🌼 ተለቀቀ የአውደ ዓመት ዝማሬ || አበባየሆሽ አዲስ አመት ሆብለን መጣን Ye Addis amet mezmur Ye Awedeamet mezmur Abebayehosh

Описание к видео 🌼 ተለቀቀ የአውደ ዓመት ዝማሬ || አበባየሆሽ አዲስ አመት ሆብለን መጣን Ye Addis amet mezmur Ye Awedeamet mezmur Abebayehosh

#የመዝሙሩ_ግጥም
🌼 🌼
🌼የእንቁጣጣሽ መዝሙር🌼
🌼 🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበላችሁ/(፪)
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ

ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)
ጌቶች አሉ ብለን
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)
እሜቴ አሉ ብለን

አበባዮሽ 🌼 ለምለም

አበባዮሽ 🌼 ለምለም

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንቆቅልሽ - - ንግሥት
ልትፈትን ሄዳ - - ንግሥት
ንግስተ አዜብ - - ንግሥት
እናት ማክዳ - - ንግሥት
በልቧ ያለውን - - ንግሥት
አጫወታቸው - - ንግሥት
አሰቀምጣ አበባ- - ንግሥት
እያሳየችው - - ንግሥት
መአዛው የሚሸት - - ከሁለቱ
የቱ ነው አለቸው - - ከሁለቱ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ንግስት ሆይ ለጥያቄሽ ጥበብ አለሽ (*፪)

የአገር አድባር የሚሆነው ከልብ ሽተሽ(*፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንቆቅልሹ - - የሳባ
ከበድም ቢለው - - የሳባ
ጥበብ ሰላለው - - ንጉሡ
ሚሥጥሩን ሊያውቀው - - ንጉሡ
ክፈት መስኮቱን - - ሰለሞን
ቢለው ለሎሌው - - ሰለሞን
ገቡ ንቦቹ - - ሊቀስሙ
ከአባባው አርፈው - - ሊቀስሙ
ብልህ ጠቢቡ - - መለሠ
ለተጠየቀው - - በእውነት
ንጉስ ሰለሞን - - አለ
አልተሠወረው - - በእውነት

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ (*፪)

ኢትዩዮጲያ የዝና ስሟ በዓለም ተሠማ (*፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ለፈጣሪዋ - - ንግሥት
ምስጋና አቅርባ - - ንግሥት
ኢትዮጲያዊቷ - - ንግሥት
ንግስተ ሣባ - - ንግሥት
ጥበቡን አይታ - - ንግሥት
አደነቀችው - - ንግሥት
ወርቅ ሸቶውን - - ንግሥት
ዕንቁ ሰጠችው - - ንግሥት

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ንግስት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ (፪)

የአምላክን የፈጣሪያችን ስሙን ጠርተሽ (*፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የኢትዮጵያ ሠዎች - - ለንግሥት
ቆሙ በተራ - - ለንግሥት
እደጅ ሆነው - - ለንግሥት
ለዙፋን ክብሯ - - ለንግሥት
በመስከረም ወር - - ለንግሥት
ሀገር ስትገባ - - ለንግሥት
ይዘው ሥጦታ - - ለንግሥት
የፈካ አበባ - - ለንግሥት

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ (፪)

ኢትዮጲያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ (፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ኢየሩሳሌም - - ንግሥት
ደርሠሽ መጣሽ - - ንግሥት
እንኳን በክብር - - ንግሥት
ለዚህ አበቃሽ - - ንግሥት
ከአምላክ በረከት - - ንግሥት
ፍሬ አግኝተሽ - - ንግሥት
የዘሽ ስጦታ - - ንግሥት
ዕንቁ ለጣጣሽ - - ንግሥት

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ንግስት ሆይ ለታሪክሽ ክብር አለሽ (፪)

ልጆችሽ አበባዮሽ እያልን እናስታውስሽ (፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


የአባቶች ተስፋ - - ለፃድቃን
የነቢያት ትንቢት - - ለፅናት
የሙሴ ፅላት - - ለፀሎት
የአሮን በትር - - ለፅናት
የዳዊት መንግስት - - ለፅናት
ይዘሸ የመጣሽ - - ከጥንት
አምስቱን አውታር - - ለሠጠሽ
ለሀገር መሠረት - በእውነት

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ (፪)

ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስ ይበልሽ (፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

በህገ ልቦና - - ህጉን
ፈጣሪን አውቀሽ - - ህጉን
ህገ ነቢያትን - - ከዓለም
ፈጥነሽ ተቀበልሽ - - ከዓለም
በብሉይ ኪዳን - - ለጌታ
መስዋዕት አቅርበሽ - - ለጌታ
ተስፋ ካረጉት - - ከአይሁድ
ከአስራኤል - - ከአይሁድ
ህገ ወንጌልን- - በፊት
ይዘሽ ተገኘሽ - - በፊት

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ፀጋ አለሽ(፪)

ስለፈፀምሽ ሦስቱን ህግጋት ለፈጣሪሽ (፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ካለፈው ሰህተት - - ሁላችን
እንድንመለስ - - ሁላችን
አዲሱ ዓመት - - ለሁሉም
መጣ ማቴዎስ- - ለሁሉም
ይህም ያልፍና - - በጊዜው
ይመጣል ማርቆስ - - በጊዜው
ሌላው ይተካል - - በጊዜው
ዘመነ ሉቃስ - - በጊዜው
ወልደነጓድጓድ - - በጊዜው
ሲደርስ ዮሐንስ - - በጊዜው
በየአራት ዓመት - - በጊዜው
ለሁሉም ሲደርስ - - በጊዜው
በየዓመቱ - - መጥምቁ
ቅዱስ ዩሐንስ - - በጊዜው

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

አደይ የብርሃን ጮራ በዮሐንስ በራ(፪)

ኢትዮጵያ ባሕል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ (፪)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ልጅ አበባ ልጅ አበባዬ
አዬ ውዲቷ እናቴ
ልጅ አበባ እያለች እማማ
አዬ ውዲቷ እናቴ
ምክሯን ሁሌ እኔ እንድሰማ
አዬ ውዲቷ እናቴ
እያሻሸች እንድሆን ጤናማ
አዬ ውዲቷ እማማ
አዬ ውዲቷ እናቴ (፪)

🌼አበባ ለምለም 🌼 ቀጤማ ለምለም
🌼ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም (፪)🌼

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ🌼
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰዎት ብዬ (፪)
🌼
ይሸታል ዶሮ ዶሮ (፪) ከማምዬ ጓሮ (፪)
ይሸታል የወይን ጠጅ (፪) ከጋሽዬ ደጅ (፪)

ከበረው ይቆዩ ከብረው 🌼
አመት አወደ አመት ደርሰው
ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
ትሁት ሰው አክባሪ ሆነው
የፍቅር ሸማን ለብሰው🌼
ንስሐ ገብተው ቆርበው
🌼ከብረው ይቆዩ ከብረው



ዚቅ ሚድያ ZIQ MEDIA።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке