Logo video2dn
  • Сохранить видео с ютуба
  • Категории
    • Музыка
    • Кино и Анимация
    • Автомобили
    • Животные
    • Спорт
    • Путешествия
    • Игры
    • Люди и Блоги
    • Юмор
    • Развлечения
    • Новости и Политика
    • Howto и Стиль
    • Diy своими руками
    • Образование
    • Наука и Технологии
    • Некоммерческие Организации
  • О сайте

Скачать или смотреть የሕዳር 12ሥንክሳር

  • kesisephrem
  • 2025-11-20
  • 10318
የሕዳር 12ሥንክሳር
  • ok logo

Скачать የሕዳር 12ሥንክሳር бесплатно в качестве 4к (2к / 1080p)

У нас вы можете скачать бесплатно የሕዳር 12ሥንክሳር или посмотреть видео с ютуба в максимальном доступном качестве.

Для скачивания выберите вариант из формы ниже:

  • Информация по загрузке:

Cкачать музыку የሕዳር 12ሥንክሳር бесплатно в формате MP3:

Если иконки загрузки не отобразились, ПОЖАЛУЙСТА, НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если у вас возникли трудности с загрузкой, пожалуйста, свяжитесь с нами по контактам, указанным в нижней части страницы.
Спасибо за использование сервиса video2dn.com

Описание к видео የሕዳር 12ሥንክሳር

ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር 12

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር አሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው ።

ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው ። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው ።

ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው ። የእግዚአብሔርየሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድርየከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ ።

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ ። ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋርበመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።

ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና

እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክየሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ ለዚህም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉት አጡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሔደ ።

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኰንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት ወደ ባለ በጎች ሒዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሒዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ግን መልአኩ ወደ ቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ ወደ ባለ ሥንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ ።

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው ። እጅግም አደነቀ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደ አደረገ ። የተራቡ ድኆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደየቤታቸው አሰናበታቸው ።

ከዚህም በኃላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው ። ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሠነጥቅ አዘዘው ። በሠነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናርበዓሣው ሆድ ተገኘ ። ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ

ለባለ ዓሣውና ለባለ ሥንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ ። በኋላኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል ።
እነርሱም ሲሰሙ ስለዚህ ነገር ደነገጡ ። እርሱም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸው ። ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ ። እነርሱም ሰገዱለት ተአምራቱም የማይቁጠር ብዙ ነው ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።

በዚችም ዕለት የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ነው በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

በዚችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ የጻድቁ በእደ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ።

በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ፊላታዎስ አረፈ ። በሹመቱ ወራትም የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደ ኖባ ንጉሥ ወደ ጊዮርጊስ እንዲህ ብሎ የመልእክት ደብዳቤ ጻፈ ወንድሜ ሆይከሊቀ ጳጳሳት ቆዝሞስ ጊዜ ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ጳጳስ ስለ ሌለን እኛ በታላቅ ችግር ውስጥ እንዳለን ዕወቅ ።

ይህም የሆነው ተንኰለኛው ሚናስ በተንኰልና በሐሰት ነገርየከበረ ጳጳሳችንን ጴጥሮስን ከሹመቱ ወንበር እንዲሰደድ ስለ አደረገው ነው ። ስለዚህ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት እስቲአልፉ ለሀገራችን ጳጳስ አልተላከልንም ።

አሁንም ስለ እግዚአብሔር ብለህ ስለ ቀናች ሃይማኖትም በድካም ከእኛ ጋር አንድ በመሆን ስለእኛ ወደ ግብጽ ሊቀ ጳጰሳት ወደ ቅዱስ ፊላታዎስ ጳጳስ ይልክልን ዘንድ ከራስህ ደብዳቤ እንድትጽፍለት እለምንሃለሁ የሚል ነበር ።

በዚያንም ጊዜ የኖባ ንጉሥ ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስን ይሾምላቸው ዘንድ የልመና ደብዳቤ ወደ አባ ፊላታዎስ ጻፈ

ይህ ቅዱስ ፊላታዎስም ልመናውን ተቀብሎ ከአስቄጥስ ገዳም ስሙ ዳንኤል የሚባል አንድ ጻድቅ መነኰስ አስመጣ እርሱን ጵጵስና ሹሞ ወደ ኢትዮጵያ አገር ላከው ወደ እነሱም በደረሰ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች በታላቅ ደስታ ተቀበሉት ። በዚህም አባት ፊላታዎስ ዘመን ብዙ ተአምራት ተገልጠዋል በሰላምም አረፈ ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ፊላታዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

