ሳይገድልህ በፊት ግደለው! || ኸሚስ ምሽት || ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሒም || Minber TV

Описание к видео ሳይገድልህ በፊት ግደለው! || ኸሚስ ምሽት || ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሒም || Minber TV

#صلوا_على_النبي #ሚንበር_ቲቪ #Minber_TV

ሳይገድልህ በፊት ግደለው!

“ኸሚስ ምሽት” በዒባዳ ከምንደምቅባችው ውድ ምሽቶች አንዱ በሆነው ለይለተል ጁምዓ በኢስቲግፋር፣በተውበት እና በሰለዋት አስውቦ፤ በቤተሰባዊ መንፈስ ቁምነገርን ከተዝናኖት ጋር አዋዝቶ፤ በጣፋጭ አንደበታቸው፣ በማይጠገብ ፈገግታቸው፣ በማይሰለች ምክሮቻቸው የነፍስ ስንቅን ከሚያቀብሉን መሻይኽ፣ ኡስታዞች እና ዱዓት ጋር አይረሴ ጊዜን የምናሳልፍበት የሚንበር ቲቪ ተወዳጅ እና ተናፋቂ ፕሮግራም ነው። የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጆች ሙሐመድ ፈረጅ እና ሑሴን ኸድር ከዘወትር የፕሮግራሙ እንግዶች ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሒም እና ኡስታዝ በድሩ ሑሴን ጋር እንዲሁም ከተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ጋር ጣፋጭ ቆይታን በማድረግ ምሽታችንን ያደምቁልናል። ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2፡30 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ እንዲከታተሉ ጋብዘንዎታል።


"ሥራ እንዴት ነው? እየበረታችሁ ነው?" ይህ በየዕለቱ ስንገናኝ የምለዋወጠው መደበኛ ጥያቄ ይሁን እንጂ ጉዳዩ "ዒባዳ እንዴት ነው"? ተብሎ እስከመጠያየቅ የሚያደርስ ደረጃ አለው በኢስላም! ሥራ መሥራት የዒባዳ ተግባራትን በመፈፀም የሚገኝን ምንዳ የማስገኘቱን ያህል፤ እየቻሉ አለመሥራት ደግሞ እጅግ በጣም የተወገዘ ድርጊት መሆኑን እስልምና ያስተምራል፡፡
ሸይኻችን በዛሬው ፕሮግራማቸው በሥራ ሰዓት መስጊድ የተገኙ ሶሃቦችን መልዕክተኛው (ሰ ዐ ወ) ስላወገዙበት አጋጣሚ እያወሱና ሥራ በኢስላም ስለተቸረው ታላቅ ክብር ቀደምት ነቢያትን በምሳሌ አስደግፈው የሚነግሩን አላቸው፡፡


እርስዎም በዚህ ፕሮግራም ላይ አስተያየት ካለዎት በአጭር መልዕክት መቀበያ ቁጥራችን በ9282 ላይ በመላክ ሊያደርሱን ይችላሉ፡፡

ይህን ፕሮግራም ከወደዱት ለሌሎችም በማጋራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ምንዳን ያግኙ!

0:00 - የመግቢያ ቆይታ
2:47 - ከድክመታችን አንዱ
3:48 - የሙሲባ ትንሽ የለውም
5:03 - ሥራ ዒባዳ ነው? በኢስላም የዕረፍት ቀን የሚባል ነገር የለም
6:50 - ሐጅ ላይ መነገድ የቻላል?
9:49 - ነብያትና የሥራ ዘርፎቻቸው
35:29 - ታላቁ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) እና ሥራ!
36:56 - ኢስላም እና የሥራ ፈጠራ
39:24 - ከሰላት ሰዓት ውጪ የሚሰግደው ሰሐባ
41:57 - በኢስላም ጡረታ የሚባል ነገር የለም
43:36 - ለመሆኑ ይህን ሰው ማነው የሚቀልበው?
45:22 - እስልምና እንዴት ተስፋፋ?
46:31 - ጊዜህን ለ4 ክፈለው
49:54 - ሳይገድልህ ግደለው
51:18 - የቱ ሥራ ይበልጥ የተወደደ ነው?
54:20 - በጠዋት ተነሱ
55:12 - እርዳታ የጠየቀው ሰሐባ
1:00:02 - የዱዓ ሰዓት

ይህን ፕሮግራም ከወደዱት ለሌሎችም በማጋራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ምንዳን ያግኙ!
ከዚህ በፊት ያለፉትን ክፍሎች ለመከታተል ይህን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ ፦    • ኸሚስ ምሽት | Khemis Mishit | A Special P...  

የሚንበር ቲቪን ይፋዊ ድረ ገጽን www.minbertv.com በመጎብኘት የተለያዩ ኢስላማዊ መረጃዎች ፤ መጽሐፎች እና ጥናታዊ ጽሁፎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
★★★★★
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ሊንኮች👇🏽 ይወዳጁን 👍🏽 ያጋሩ ⤴️
📍YouTube 👉    / @minbertv1  
📍Facebook👉   / minbertv  
📍Telegram👉 https://t.me/minbertv
📍TikTok 👉   / minber_tv  
📍Instagram 👉   / minbertv  
📍X / Twitter 👉   / minbertv  
📍Website 👉 https://www.minbertv.com

የሚንበር ቲቪ ስርጭት በኢትዮሳት ለመከታተል:–
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 30000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል

ሚንበር_ቲቪ
ሁለንተናዊ_ከፍታ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке