በገናችንን እንዴት እንንከባከብ

Описание к видео በገናችንን እንዴት እንንከባከብ

⚜የዜማ(መዝሙር) አጀማመር - በሐዲስ ኪዳን⚜

👉በጌታችን ልደት ለመጀመርያ ጊዜ ሰውና መላእክት አንድ ላይ ሆነው ዘምረዋል ።ሉቃ ፪÷፲፬
👉የኢየሩሳሌም ሕፃናትና አረጋውያን ለጌታችን ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት እያሉ ዘምረውለታል፡፡
👉ሐዋርያት ምስጢረ ቁርባንን ከተቀበሉ በኋላ ዘምረዋል፡፡ ማቴ ፳፮÷፴
👉በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔም እርስ በእርሳችሁ ተነጋገሩ እንዳለ ቆላ.፫÷፲፮
ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ በፍልጵስዩስ ወኅኒ በጸሎትና በዜማ ያመሰግኑ ነበር፡፡ ዝማሬያቸዉም የወኅኒ ቤቱን ደጆች አስከፍቷል እነሱንም ከእስራት አስፈትቷል፡፡ የሐዋ ሥራ.፲፮÷፲፱-፳፮

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

⚜መንፈሳዊ ዜማ(መዝሙር) በኢትዮጵያ⚜

#ቅድመ_ኦሪት
🙏ኦሪት ገና ወደ ኢትዮጽያ ከመግባቱ በፊት ስብሐተ እግዚአብሔር ፤ አምልኮተ እግዚአብሔርና ፈሪሃ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ አብሮ ነበር ፡፡ ከዚህ ሁኔታ በመነሳት ከሕገ ኦሪት መምጣት በፊት በኢትዮጵያ ዜማ ነበር ማለት ይቻላል ፡፡

#ጊዜ_ኦሪት
በቀዳማዊ ሚኒልክ ዘመን በሊቀ ካህናቱ በዘካሪያስ እጅ ታቦተ ጽዮንና ሌዋዉያን ሲመጡ የመዝሙር መጻሕፍትና በተመሳሳይ የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ አብረዉ መጥተዋል ፡፡ በዘመነ ኦሪት የመጡ የዜማ መሳሪያዎች ፤ አለባባስና የመዝሙር አጠቃቃም ስልቶች ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን እየተገለገለችበት ትገኛለች ፡፡ ለምሳሌ ከዜማ መሳሪያዎች መካከል ከበሮ ፤ ጸናጽል ፤ መለከት ፤ መሰንቆ ፤ በገና ይገኙበታል ፡፡ ከአለባበስም ረጅም ቀሚስ ፤ ጥምጥም ፤ መጎናጸፊያ (ጋቢ ) እና ካባ ይገኙበታል ፡፡

🙏🙏🙏ቅድመ ቅዱስ ያሬድ🙏🙏🙏

👉“ወበዉዕቱ መዋዕል አልቦ ማኅሌተ ቅኔ በልዑል ዜማ ዘእንበለ ለሆሣሥ” ይላል። ግንቦት ፲፩ ስንክሳር
➡️ትርጉሙም በቀስታ ፤ በዝግታ ነዉ እንጂ ድምጽን ከፍ አድርጎ በመናገር ፤ ጉሮሮ በማሳመር ፤ ቃልን በማራቀቅ ወይም በማጉላት ፤ ለቃላት ቀለም በመስጠት ፤ የሚጮህ ዜማ አልነበረም ማለት ነዉ ፡፡
👉አንድም "ወበዉዕቱ መዋዕል አልቦ ማኅሌተ መዝሙር ዘከመ ይእዜ በልዑል ቃል ዘእንበለ በትሑት ቃል።"
➡️ትርጉሙም በዚያ ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ ማለት ነው።

🙏🙏🙏የቅዱስ ያሬድ መመረጥ🙏🙏🙏

እግዚአብሔር ቀደም ሲል በመዝሙረ ዳዊት ፸፯ ÷ ፳፭ “የመላእክትንም እንጀራ የሰዉ ልጆች በሉ”የተባለዉና በመዝ ፸፫ ÷፲፬ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸዉን ሰጠሃቸዉ፡፡ በማለት በልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንዲመሰክር ያደረገዉን ኢትዮጵያዉያን የመላእክት እንጀራ የተባለዉን ምስጋና በመላእክት ምስጋና በማመስገን ከመላእክት ጋር እንዲተባበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖትና አምልኮተ እግዚአብሔር በልዩ የመላእክት ጣዕመ ዜማ እንዲታጀብ ፈቃዱ በመሆኑ ከአክሱም ጽዮን ካህናተ ደብተራ መካከል ቅዱስ ያሬድን ለሰማያዊ የመላእክት ጣዕመ ዜማ መረጠ ፡፡ይህንን ሰማያዊ ዜማ ቤተ-ክርስቲያናችን እንስካሁን ደስ እየተገለገለችበት ትገኛለች።

🛎#ማጠቃለያ

🙏ዜማ ቅድመ ቅዱስ ያሬድ ወይም ከሕገ ኦሪት መምጣት በፊት በንባብ ዜማ በቀስታ ፤ በዝግታ፤ በትሑት በማስተዛዘል ነበር ። የመዝሙረ ዳዊት ንባባዊ ዜማ ወይም ዜማዊ ንባብ ከታቦተ ጽዮን ጋር አብረው ወደ ሃገራችን መምጣት የመዝሙረ ዳዊቱም አገልግሎት እንደ አሁኑ ያሬዳዊው ዜማ ከመሆኑ በፊት በኦሪቱ ስርዓት በነበረው ዜማ ይካሄድ እንደ ነበር ያስረዳል።

#በገና #በገና_መዝሙር
#ኤርምያስበገና #ዝክረበገና
#ኦርቶዶክስ
#Begena #Ermiasbegena
#church #photo
#artistic #artwork
#bass #instrumental
#Begena #hilling
#meditation #strings
#harp #handmade
#kerar #kerarlesson

Комментарии

Информация по комментариям в разработке