ዳዊት "እንደ ልቤ" የተባለበት ሚስጥር ምንድነው? ክፍል 3

Описание к видео ዳዊት "እንደ ልቤ" የተባለበት ሚስጥር ምንድነው? ክፍል 3

ክፍል 3
አስተማሪ፦ ፓስተር ኢያሱ ተስፋዬ, አማኑኤል ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በሞንትሪያል
መጋቢት 04 ፥ 2012 ዓ. ም. እ.አ.አ.

Part 3
Teacher: Pastor Eyasu Tesfaye, Ammanuel Montreal Evangelical Church
Mar 04, 2012

ዳዊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው በስፋት ከተጻፈላቸው የእስራኤል ነገስት መካከል አንዱ እና ቀዳሚ ሲሆን ህይወቱ በአመዛኙ በእምነት ምሳሌነት የሚጠቀስ የእግዚአብሔር ሰው ነው። ለዚህም ማስረጃው እግዚአብሔር ስለ ዳዊት "እንደ ልቤ" የሆነ ሰው ብሎ መስክሮለታል። ሆኖም ዳዊት በንግሥናው ዘመን ውስጥ በተለያዩ ድርጊቶች እግዚአብሔርን ሲያስቆጣ ደግሞም በንስሃ ከእግዚአብሔር ጋር ሲታረቅ ሲታይ እንደማንኛችንም ስጋ-ለበስ እንደሆነ ያስታውሰናል። ስለዚህም ዳዊት ህይወቱ ካጋጠሙት ነገሮች (በድሉም ሆነ በውድቀቱ) እኛ ብዙ ልንማራቸው የሚገባ ነጥቦች እንዳሉ ያመለክተናል። በተለይም ደግሞ እንደኛ ሰው የሆነውን ዳዊትን እግዚአብሔር "እንደ ልቤ" ያለበትን ምክኒያቶች በዚህ ተከታታይ ትምህርት ውስጥ እንመለከታለን።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке