አዲስቅኝት ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከባህረ ሐሳብ መምህሩ ሄኖክ ያረድ ፈንታ ጋር!እንኳን ለመስቀለ ብርሃኑ አደረሳችሁ እንላለን ከወዲሁ!

Описание к видео አዲስቅኝት ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከባህረ ሐሳብ መምህሩ ሄኖክ ያረድ ፈንታ ጋር!እንኳን ለመስቀለ ብርሃኑ አደረሳችሁ እንላለን ከወዲሁ!

https://addisperspective.com/category...

  / newperspectiveethio  

የኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ ነሐሴ 25 ላይ የሚያስገባው ወቅት የለውም፡፡ ይልቅ ነሐሴ 28 ቀን የሚገባ ንዑስ ክፍለ ጊዜ እንዳለ ከባሕረ ሐሳብ ጓዳ፣ ከግጻዌው መድበል ቢገባ በዘመነ አክሱም በ6ኛው ምዕት የነበረው ቅዱስ ያሬድ የሰጠውን ስያሜ ማግኘት ይቻላል፡፡
የአለቃ ያሬድ ፈንታ ወልደዮሐንስ በአራቱ ወቅቶች ላይ የተመሠረተው ‹‹መጽሐፈ ግጻዌ ሐዲስ ዘተሰናአወ በአርባዕቱ ክፍላተ አዝማን›› መጽሐፋቸው እንደገለጹልን፡- ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜን 5/6 ጎህ፣ ነግህ፣ ጽባሕ፣ ብርሃንና መዓልት ይባላል፡፡
ረዳት ፕሮፌሰሩ የሚያስተምሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በክረምት የሚሰጡትን/ የሚያሰተምሩትን ‹‹የሰመር ኮርስ›› እያሉ መጥራታቸው ሁሌም ምን ነው ‹‹ሰው የለም ወይ›› የሚያሰኝ ነው፡፡ ቅልጥ ባለው ክረምት የበጋ ብሎ መጥራት የሚያበቃውስ መቼ ይሆን!? ቀደምት ሊቃውንት ‹‹በኛ ክረምት በነሱ በጋ›› ሲሉ ነው የኖሩት፣ የጻፉትም፡፡
የዘመን አቆጣጠሯ መነሻና መድረሻ የወቅት አከፋፈልና ስያሜ ተጠንቅቆ አለመያዙና በቅጡ አለመተላለፉ ከላይ የተጠቀሰው መንደርደርያ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

Комментарии

Информация по комментариям в разработке