🔴 NEW || ለራሳችሁ ቤት ስሩ || ድንቅ ስብከት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan sibket

Описание к видео 🔴 NEW || ለራሳችሁ ቤት ስሩ || ድንቅ ስብከት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan sibket

ዘፍጥረት 30
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፥ እግዚአብሔርም ተለመናት፥ ማኅፀንዋንም ከፈተላት፤
²³ ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ አለች፤
²⁴ ስሙንም፦ እግዚአብሔር ሁለተኛ ወንድ ልጅን ይጨምርልኝ ስትል ዮሴፍ ብላ ጠራችው።
²⁵ ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።
²⁶ ስለ እነርሱ የተገዛሁላቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ የተገዛሁልህን መገዛት ታውቃለህና።
²⁷ ላባም፦ በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና አለው።
²⁸ ደመወዝህን ንገረኝ፥ እርሱንም እሰጥሃለሁ አለ።
²⁹ እርሱም አለው፦ እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ።
³⁰ ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፤ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፤ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?
³¹ እርሱም፦ የምሰጥህ ምንድር ነው? አለ። ያዕቆብም አለው፦ ምንም አትስጠኝ፤ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደ ገና በጎችህን አበላለሁ እጠብቃለሁም።
³² ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር ያለበቱን እለያለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።
³³ ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደ ፊት ጻድቅነቴ ይመሰክርልኛል፤ ከፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ የሌለበት ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቆጠርብኝ።
³⁴ ላባም፦ እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን አለ።
³⁵ በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።
³⁶ በእርሱና በያዕቆብ መካከልም የሦስት ቀን መንገድ ያህል አራቃቸው ያዕቆብም የቀሩትን የላባን በጎች ይጠብቅ ነበር።
³⁷ ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው።
³⁸ የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎቹ ፊት አኖራቸው፤ በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይጎመጁ ነበር።
³⁹ በጎቹም በትሮቹን አይተው ከመጎምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ፤ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጕርጕር ነቍጣም ያለበቱን ወለዱ።
⁴⁰ ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ፤ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም።
⁴¹ እንዲህም ሆነ፤ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፤
⁴² በደከሙ በጎችም ፊት በትሩን አያደርገውም ነበር፤ የደከሙትም ለላባ፥ የበረቱትም ለያዕቆብ ሆኑ።
⁴³ ያ ሰውም እጅግ ባለ ጠጋ ሆነ፤ ብዙም ከብት ሴቶችም ወንዶችም ባሪያዎች ግመሎችም አህዮችም ሆኑለት።
✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁላችንም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ። በጸሎትም ያስቡን +++ Subscribe ያድርጉን +++ Share ያድርጉ +++
#aba_gebrekidan_girma
#አባ_ገብረኪዳን_ግርማ
#aba_gebrekidan
#አባ_ገብረኪዳን_ስብከት
#orthodox_tewahdo
#Aba_Gebrekidan_Interview
#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳን_ግርማ
#ርዕሰ_ሊቃውንት
#ኦርቶዶክስ
#ተዋህዶ
#orthodox
#tewahdo

Комментарии

Информация по комментариям в разработке