ጥቂት የምክር ቃል | ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ | Pastor Tesfaye Gabiso | Halwot Emmanuel United Church

Описание к видео ጥቂት የምክር ቃል | ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ | Pastor Tesfaye Gabiso | Halwot Emmanuel United Church

ጥቂት የምክር ቃል | ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ
📖 3 ዮሐንስ 1 (3 John)
2፤ ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።
● እንዲከናወንልን ምን እንድርግ?
➥ አማኝ ጌታ ቢፈቅድ እና ብንኖር ነው ማለት ያለበት፤ ይህ እግዚአብሔርን የማወቅ ምልክት ነው።
➥ አለማዊ የሆነ ሰው በራሱና ባለው ነገር ስለሚመካ ይህንን አይልም።
➥ እግዚአብሔር የሚፈቅደው ነገር እንዳለው ሁሉ የሚከለክለውም ነገር አለ።
➥ አማኝ ስራን ሊወድ ይገባል፤ ስንፍና የስኬት ጠር ነዉ።
➥ ጌታ በቃል ብቻ ሳይሆን በስራ የበረታ ነው።
➥ ስራን አቅደን መስራትና ታታሪ መሆን አለብን።
➥ እግዚአብሔር እኛ በአቅማችን ስንሰራ እርሱ ደግሞ ያሳካልናል፤ ከኛ በላይ የሆነውን ያሳካልናል።
➥ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ይከናወንልናል ።
➥ ቃሉን አጥንተን በልባችን ማስቀመጥ ልምድ ሊኖረን ይገባል።
➥ በማይመች ጊዜ እንኳን እንድናፈራ ያደርገናል።
➥ በእውነት መሄድ ዋና ነገር ነው፤ የክርስቲያን ዋና ነገር እውነተኛነት ነው።
➥ እውነተኛነት የታማኝነት መገለጫ ነው፤ እዉነተኛ ያልሆነ ሰው ግንኙነቱን ያሻክራል፤ እውነተኛነት ከእውነት ጋራ መተባበር ነው።
➥ በምድር የጀመርነው የክርስቶስን እሩጫ ከክርስቶስ ጋር ሆነን መጨረስ አለብን፤ መሞት ከጌታ ጋር ሆኖ እሩጫን ማጠናቀቅ ነው።
➥ አንድ ክርስቲያን ስኬታማ ነው የምንለው ከክርስቶስ ጋር ያለዉን ግንኙነት አለማቋረጥ ክርስቲያን ሆኖ ሲኖር ነው።
➥ የጌታን ነገር አስቀድመን መኖር ዋና ነው፤ ሩጫን በመጨረስ የአክሊል ሽልማትን መቀበል ነው ስኬት።
_ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
#አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ት ቤት አጠገብ ☎️ +251118407763 📱+251 973 422024

Комментарии

Информация по комментариям в разработке