መንፈሳዊ ረሃብ ክፍል 1

Описание к видео መንፈሳዊ ረሃብ ክፍል 1

“ረሃብ” የሚለውን ቃል ስንሰማ ከብዙ ሁኔታዎች ጋር ልናያይዘው እንችላለን፡፡ የተለያዩ አገራት ሕዝቦችም ስለ ረሃብ አንድ ዓይነት አመለካከትና ትርጉም አይኖራቸውም፡፡ ከተሜዎችና ገጠሬዎችም እንዲሁ። ሕጻን ይርበዋል፤ ያለቅሳል፤ ሲያለቅስ ይሰጠዋል፡፡ ዝም ይላል፡፡ አዋቂም ባያለቅስም በተወሰነ ጊዜ ምግቡን ካላገኘ ይራባል፡፡ ነገር ግን ከድርቅ ጋር የተያያዘው ረሃብ፣ ከተራው ረሃብ ይለያል፡፡ በድርቅ ምክንያት የሚመጣው ረሃብ፣ በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎችን ያስርባል፡፡ ቁርስ እየቀረ በምሳና በራት መዋል፡፡ ቀጥሎም ቁርስና ምሳ ወይም እራት እየቀረ በአንድ ምግብ መዋል፡፡ የአንድ እለት የምግብ መጠን እየቀነሰ መሄድና መታጣትን ያስከትላል፡፡ መንፈሳዊ ረሃብስ ምን ይመስላል? ያጠወልጋል ወይስ ምን ያደርጋል?

Комментарии

Информация по комментариям в разработке