በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ብቻ ናቸው | Ethiopia | Berhanu Nega| 12th grade eaxam

Описание к видео በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ብቻ ናቸው | Ethiopia | Berhanu Nega| 12th grade eaxam

የዘንድሮውን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 674,823 ተፈታኞች ውስጥ፤ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያስመዘገቡት ተማሪዎች 5.4 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ተማሪዎችን ካስፈተኑ ትምህርቶች ቤቶች መካከል 1,363 የሚሆኑት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን የገለጸው የዚህን አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት፤ ዛሬ ሰኞ ጷጉሜ 4፤ 2016 ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ የተደረገውን ይህን ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ፤ ስምንት በመቶ ያህል የሚሆኑት በይነ መረብን ተጠቅመው የተፈተኑ ናቸው።

የዘንድሮውን ሀገር አቀፍ ፈተናውን ለመውሰድ ከተቀመጡት ተማሪዋች መካከል፤ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ነው። ከተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ፈተናውን ከወሰዱ 321,536 ተማሪዎች መካከል፤ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡት 9 በመቶው መሆናቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ዝርዝሩን በጹሁፍ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/14151/
---------------------------------------------------------------------------------
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ http://ethiopiainsider.com​
ፌስቡክ ፦   / ethiopiainsider  
ትዊተር (ኤክስ) ፦   / ethiopiainsider  
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaInsiderNews
ቲክቶክ፦   / ethiopiainsider  

Комментарии

Информация по комментариям в разработке