Tesfaye Gabiso Selected Songs👍እንደተቀበልኩት ምህረት👏እጅግ ተቸግሬ ስማጸን 👏🏼በጊዜውም አለጊዜውም👏🏼ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ👍

Описание к видео Tesfaye Gabiso Selected Songs👍እንደተቀበልኩት ምህረት👏እጅግ ተቸግሬ ስማጸን 👏🏼በጊዜውም አለጊዜውም👏🏼ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ👍

1. እጅግ ተቸግሬ ስማጸን አይተኸኝ
እግዚአብሄር ይኸ ነው ተስፋ ያደረኩት
ታማኝነቱን አይቸ እጄን ልቤን የሰጠሁት
ያላዋቂዎች ልቦና በሰዎች ተስፋ ያደርጋል
ግን እግዚአብሄር ብቻ ደህንነትን ያዘጋጃል

እጅግ ተቸግሬ ስማጸን አይተኸኝ
እኔ ካንተ ጋር ነኝ አትፍራ እያልከኝ
በመጽናናት ሞልተህ ደስታን ታስታጥቀኛለህ
የልቤ አምላክ ሆይ የዘላለም እድል ፈንታዬ ነህ

የተማሰ ጉድጓድ አቁሞ በኔ ላይ ያልዘጋ
ጉልበቴ ባለቀ ጊዜ ለብቻዬ አልተውከኝም
ስለትንሽዋ እምነቴ ለባላጋራ ስሞግት
የድል አምባ አስረገጥከኝ ውጊውን ሁሉ ፈጽመህ

ምስጋናዬን እያዜምኩኝ ባንተ ደስ ይለኛል
በከንቱ ለሚጠሉኝም ሞገስ አጎናጽህፈኛል
ዓለም ብትሰርዘኝም የህይወት መዝገብ አውቆኛል
እስከ መጨረሻው ድረስ ህይወቴ ባንተ ይጸናል

2. እንደተቀበልኩት ምህረት

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት
እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት

እስራቴን ቆርጠህ ቀንበሬን ሰብረሃል
ነፍሴ እንድታከብርህ ነጻ አውጥተኸኛል
ባርነት አበቃ ልጅ ነህ ብለኸኛል
በደምህ ቃል ኪዳን ያንተ አድርገኽኛል

የተስገምገመ ከውድቀት እንዲተርፍ
የደከመን ሁሉ በቃል እንድደግፍ
አንቃኝ በማለዳ ቀስቅሰኝ ከእንቅልፍ
ታማኝ ሎሌ አድርገኝ ልብን የሚያሳርፍ

ስንፍናዬን አርቅ በተስፋህ በትር
እንድተጋ እርዳኝ ከሰጠኸኝ ዙፋን ስር
እየሱስ ያድናል ብዬ እንድመሰክር
ህይወቴን ሙላልኝ በመስቀልህ ፍቅር

ጥበብ ለሌላቸው ለማያስተውሉ
ለተማሩም ሰዎች አውቀናል ለሚሉ
ወንጌሉን ልናገር እንዲድኑ አምነው
ለነዚህ ሁሉ እዳዬ ትልቅ ነው

ወንጌል አይቆጠብ አይወሰን በክልል
እስከምድር ዳር ይሂድ ቃልህ ሳይከለከል
ለቅርቡ ለሩቁ ጽድቅህም ይታደል
እየሱስን አግኝቶ ፍጥረት እሰይ ይበል


3. በጊዜውም አለጊዜውም

የጠላቴን ራስ ቀጥቅጠህ
ከመንጋጋው እኔን ነጥቀህ
ቅዱስ ደምህን አፍስሰህ
ለሙት ልጅህ ህይወት ሰጥተህ
ታላቁን መዳን ድኛለሁ
አሁንም መጽናት እሻለሁ

በጊዜውም አለጊዜውም በትግስት ጸንቸ ቁሜ
ፊትህን ለማየት እጓጓለሁ እሩጫዬን ፈጽሜ
ስለዚህ ፈቃድህ ይሁንልኝ ውድ አባቴ
በሰላም በጤና አድርሰኝ ከቤቴ

ስቅበዘበዝ መክረኸኛል
ስተክዝ አጽናንተኸኛል
ባቆስልህም ወደኸኛል
ዘወትር ተሸክምኸኛል
እስከዛሬ ችለኸኛል
ቅዱስ ስምህ አቁሞኛል


ዘወትር በሁሉም ስፍራ
አንተን ልመስል አንተን ልፍራ
ከአለም አድርገኝ ልዩ
በኔም ሕይወት አንተን ይዩ
ሥጋየን ለዓለም ሰቅዬ
ልጓዝ አንተን ተከትዬ

በድካም ሕይወቴ ላልቶ
አካሄዴም ተበላሽቶ
ቅዱስ ስምህ እንዳይሰደብ
አደራ ልጅህን አስብ
እስክትመጣልኝ በክብር
አንተን አስከብሬ ልኑር

በከፍታም በዝቅታም
በሃዘንም በደስታም
ሳልደናገር በርጋታ
በፈተናም ሳልረታ
በትጋት ፀንቸ በእምነት
ፊትህን ልየው በክብር

4. ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ

መዋረዳቸውን አይተህ አንተ ባረከሃቸው
የቤትህን ልጆች አንተ ሰበርሃቸው
ትእቢታቸው ቀርቶ በትሁት ልባቸው
እንባቸውን ሲያፈሱት ለአንተ አየሁዋቸው

ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ
እኔነቴ ቀርቶ ፀጋህ እንዲበዛልኝ
ትእቢቴን ሽረህ ትህትና አልብሰኝ (2)

ጌታ ዘወትር መሰበርን ሽቸ
አብዝቸ እጮሃለሁ ሌት ተቀን ተግቸ
እስከመቸ ድረስ ሕይወቴ እንዲህ ደርቆ
እኖራለሁ ጌታ ልምላሜ አርጎ

የመሰበር ፍላጎቴ ግለቱ ሳይበርድ
ሰማዮችን ከፍተህ ምነው ብትወርድ
ምርኩዜን ፈትተህ እባክህ ስበረኝ
ትሁትና ታዛዥ መሆን አስተምረኝ

የራሴን ማንነት ያኔ በርግጥ እረዳለሁ
የውስጥ አይኔ በርቶ አብዝቸም አያለሁ
በፍጹም ግልጽነት ስምህን አውጃለሁ
በበረከት ሙላት አስከብርሃለሁ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке