዘብሽን በምጽዋት ማባከንሽን ትተሸ ከምእመናን ወገን ለአንዱ ሚስት ትሆኚ ዘንድ እግዚአብሔር ወደ አንቺ ልኮኛል፡፡ በዚህም ላይ ያለ ባል የምትኖር ሴት መቅዘፊያ እንደሌላት ወይም መልሕቅዋ እንደተቆረጠ መርከብ መሆንዋን ዕወቂ፡፡" አላት፡፡ ከብሉይ መጻሕፍት እነ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ፣ ዳዊትን እያነሣ ያገቡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ባለሟሎች የነበሩ መሆናቸውን ጠቅሶ ማግባት እንዳለባት ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያም መልሳ በእውነት የእግዚአብሔር መልአክ ከሆነ የመታወቂያው ምልክት የሚሆን ትእምርተ መስቀሉ ወደየት እንዳለ ጠየቀችው፡፡ እርሱም፤ "በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ ያለ ምልክት የለም፡፡" አላት፡፡ በእጅጉ ስለተጠራጠረችው ባሏ ከመሞቱ በፊት አሠርቶ የሰጣትን የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ልታመጣ ወደ ሥዕል ቤቷ ሔደች፡፡ ይህን ጊዜ ዲያቢሎስ መልኩ ተለወጠ፤ ዘልሎም አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያ ወደ ቅዱስ ሚካኤል እንዲያድናት እየጮኸች ለመነች፡፡ ለመልካም ሥራ የሚፋጠን መልአከ ኃይል ቅዱስ ሚካኤልም መጥቶ አዳናት፡፡ ሰይጣኑንም በብዙ ሥቃይ አሠቃየው፡፡ ሰይጣኑም እግዚአብሔር የሰጠው ዘመኑ ሳይፈጸም አያጠፋው ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን ተማፀነው፤ ያን ጊዜም ተወው፡፡ ከዚህ በኋላም የቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ ቀን ደርሷልና ቅዱስ ሚካኤል ሔዳ ቤቷን ታዘጋጅ ዘንድ ነገራት፡፡ "በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ትለያለሽ፡፡ እነሆ እግዚአብሔርም ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን ልቡና ያላሰበውን ዋጋሽን አዘጋጅቶልሻል፡፡" ብሎ ከነገራት በኋላ ሰላምታ ሰጥቷት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ እርሷም ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ከአዘጋጀች በኋላ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ እና ካህናቱ ዘንድ መልእክተኛ ላከች፤ ቀጥሎም በእነርሱ እጅ ለነዳያንና ለችግረኞች ምጽዋትን ይሰጡላት ዘንድ ገንዘብን ሰጠች፡፡ ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል በደረቷ እና በፊቷ ላይ አድርጋ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየች የቅዱስ ሚካኤል በዓል በሚከበርበት ዕለት በሰኔ ፲፪ ቀን በክብር ዐረፈች፡፡ አምላከ አማልክት ልዑል እግዚአብሔር ከክፉ ዲያቢሎስ እጅ ያስጥላት ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን ወደ ቅድስት አፎምያ እንደላከ እኛንም በፈተናዎቻችን ሁሉ ይረዳን ዘንድ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡ ይቆየን……. ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Комментарии

