የቲቶ መልእክት - ጤናማ ትምህርት ጤናማ ኑሮ (Titus – Healthy Teaching Healthy Conduct)

Описание к видео የቲቶ መልእክት - ጤናማ ትምህርት ጤናማ ኑሮ (Titus – Healthy Teaching Healthy Conduct)

የቲቶ መልእክት አጭር ቢሆንም አንድ አማኝ ሊያውቃቸው የሚገቡትን መሠረታዊ ነገሮች በውስጡ የያዘ ደብዳቤ ነው። የመልእክቱን ትኩረት ጤናማ ትምህርት ጤናማ ኑሮ በማለት መስቀመጥ ይቻላል። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ደብዳቤ የጻፈበት ምክንያት 1፡5 ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ቲቶ የተጀመረውን ጅምር ሥራ እንዲጨርስ እና በየከተማው ሽማግሌዎችን እንዲሾም ታዟል። በምእራፍ 1 መግቢያውን ተከትሎ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መሥፈርት እና በቀርጤስ የነበሩ የሐሰት መምህራን ባሕርያት ተዳሰዋል። በቀርጤስ የነበሩ ሰዎች እና የሐሰት መምህራን ሁኔታን ከገለጸ በኋላ በምእራፍ 2 ላይ ቲቶ ግን ጤናማ ትምህርት እንዲያስተምር ያሳስበዋል። ምእራፍ 2 አማኞች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸው በማሳሰብ ላይ ሲያተኩር ምእራፍ 3 ደግሞ አማኞች በማያምኑት መካከል እንዴት መመላለስ እንዳለባቸው ያስተምራል። ይህ ደብዳቤ ጤናማ ትምህርት ጤናማ ቤተ ክርስቲያን እና ማኅበረ ሰብ እንደሚፈጥር ያመለክታል። ይህቺን አጭር ቪድዮ በመመልከት የደብዳቤውን ትኩረት መገንዘብ ይቻላል።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке