ፉዓድ ሸምሱ|| ሠላሜ |አዲስ| መንዙማ 2016||Fuad Shemsu||Selame ||New Menzuma2023

Описание к видео ፉዓድ ሸምሱ|| ሠላሜ |አዲስ| መንዙማ 2016||Fuad Shemsu||Selame ||New Menzuma2023

ማዲህ ፉአድ ሸምሱ
ግጥም ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ
ዜማ :ሙአዝ ሀቢብ
ተጨማሪ ዜማ :ኸይራቶች
ስቱዲዮ: ኑሩ ኡመር [ቦርከና]
ሚክሲንግ:ሶል( ሀመር)
ካሜራ  :ሰዒድ ሙሐመድ
ምስል ቅንብር  :ሰዒድ ሙሐመድ
ሌሪክስ ኤዲቲንግ : አሊ ሙሐመድ (Alif)
ግራፊክስ አድናን አማን
ኘሮዳክሽን ማናጀር :ፋሩቅ ጋሊብ
ኘሮዲዉሰር  :አል-ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን

💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

ሙሉ ግጥም
ሰላሜ
።።።።።።።

ኻሊቁ፣ ጀማል ጀላላን ጠቅልሎት ለሱ
ደፍቶለት፣ የኑሩን ዙፋን ዘውዱን ከራሱ
ላንዴ አይታው፣ ትዋልላለች የማንም ነፍሱ
     አንተዬ እንደሱ፣ አንድ የለም ሚወደዲ
።።።።።።።።

ያንቱ ፊት፣ ጨለማን ገፎ ኑሩ ሲደንቀን
ምን ይባል፣ ፀሃይዋን ንቆ ሲያበራ በቀን
ቅኔውም፣ ተደበቀብን ሰም ወርቁ ራቀን፣
ወይ ገሎ አይለቀን፣ እንደነ አህመደል ሃዲ
።።።።።

ፀጉሩማ፣ ሲገርመን ወዙ መርገፍ ሳይቃጣው
አጀባው፣ ጠቁሮ ማብራትን ከዬት አመጣው
  ወስዶብን፣ ይሄው ልባችን እኛም ስናጣው
ጉድ አርጎ አመጣው፣ ለጉድ እስኪሆን ጉዲ
።።።።

መሀባው፣ ወይ አይለመድ ወይ አልቀለለ
እንዳሻው፣ ስንቱን አነሳው ስንት እየጣለ
ወርውሮ ፣ውዱ የሳተው እስኪ ማን አለ
    ልቡ ያልዛለ፣ ሲጠሩ ሙሐመዲ
።።።

ሙሐመድ፣ እንኳን መታከት መች ይጠገባል
ጆሮዬ፣ በሰማ ቁጥር ሙሐመድ ሲባል
ሙሐመድ፣ እየናፈቁኝ ሆዴ ይባባል
     ድኗል እንዲባል፣ በሉ እስኪ ሙሐመዲ
።።
    
   ወለላው፣ ያይኔ ማረፊያ ኗሪው በነፍሴ
   ጀማላው፣ ካለርሱ አይሰራም ጅስሜም ህዋሴ
ስሙ ነው፣ ሳዝን መደሻ፣ ስታረዝ ልብሴ
      ስሙ ነው ዋሴ፣ የኔ ወገን ዘመዲ
    ።።።።

ካበሻ፣ የሸውቁን ገመድ ጦይባ ቀጥሎ
እንደ ሰው፣ ጨርቅ ቢለብስም ልቡን ግን ጥሎ
ለይምሰል፣ ፈገግ የሚለው ውስጡ ተቃጥሎ
   ላዩ ሰው መስሎ፣ ሲስቅ ሲቀልዲ
።።።።

በኔ ላይ፣ ምነው ጠና ባሰሳ ነገሩ
ምንድን ነው፣ ልቤ ተሻግሮ ጦይባ ማደሩ
እንዲህ ነው ለካ ትልቅ ሰው መውደድ ማፍቀሩ
    ርቆኝ አገሩ፣ ሸውቁ ሲሰራኝ ጉዲ
   ።።።።።።።።
    
መልበሴ፣ ነው ያስመሰለኝ እንጂ ደህና ሰው
ሳቄ እንጂ፣ መች ታዬ አይኔ ናፍቆ ሚያለቅሰው 
ማን አይቶ፣ ጀማሉ ውስጤን እንደሚያምሰው
ማልገልጠው ለሰው፣  ስንት አለ በኔ ሆዲ
    ።።።።።

ሳታገኝ፣ ሳይደርስህ ገና ያይኑ በረከት
አንድም ቀን ፣ጀንበሩን ፊቱን ሳትመለከት
መሳቅህ፣ ምንድን ከቶ ያንተ መንከትከት
    እስኪ ተመልከት፣ ያን ናፋቂውን ግንዲ   
።።።


በልቤ ቀበሌ አምባ፣ ተቸምችሞ ሙሀባ
ሌላማ እንዳያስገባ፣ ሞልቶታል ሙከረሙ
።።

መውደዱ አድሮ እያከለ፣ መቋቋሙን ያልቻለ   
ሀበሻ ላይ ስንት አለ፣ የጠናበት መድከሙ
።።።።።
  
ካንቱ ወዲያ ሙሉነት፣ ካንቱማ ወዲያ ረህመት
ቢጤውም ሆኗል ዘበት፣ ላይገኝ ከአለሙ

በደም ተንክሮ ልብሱ ፣ተሸርፎም ውቡ ጥርሱ
ማርልኝ ሚል ምላሱ፣ ሌላው ሲል ተራገሙ 
።።።።

ማን ይሆን ውቡን ጥርሶን፣ የመታው የሸረፈው
  የኔውን ባራገፈው፣ አንቱ ደህና ሁነሁ
  ።።።

ስቃዮትን ልሰቃይ፣ ቅጣቶንም ልቀጣው
ላንቱ ስል ሁሉን ልጣው፣ ሾክ እንኳን አይንካሁ
።።።።።

።።።።  
ልቅናን በጠቅላላ፣ ለሱ አድርጎለት መውላ
ወዶ ለጠራው ሁላ፣ መሻሪያ ሆኗል ስሙ 
።።።።

አብዱሏህ ወዳጃቸው፣ ተሳሰረና እግራቸው
መነሳት ተሳናቸው፣ ደርሶ ድንገት ታመሙ
   
እስኪ እንደው ቢያስታግሰው ፣ዓፊያህን ቢመልሰው    
አንተ ምትወደውን ሰው፣ ጥራ አሏቸው በስሙ

ከንብረት ከህይወትም፣ ከናት በላይ ካባትም
አብልጠው ሚወዱት፣ መች አለ እንደ ኢማሙ

  ሲወዱም ነው ሙሐመድ፣ ሲናፍቁም በሙሐመድ
  ሙሐመድ ነው ሙሐመድ ፣ቢድኑም ቢታመሙ

አብዱሏህ ወዳጃቸው፣ አሏህ እንዲያሽራቸው
ሙሐመድ ቢል አፋቸው፣ ከወዲያው ድነው ቆሙ
።።።።

የኒዕማዎች አይነታ፣ ወደር የለሽ ስጦታ
  አንቱ ኖት የኔ ፈንታ፣ ዙል ኹሉቂን ዓዚሙ
  
ትልቅ ሰው ተሰጥቼ፣ ትልቅ ሰው ተጠግቼ
ምን ጎሎኝ ምን አጥቼ፣ ወደ ሌላ ማዝገሙ

ኑሮው ሲተናነቀኝ፣ ደስታ ሳቄም ቢርቀኝ፣
ሙሐመድ ስል ለቀቀኝ፣ ሀዘን ጭንቁ ህመሙ
።።።።።።

   ልቤን ከጉድ ያዳነው፣ ጉድለቴን የከደነው    
ቀና ያልኩት ባንቱ ነው፣ ሊጥሉኝ ሲሸከሙ
።።።
      
ምን ባጣ ብቸገርም፣ ዱንያው ሁላ ቢቀርም
ባንቱ አልደራደርም፣ ክብሬ ኖት ሙከረሙ  
።።።
      
የተናቀው መላቁ፣ የጠፋው ለመድመቁ
   ያዘነው ለመሳቁ፣ ሰም ወርቁ ሙከረሙ
።።።።

በልቤ ውስጥ ያለው፣ መግለፅ የማልችለው
ከምፅፈው በላይ፣ ሚበልጠው እሱ ነው

  አንቱ ተናፋቂው፣ ተወዳጁም አንቱ
አንቱን እየያዘ፣ ባንቱ አማረ ስንቱ

ሙሐመድ ልበለው፣ በማታም በጧቱ
እንደስሙ ሚጣፍጥ፣ አትሰራም ንቢቱ

   ሌላውን ረስቶ፣ ሁሉን ችላ ብሎ
ሙሐመድ ሲል ያድራል፣ ሙሐመድ ሲል ውሎ
  
ስፈታ እንዳልኖርኩኝ፣ ስንቱን ወርቅ ቅኔ
  ቅኔ ናፍቆትሁ ግን፣ አቅቶኛል ለኔ

የሚያመልጠው የለው፣ አይርቁም አይሸሹ
እሱ ዳኛ ፈራጅ፣ እሱው ነው ከሳሹ
  
ናፍቆቱ ሃይሎ፣ እንዳላሳመመኝ
አጀብ ግን እሱው ነው፣ ሊያድን የሚያክመኝ
   