Информация по комментариям в разработке

Похожие видео

  • ግንቦት 21 ደብረ ምጥማቅ ማርያም ወረብ|Ginbot 21 Debre Mitmaq Wereb|በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ|አ.አ| መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
    ግንቦት 21 ደብረ ምጥማቅ ማርያም ወረብ|Ginbot 21 Debre Mitmaq Wereb|በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ|አ.አ| መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
    5 лет назад
  • ⚡️СРОЧНО! Москва ОБЪЯВИЛА ПРО ПОРАЖЕНИЕ после АТАКИ Трампа! Гневное ЗАЯВЛЕНИЕ Лаврова. Важное 06.03
    ⚡️СРОЧНО! Москва ОБЪЯВИЛА ПРО ПОРАЖЕНИЕ после АТАКИ Трампа! Гневное ЗАЯВЛЕНИЕ Лаврова. Важное 06.03
    5 часов назад
  • መዘንጋት ባለበት | Mezengat Balebet | ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ| በዘማሪ ዲ.ን ጽናት ስለሺ|መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
    መዘንጋት ባለበት | Mezengat Balebet | ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ| በዘማሪ ዲ.ን ጽናት ስለሺ|መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
    5 лет назад
  • Союзник Путина убит / Приказ на ответный удар
    Союзник Путина убит / Приказ на ответный удар
    8 часов назад
  • ☦️Утренние молитвы с текстом - спокойное чтение и без спешки. Православные молитвы.
    ☦️Утренние молитвы с текстом - спокойное чтение и без спешки. Православные молитвы.
    8 дней назад
  • ሰኔ 21 በዓለ ህንጸተ ቤታ ለማርያም ወረብ| Sene 21 Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት | አ.አ | መናገሻ ገነተ ጽጌ
    ሰኔ 21 በዓለ ህንጸተ ቤታ ለማርያም ወረብ| Sene 21 Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት | አ.አ | መናገሻ ገነተ ጽጌ
    5 лет назад
  • Relaxing Nature Ambience Meditation🌼GOOD MORNING SPRING NATURE THERAPY🌷Flowery MEADOW Healing Sounds
    Relaxing Nature Ambience Meditation🌼GOOD MORNING SPRING NATURE THERAPY🌷Flowery MEADOW Healing Sounds
    7 лет назад
  • Война в Заливе: Кремль объявил Трампа врагом — теперь всё зависит от Ирана/№1105/ Юрий Швец
    Война в Заливе: Кремль объявил Трампа врагом — теперь всё зависит от Ирана/№1105/ Юрий Швец
    12 часов назад
  • МАТЬ И СЕСТРА ИЩУТ УБИЙЦ -
    МАТЬ И СЕСТРА ИЩУТ УБИЙЦ - "СВЯЗАЛИ, ОБЛИЛИ БЕНЗИНОМ, И ПОДОЖГЛИ. А ПОТОМ ПОДМЕНИЛИ ТЕЛО».
    19 часов назад
  • 24 часа в ХУДШЕМ ПОЕЗДЕ в Китае! Что внутри?
    24 часа в ХУДШЕМ ПОЕЗДЕ в Китае! Что внутри?
    21 час назад
  • ДНЕПР ПОД УГРОЗОЙ ЗАХВАТА // ЛЕТОМ - КАТАСТРОФА СО СВЕТОМ И ВОДОЙ // ХУЖЕ БЫВАЕТ
    ДНЕПР ПОД УГРОЗОЙ ЗАХВАТА // ЛЕТОМ - КАТАСТРОФА СО СВЕТОМ И ВОДОЙ // ХУЖЕ БЫВАЕТ
    2 часа назад
  • የሐምሌ 22 የቅዱስ ዑርኤል በዓል ወረብ | Hamle 22 Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ
    የሐምሌ 22 የቅዱስ ዑርኤል በዓል ወረብ | Hamle 22 Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ
    5 лет назад
  • 🔴 СРОЧНО ИРАН И ТРАМП НАСТРОЕНЫ ВОЕВАТЬ ДО ПОСЛЕДНЕГО #новости #одиндень
    🔴 СРОЧНО ИРАН И ТРАМП НАСТРОЕНЫ ВОЕВАТЬ ДО ПОСЛЕДНЕГО #новости #одиндень
    5 часов назад
  • ТЁТЯ ПОДПОЛКОВНИК обвинила Путина в некомпетентности В ГЛАЗА.  ОБНУЛЕНИЕ глобального ЮГА.
    ТЁТЯ ПОДПОЛКОВНИК обвинила Путина в некомпетентности В ГЛАЗА. ОБНУЛЕНИЕ глобального ЮГА.
    4 часа назад
  • የመስከረም17 በዓለ_መስቀል ወረብ በመምህር ኢያቄም ታደሰ የመ/ገ/ጽ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ #YeMeskerem17 #wereb #ortodox
    የመስከረም17 በዓለ_መስቀል ወረብ በመምህር ኢያቄም ታደሰ የመ/ገ/ጽ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ #YeMeskerem17 #wereb #ortodox
    3 года назад
  • Нежная музыка, успокаивает нервную систему и радует душу 🌸 целебная музыка для сердца
    Нежная музыка, успокаивает нервную систему и радует душу 🌸 целебная музыка для сердца
  • США-ИРАН: СБИТ ПЯТЫЙ САМОЛЕТ США. МОЩНЫЙ УДАР ПО ИЗРАИЛЮ. СТРАНЫ ЗАЛИВА РАЗРЫВАЮТ ДОГОВОР С США.
    США-ИРАН: СБИТ ПЯТЫЙ САМОЛЕТ США. МОЩНЫЙ УДАР ПО ИЗРАИЛЮ. СТРАНЫ ЗАЛИВА РАЗРЫВАЮТ ДОГОВОР С США.
    2 часа назад
  • 🔥ЛИПСИЦ: ДОЛЛАР по 100 – это НАЧАЛО! Денег НЕТ: Массовые УВОЛЬНЕНИЯ в Москве @i_gryanul_grem
    🔥ЛИПСИЦ: ДОЛЛАР по 100 – это НАЧАЛО! Денег НЕТ: Массовые УВОЛЬНЕНИЯ в Москве @i_gryanul_grem
    3 часа назад
  • 💣Срочно! ПЕРЕЛОМ НА ФРОНТЕ. ВОЙСКА РФ УХОДЯТ НА НОВОЕ НАПРАВЛЕНИЕ. Жданов: это разрежет ОБОРОНУ ВСУ
    💣Срочно! ПЕРЕЛОМ НА ФРОНТЕ. ВОЙСКА РФ УХОДЯТ НА НОВОЕ НАПРАВЛЕНИЕ. Жданов: это разрежет ОБОРОНУ ВСУ
    6 часов назад
  • ረድተሀልና ባህራንን | በዘማሪ ዲ.ን. እሱባለው ዳዲ | የዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሐኑ መዝሙር | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
    ረድተሀልና ባህራንን | በዘማሪ ዲ.ን. እሱባለው ዳዲ | የዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሐኑ መዝሙር | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
    5 лет назад
  • О нас
  • Контакты
  • Отказ от ответственности - Disclaimer
  • Условия использования сайта - TOS
  • Политика конфиденциальности

video2dn Copyright © 2023 - 2025

Контакты для правообладателей video2contact@gmail.com