Ethiopian Stew ቀይ ቁሌት

Описание к видео Ethiopian Stew ቀይ ቁሌት

ቀይ ቁሌቱን ለማዘጋጀት የሚረዳ የአበሳሰል መመሪያ
3 ኪሎ ደቆ የተከተፈ(ተፈጨ) ቀይ ሽንኩርት ድስት ውስጥ እንጨምር እና ከድነነው በራሱ ውሃ እንዲበስል ከድነን አንተወዋለን
ውሃውን ጨርሶ ሙክክብሎ ሲበስል 2 የቡና ሲኒ የምግብ ዘይት ጨምረን በደንብ እናማስለዋለን
6 የሾርባ ማንኪያ በርበሬ ጨምረን በደንብ እናሸዋለን በርበሬውን ስንጨምር ሁሉን በአንዴ ሳይሆን ትንሽ ትንሽ እየጨመርን ማማሰል ይኖርብናል ይህም በደንብ እንዲዋሃድ ይረዳናል
በርበሬውን በደንብ ካዋሃድነው በሃላ በቡና ማንኪያ ልኬት 3 የማቁላያ ቅመም እንጨምራለን
የማቁላያ ቅመሙ ጨምረን በሃላ ከ7-10 ደቂቃ ካሸነው በሃላ በቡና ማንኪያ ልኬት 2 የተፈጨ ኮረሪማ እንጨምራለን
ለተወሰነ ደቂቃ ኮረሪማውን ጨምረን ካሸነው በሃላ 1 የሾራባ ማንኪያ ብስል ቂቤ እንጨምር እና እናሸዋለን
አንድ ከግማሽ የሾርባ ማንኪያ ነጭ ሽንኩርት እንጨምርና ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ያህል እናሸዋለን
1 የሾርባ ማንኪያ ጨው እንጨምርና ለተጨማሪ 10 ደቂቃ በድንብ እናሸዋለን

Комментарии

Информация по комментариям в разработке