ዘማሪት ትርሀስ ገ/እግዚአብሔር - ወደኋላ አልልም | Zemarit Tirhas G/Egziabher - Weduhala Alilm

Описание к видео ዘማሪት ትርሀስ ገ/እግዚአብሔር - ወደኋላ አልልም | Zemarit Tirhas G/Egziabher - Weduhala Alilm

ኢዮራም ቲዩብ የተለያዩ መዝሙሮችን እና ትምህርቶች የሚገኙበት ቻናል ሲሆን ለወደፈት የምንለቃቸው ቪዲዮዎች እንዲደርሳችሁ Subscribe ቀጥሎም የደውል ምልክቷን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

This is Eyoram Tube Youtube channel , here You will find many Christian Songs and Teaching Videos. To keep in touch with us please subscribe and don't also forget to tap Bell button.

If you want to contact channel owner: Phone No: +251941067481 Telegram: t.me/akuna444
#zemari #zemarit #tirhas #gebreegziabher #mezmur #ethiopianorthodox #christian #ትርሀስ #ገብረ #እግዚአብሔር

ወደ ኃላ አልልም

ወደ ኃላ አልልም ከእንግዲህ
ስላየውህ ፊቴ ተስለህ
ከተገለጥክልኝ ህያው ተድላ
አልሻም በጭራሽ ከአንተ ሌላ

ከሰለሞንስ የሚበልጠው
የክብር ጌታ ከኔ ጋር ነው
ሁሉን ሚያስተው ሁሉን ሚያስንቅ
አለ በልቤ የእግዚአብሔር ጽድቅ
የማልሸቅጥብህ ንውት ጌታ
የማልደርብብህ ንፁህ በፍታ
በሰው ፊት ለሆንከኝ ሞገስ ግርማ
እሰዋልሃለው የአፌን ዜማ

ለሚያልፍ መብል አልተከትልኩት
ታዓምር አይቼ መድህን አላልኩት
ማቄን እስክቀድ እንዲህ መሆኔ
ፍቅሩ ገብቶኝ ነው የሆነው ለኔ
ከፈርዖን ሽንኩርት ዓሳ ይልቅ
አንተን በመምረጤ ብጣል ብናቅ
ዉዴ መገኘትህ እስካለኝ
የዚህ ዓለም ወጅብ አይደንቀኝ

አንተን ያሉትን በፀሎት ስከስ
መች ጠፀየፍከኝ በእንባ ስመለስ
ደማስቆ ሳልደርስ ደርሰህልኝ
የፅድቅህን ጦር አስጣተከኝ
መከራ ቢመጣ እስራት
ተሰናድቻለው እስከሞት
መነቀፍ በስሙ መሰደቤ
ሊለየኝ አይችልም ከወደቤ

ባይቀበሉኝ ቢበዛ ከልካይ
እጠብቃለው የነገን ጸሐይ
ከእንግዲህማ የለም ዝምታ
ሕይወት በዝቶልኝ በሞተው ጌታ
መዝሙሬ ቢመርም ለሚጠፉት
የሕይወት ሽታ ለሚድኑት
ጠላትን ሚያሸብር የድል ቅኔ
ገና ነው ይሰማል በዘመኔ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке