Logo video2dn
  • Сохранить видео с ютуба
  • Категории
    • Музыка
    • Кино и Анимация
    • Автомобили
    • Животные
    • Спорт
    • Путешествия
    • Игры
    • Люди и Блоги
    • Юмор
    • Развлечения
    • Новости и Политика
    • Howto и Стиль
    • Diy своими руками
    • Образование
    • Наука и Технологии
    • Некоммерческие Организации
  • О сайте

Скачать или смотреть ግብፅ በኢትዮጵያ ተከሰሰች

  • Daily_adiss
  • 2025-09-08
  • 4805
ግብፅ በኢትዮጵያ ተከሰሰች
  • ok logo

Скачать ግብፅ በኢትዮጵያ ተከሰሰች бесплатно в качестве 4к (2к / 1080p)

У нас вы можете скачать бесплатно ግብፅ በኢትዮጵያ ተከሰሰች или посмотреть видео с ютуба в максимальном доступном качестве.

Для скачивания выберите вариант из формы ниже:

  • Информация по загрузке:

Cкачать музыку ግብፅ በኢትዮጵያ ተከሰሰች бесплатно в формате MP3:

Если иконки загрузки не отобразились, ПОЖАЛУЙСТА, НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если у вас возникли трудности с загрузкой, пожалуйста, свяжитесь с нами по контактам, указанным в нижней части страницы.
Спасибо за использование сервиса video2dn.com

Описание к видео ግብፅ በኢትዮጵያ ተከሰሰች

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ለFIFA ክስ አቀረበች።

ትላንትና በግብፅ፣ ካይሮ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ያደረገችውን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።

ከዚህ ጨዋታ ጋር በተያያዘ የግብፅ ደጋፊዎች የፈጸሙትን ተግባር በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል FIFA ክስ አስገብቷል።

ፌዴሬሽኑ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን የፍፁም ቅጣት ምት ሲያገኝ " ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ እይታውን ሊረብሽ የሚችሉ መብራቶች (ጨረር) አይኑ ላይ ተደርገውብታል " ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በጨዋታው ወቅት ለማየት እንደተሞከረውና በስታዲየሙ ተገኝቶ በምስል ለማስቀረት እንደቻለው የኢትዮጵያ የፊት መስመር ተጫዋቾች በሚያጠቁበት ጊዜ ድርጊቱ በተደጋጋሚ ይፈፀም ነበር።

የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ይህን ድርጊት በተደጋጋሚ ጊዜ በተለያዩ ጨዋታዎች ላይ ሲያደርጉ ይስተዋላል።

FIFA በስታዲየም ቁጥጥር ህገ ደንቡ መሰረት ተንቀሳቃሽ መብራቶች / ጨረር (Laser Pointers) ወደ ስታዲየም ይዞ መግባትን ይከለክላል።

ሌላው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር የታየውን አሳፋሪ የግብፅ ደጋፊዎችን ድርጊት ይመለከታል።

የግብፅ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ክብር የሚነካ ተግባር መፈጸማቸውን በመግለፅ ፌዴሬሽኑ ለFIFA ክሱን አቅርቧል።

የግብፅ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር የአንድን ሀገር ክብር በማይመጥን መልኩ ከፍተኛ ጩኸት እያወጡ በማወክ ፣ ፊሽካ በመንፋት እንዲሁም የተለያዩ ድምፆችን በማሰማት ብሔራዊ መዝሙሩን ሲረብሹ ነበር።

ይህ የግብፃውያን ድርጊት የFIFA የዲሲፕሊን ኮድን የሚጥስ በመሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክሱን ለFIFA አቅርቧል።

ፌዴሬሽኑ FIFA የቀረበውን ክስ ተመልክቶ ተገቢውን ምርመራ ከፍቶ የግብፅ ደጋፊዎች ለፈጸሙት ተግባር በግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን ጠይቋል።

FIFA ከፌዴሬሽኑ የቀረበለትን ክስ ተመልክቶ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке

Похожие видео

  • О нас
  • Контакты
  • Отказ от ответственности - Disclaimer
  • Условия использования сайта - TOS
  • Политика конфиденциальности

video2dn Copyright © 2023 - 2025

Контакты для правообладателей [email protected]