ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ | TPLF| Tigray| Debretsion| ethiopiainsider

Описание к видео ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ | TPLF| Tigray| Debretsion| ethiopiainsider

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት "የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል" ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ። አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን "አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም” ብለዋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡበት እና ከትላንት በስቲያ ሰኞ የተጠናቀቀው የህወሓት 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ እውቅና አልተሰጠውም። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 14 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም አልተሳተፉም።

ዶ/ር ደብረጽዮን ሊቀመንበር ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ከ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር “ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም” ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር "የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው" ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን፤ በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን "ካቋቋሙ ወገኖች ጋር ውይይት ያስፈልጋል” ብለዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግራይ ሠራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።

በጉዳዩ ላይ ከፌደራል መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ዶ/ር ደብረጽዮን፤ "እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" አስረድተዋል።
-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ http://ethiopiainsider.com​
ፌስቡክ ፦   / ethiopiainsider  
ትዊተር (ኤክስ) ፦   / ethiopiainsider  
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaInsiderNews
ቲክቶክ፦   / ethiopiainsider  

Комментарии

Информация по комментариям в разработке