ኅዳር ፲፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት

፪.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ

፫.ቅዱሳን ዱራታኦስና ቴዎብስታ

፬.አፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ

፭.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

፮.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ

፯.አባ ፊላታዎስ ሊቀ ዻዻሳት

ወርኀዊ በዓላት

፩.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ

፪.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ

፫.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ ሰማዕት

፬.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

፮.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ

፯.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ

በሰማይም ሰልፍ ሆነ ። ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ ። አልቻላቸውምም ። ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም ። ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ ። ራዕይ. ፲፪ ፥ 2


‪@እናታችንማርያምሆይእንወድ‬​ ‪@kesishenokweldemariam2240‬​ ‪@EfoyZeOrthodox‬

Комментарии

Информация по комментариям в разработке

Похожие видео

  • Ethiopia - “እጅ ስጡ” የትራምፕ የመጨረሻ ትዕዛዝ፣ የቀይባህር በር ተዘጋ፣ ኢራን ወደሁሉም አቅጣጫ ተኮሰች፣ ከአዲስ አበባ የወጣው መግለጫ
    Ethiopia - “እጅ ስጡ” የትራምፕ የመጨረሻ ትዕዛዝ፣ የቀይባህር በር ተዘጋ፣ ኢራን ወደሁሉም አቅጣጫ ተኮሰች፣ ከአዲስ አበባ የወጣው መግለጫ
    4 часа назад
  • #አነጋጋሪዋ_ሚስጥረስላሴ #ስሙር_አላምረው #ወሀቢያና_ኦርቶዶክሳውያን/ @VOEAtv @Tsegayekiflu @AbelBirhanu @NEGASHMEDIA
    #አነጋጋሪዋ_ሚስጥረስላሴ #ስሙር_አላምረው #ወሀቢያና_ኦርቶዶክሳውያን/ @VOEAtv @Tsegayekiflu @AbelBirhanu @NEGASHMEDIA
    3 дня назад
  • ጾም አርብዓን ቅድመ ምድላውን ናይ ኣሓት ኣብያተ ክስትያንን ምብራቅ ኦርቶዶክሳውያን እንታይ ይመስል?
    ጾም አርብዓን ቅድመ ምድላውን ናይ ኣሓት ኣብያተ ክስትያንን ምብራቅ ኦርቶዶክሳውያን እንታይ ይመስል?
    1 день назад
  • 🟠
    🟠"ወደ ንስሃ የሚመሩ የማለዳ ዝማሬዎች" #በመንበርከክ #ማነው_እንደኔ #የታል_አንተን_መፍራት #ፍቅር_ነህ #መበርቻዬ_ነህ_መጽናኛዬ #የእውነትን_መንገድ
    1 год назад
  • 7ተ ሰዓታት ጸሎት ኣብ መዓልቲ! ናይ ንግሆ ጸሎት New Eritrean tigrigina morning prayer ፡ ነሕዋትኩም ውን ስደዱሎም ብጸሎት ክባረኹ።
    7ተ ሰዓታት ጸሎት ኣብ መዓልቲ! ናይ ንግሆ ጸሎት New Eritrean tigrigina morning prayer ፡ ነሕዋትኩም ውን ስደዱሎም ብጸሎት ክባረኹ።
    3 года назад
  • ጾማችን በበገና እግዚያብሔርን በማመስገን ይሁን!!!
    ጾማችን በበገና እግዚያብሔርን በማመስገን ይሁን!!!
    4 дня назад
  • የየካቲት 21 ሥንክሳር#አባ ዘካርያስ#ቅዱስ አናሲሞስ#የፊሊሞና አገልጋይ አረፈ#አባ ገብርኤል ሁለቱ#ድንግል እመቤታችን
    የየካቲት 21 ሥንክሳር#አባ ዘካርያስ#ቅዱስ አናሲሞስ#የፊሊሞና አገልጋይ አረፈ#አባ ገብርኤል ሁለቱ#ድንግል እመቤታችን
    1 день назад
  • ⚡️ Гиперзвуковой удар по военным США || Армию призвали капитулировать
    ⚡️ Гиперзвуковой удар по военным США || Армию призвали капитулировать
    7 часов назад
  • የእስራኤል አሜሪካ ጥቃትና የኢራን መሪዎች ዕጣፈንታ ፣የመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚሳይል ተመቱ
    የእስራኤል አሜሪካ ጥቃትና የኢራን መሪዎች ዕጣፈንታ ፣የመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚሳይል ተመቱ
    4 часа назад
  • Lidetu Ayalew ልደቱ አያሌው || ‟የህዝቦች ትብብር አስፈላጊነት
    Lidetu Ayalew ልደቱ አያሌው || ‟የህዝቦች ትብብር አስፈላጊነት" || ኢትዮጵያን ለማዳን || ወቅታዊ ጉዳዮች"!!
    3 часа назад
  • Начало большой войны / Ликвидация главнокомандующего армией
    Начало большой войны / Ликвидация главнокомандующего армией
    6 часов назад
  • ተስፋ🙏 ተስፋ አትቁረጡ! እጅግ ድንቅ ትምህርት በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን #Orthodox #tewahedo #ተስፋ #Tesfa #Hope #አባገብረኪዳን
    ተስፋ🙏 ተስፋ አትቁረጡ! እጅግ ድንቅ ትምህርት በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን #Orthodox #tewahedo #ተስፋ #Tesfa #Hope #አባገብረኪዳን
    7 месяцев назад
  • 🔴 СРОЧНО МЕСТЬ ИРАНА: УДАРЫ ПО ДУБАЮ, КУВЕЙТУ, БАХРЕЙНУ #новости #одиндень
    🔴 СРОЧНО МЕСТЬ ИРАНА: УДАРЫ ПО ДУБАЮ, КУВЕЙТУ, БАХРЕЙНУ #новости #одиндень
    4 часа назад
  • የአለም ማብቂያ ደውል በኢራን ተደወለ ፈጣሪ የቤት ሰራተኞችን ይጠብቅ 😂😜😂
    የአለም ማብቂያ ደውል በኢራን ተደወለ ፈጣሪ የቤት ሰራተኞችን ይጠብቅ 😂😜😂
    54 минуты назад
  • #ልደታ#ባታ#ማርያም#ድንግል#habesha#ፋሲካ#ስቅለት#orthodox#tewahdomezmur#dingle#mary#mezmur#እመቤታችን#eotc#saintmary
    #ልደታ#ባታ#ማርያም#ድንግል#habesha#ፋሲካ#ስቅለት#orthodox#tewahdomezmur#dingle#mary#mezmur#እመቤታችን#eotc#saintmary
    5 месяцев назад
  • ነቢይ አያስፈልግህም፤ የተከፈተ አይን ለአገልግሎት፤መንፈስ ቅዱስ Unlocking Your Spiritual Vision:
    ነቢይ አያስፈልግህም፤ የተከፈተ አይን ለአገልግሎት፤መንፈስ ቅዱስ Unlocking Your Spiritual Vision:
    3 часа назад
  • Украинский фронт - трагедия в Иране. Трамп получил быстрый ответ. 28.02.26 Саня во Флориде
    Украинский фронт - трагедия в Иране. Трамп получил быстрый ответ. 28.02.26 Саня во Флориде
    3 часа назад
  • 5 фактов о советском Шерлоке, которые свели американца с ума
    5 фактов о советском Шерлоке, которые свели американца с ума
    3 дня назад
  • ⛔ ቅዱስ ሚካኤል ማን ነው ? 🤔 የ ሚካኤል ታሪክ / የ ህዳር 12 አመታዊ ክብረ በዓል / የ አባ ገብረ ኪዳን ስብከት 🙏 ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
    ⛔ ቅዱስ ሚካኤል ማን ነው ? 🤔 የ ሚካኤል ታሪክ / የ ህዳር 12 አመታዊ ክብረ በዓል / የ አባ ገብረ ኪዳን ስብከት 🙏 ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
    3 месяца назад
  • РЕЖИМ ТРЕЩИТ ПО ШВАМ | ГЛАВАРИ ИРАНА ЛИКВИДИРОВАНЫ | МОЩНЫЕ УДАРЫ ПО ИРАНУ
    РЕЖИМ ТРЕЩИТ ПО ШВАМ | ГЛАВАРИ ИРАНА ЛИКВИДИРОВАНЫ | МОЩНЫЕ УДАРЫ ПО ИРАНУ
    3 часа назад
  • О нас
  • Контакты
  • Отказ от ответственности - Disclaimer
  • Условия использования сайта - TOS
  • Политика конфиденциальности

video2dn Copyright © 2023 - 2025

Контакты для правообладателей video2contact@gmail.com