ወቅታዊ ትምህርት ‘’ ሀገር የሌለው ሰው “ በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ። ሼር ሼር ዓለም በተዋህዶ ድምፅ ትጥለቀለቅ።

Описание к видео ወቅታዊ ትምህርት ‘’ ሀገር የሌለው ሰው “ በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ። ሼር ሼር ዓለም በተዋህዶ ድምፅ ትጥለቀለቅ።

የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ወቅታዊ ትምህርት ይደመጥ ይደመጥ ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ። ሼር ሼር ሼር ሼር ዓለም በተዋህዶ ድምፅ ትጥልቀለቅ። ላልሰሙት አሰሙ ላልነቁ አንቁ! መንፈሳዊነት ይብለጥ! የማዳመጥ ጊዜ ላይ ነን!!!


እጅግ በቁጥር የበዙ ሰዎች ስሜታቸው ከመለዋወጡ በፊት፤ ስሜታቸው እንዲለወጥ ከውስጥ የሚገፋ ኃይል እንዳለባቸው ልብ አይሉትም፡፡ ምክንያቱም፤ መናፍስቱ ከውስጥ ሆነው በኛ አሳብ ልክ ሲጣሉን፤ ራሳችንን በራሳችን የምናወራ እንጂ ከሌላ ባዕድ ፍጡር ጋር እየተዋጋን እንደሆነ አናስተውልም፡፡

ርኩስ መናፍስት የጥፋት አሳባቸውን ወደ ጥፋት ግብር ከመቀየራቸው በፊት ሁልጊዜ መቼት የሚባለውን "መቼ" እና "የት" የሚለውን የሥነ ጥበብ ሕግ ይጠቀሙታል፡፡ ይኸውም፤ መቼ የጥፋት አሳብ ማመንጨት፣ መቼ የጥፋት ግፊት መጨመር፣ መቼ የጥፋት ግብርን ማጽደቅ የሚል፤ ጊዜን ከውስጥ ወደ ውጪና ከውጪ ወደ ውስጥ የመጠበቅ ሂደት ይጓዙበታል፡፡ የት ብለው በሚጠብቁት የቦታ መምረጥ አሠራር ውስጥ፤ የት ሥፍራ ላይ ጥፋቱን እንደሚመሩ፣ የውስጥ ጫናውን እንደሚፈጥሩ፣ የግብር ሂደቱን እንደሚያስፈጽሙ እኛ ውስጥ ሆነው ያቅዳሉ፡፡ ምሳሌ ስንመለከት፤ በመንፈሳዊ ጥንካሬና መረዳት ውስጥ ባለንበት ሰዓትና ቦታ ላይ መናፍስት ዝም ይላሉ፡፡ ከጊዜያት ቆይታ በኋላም ወደ ሥጋዊ አኗኗርና ድክመት የምናዘነብልበት ጊዜና ቦታ ሲመጣ፤ ከውስጥ ሆነው የመጣላት እቅዳቸውን ከውጪ በመጣው አጋጣሚ አስታከው ለመፈጸም ይታገላሉ፡፡

አሁን አንዳንድ ሰዎች ትናንት ሰላም ብለናቸው ዛሬ ሰናገኛቸው ኩርፍ ብለውን ያልፋሉ፡፡ ትናንት ተሳስቀን፣ ተደስተን፣ ብዙ ቁም ነገር አውርተን፣ ለዛሬው ጊዜ እቅድ አውጥተን ሳለ፤ ዛሬ ስናገኛቸው ፍጹም ከትናንት ተቃራኒ ሆነው የሚያስደነግጡን ሰዎች አሉ፡፡ ይሄ ግለሰቦቹ ውስጥ ያሉት መናፍስት ሰውየውን ከውስጥ ወደ ውጪ ሲጣሉት፤ ይሄ የውስጥ ፍጭት ወደ ውጪ በተገለጠ ጊዜ፤ ግለሰቡ ለራሱ መለዋወጡ ሳያውቀው በሚተረማመስ አሳብ መካከል ዝብርቅርቅ ያለ ጠባይን ይገልጣል፡፡

በሌላውም ደግሞ፤ ከጊዜያት በኋላ ወደ ሕይወታችን የሚገቡ መናፍስት የጠባይ መዘባረቅ እንዲፈጠርብን ያደርጋሉ፡፡ አንድ ግለሰብ በቡዳ መንፈስ ቢያዝ፤ መንፈሱ የተዋረሰውን ግለሰብ የተነሣበትን ሰው(አዋራሹን) ጠባይ ሊያሲዘው ይችላል፡፡ ችኩል የነበረ ሰው በቡዳ ሲበላን፤ እኛም ካለተፈጥሮአችን ችኩል ለመሆን እንገደዳለን፡፡ ጠበኛና ደመኛ የሆነ ሰው የቡዳ መንፈስ ወደ ሕይወታችን ሲመጣ፤ ጥል የምንፈራና የምንሸሽ የነበርነው ሰዎች ተለውጠን አምቧ ጓሮ የምንፈጥርና ለጠብ የምንጋበዝ ሆነን ቁጭ እንላለን፡፡ የመተት መናፍስትም በተመሳሳይ፤ የመታቹንና የአስመታቹን ጠባይና ባሕሪይ ለተመታቹ ግለሰብ ስለሚያዋርሱት፤ መናፍስቱ የኛ የተፈጥሮ ጠባይ ባልሆነ ሁናቴ እንድንግለጽ ሊያስገድዱን ይችላሉ፡፡

" መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 12፥35)

Комментарии

Информация по комментариям в разработке