     ፍቅሩ እያበረደው፣ ናፍቆትሁ ሲፈጀው
  አንቱዬ ምን ይሁን፣ ልቤ ምን ይበጀው 

በሸውቁ መንምኖ፣ ጅስሙ እንደ ጨርቅ አልቆ
ላዩን ደህና መሳይ፣ ውስጥ ውስጡን ማቅቆ 
  አትፍረዱ በሱ፣ ቢገኝ መሬት ወድቆ
  ማን ሲድን አይተሃል፣ ትልቁን ሰው ናፍቆ

አልሰማህም ሸውቁ፣ የሰራውን ስራ
እንኳን ስጋ ለባሽ፣ አርገፍግፏል ጎራ

እሩህ የሌለውን፣ ግንዱን ሲያስለቅሰው
  እኛ ሩህን ይዘን፣ ወዴት እንድረሰው

  ስቃዩ አሳዝኖሁ፣ ብታቅፉት እኮ ነው
ህመሙ አባርቶለት፣ ግንዱ የሰከነው

ጠንቶ ሲያስለቅሰኝ፣ ሸውቁ ሲያዋልለኝ
    ያላንቱ ሰይዲ፣ ማን አይዞህ ይበለኝ
   ።።።።።
  
ልቡ አንቱን ናፍቆ፣ መሀባው ሲረታው
  አዝነሁ ካልደረሱ፣ ላይድን ነው በሽታው
።።።

ለኔም ኑልኝ እንጂ ፣ማዬቱ ይድረሰኝ 
እንደዚያች ጨረቃ፣ ናፍቆትሁ ሳይገምሰኝ

ዱንያው ጥንቅር ይበል፣ ይቅርብኝ ወረቱ
ሙሉ አርጎ ያኖራል፣ ያንቱን ፊት ማየቱ 

የሚቻል አይደለም፣ አውቃለሁ ውበቱን
   ያየ ያላየውን፣ ልብ መቀማቱን

አብረው የኖሩትም፣ ችለው መች ደንድነው
   እንደኔ ያላዬው፣ ምን ይሆን ሚያድነው

ግን ታሞ ከመኖር፣ ናፍቆ አይንሁን አይኔ
  አንዴም አይቶ መሞት፣ ይሻለኛል ለኔ

እስከ መች በሩቁ፣ ልንገብገብ ልሰቃይ
ልውደቅ አጠገብሁ፣ መታመሙ ይብቃኝ
ማንነት ሲረክስ፣ ጅህልናው ደንፍቶ
    መብቷ አፈር ሲገባ፣ ሴትነቷ ጠፍቶ

አዛኝ ረህመት አርጎ፣ ጀሊሉ ቢያስገኘው
አንተው ሙሐመድ ነው፣ ሰውን ሰው ያሰኘው
 
አንድ ነው መንገዱ፣ መድረሻው ሰንሰሉ
እሱም ሙሐመድ ነው፣ ሙሐመድን ላሉ 
ካለኛው ሙስጦፋ፣  ካለኛው ሙሐመድ
ሄዱት ሄዱት እንጂ፣ ዝግ ነው ሌላው መንገድ

ንቅንቅ የለም ካንቱ፣ ያቁረተል ዓይኔ
  የሙሐመድ መባል፣ ይበቃኝል ለኔ
  
ከተውኩማ ስሙን፣ ልገኝ አይደል ሞቼ
ዛዲያ ማንን ልጥራ፣ ሙሐመድን ትቼ
  
  ከሰይደል ውጁድ፣ ከሙሐመድ በቀር
ታዲያ ምን ሊወደድ፣ ከቶ ምን ሊፈቀር
  
እንዲያው ትንግርት ነው፣ ልቤ አይችልም ከቶ
ስሙን ትቶ ሃያት፣ መኖር መድሁን ትቶ 
  
የጨቅላ ልጅ ጠረን፣  ያንገቱ ስር ሽታ
   የወላጅን ስቃይ፣ ይነቅለዋል ባፍታ
      
እንኳን በሙሐመድ፣ ባወደሰው ጌታው
እናቱን ያገኘም፣ ይድናል በሽታው 

እንኳን ሙሐመድን፣ የሚያምሩት ነብዬ
ስንቱ ጤና ሆኗል፣ እናቱን እንዳዬ
ስንቱ ቁስሉ ሽሯል፣ ወዳጁን ስላዬ
።።።።።።።።

✍ግጥም ዑስታዝ ሰዒድ አህመድ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке