01 track Ke eyesus gara Official zerfie kebede Amharic Iryics song

Описание к видео 01 track Ke eyesus gara Official zerfie kebede Amharic Iryics song

ከኢየሱስ ጋር

ከኢየሱስ ጋራ በሞቱ እኔ ተባብሬ
ለዓለም ሞቻለው እራሴን ከእርሱ ጋር ቀብሬ በቀሪው ዘመኔ ኢየሱሴን እየመሰልኩ መኖር እወዳለሁ
የእግዚአብሔርን መሻቱ በእኔ ላይ ገብቶኛል ይሄው ነው
ስንኝ
በዓለም ብኖርም አልመስላትም
ስርዓቷ አይገዛኝም
በዓለም ብኖርም አልመስላትም ነገሯ አይገዛኝም
በአዲሱ ማንነቴ ከሰማይ ነኝ እኔ
ከምድርም አይደለሁም ከሰማይ ነኝ እኔ
በሰማይ ኃይልና አቅም ብርታት ወጥቼ እገባለው
ባለድል ያረገኝ የተካፈልኩት የእግዚአብሔር ሕይወት ነው /2/

የኢየሱስ መሆኔ ነው የእኔ መለያዬ
ምድር ይዞ አያስቀረኝ ሰማይ ነው ኑሮዬ
አዝማች
ከኢየሱስ ጋር በሞቱ እኔ ተባብሬ
ለዓለም ሞቻለው እራሴን ከእርሱ ጋር ቀብሬ
በቀሪው ዘመኔ ኢየሱሴን እየመሰልኩ
መኖር እወዳለሁ
የእግዚአብሔር መሻቱ በእኔ ላይ ገብቶኛል ይሄ ነው
ብሪጅ
በስጋ ውስጥ ብኖርም ስጋዬ አይገዛኝም
በደሙ ዋጅቶኛል ኢየሱስ የራሴ አይደለሁም
ስጋዬ መቅደሱ ነው የመንፈስ ማደሪያ ነፃነቴን ተጠቅሜ ኃጢአትን አልሰራም
የኢየሱስ ሕያው መንፈስ ሕይወቴን ገዝቶታል
ለራሴ እንዳልኖር አድርጎ ለራሱ ማርኮኛል

የኢየሱስ መሆኔ ነው የእኔ መለያዬ
ምድር ይዞ አያስቀረኝሰማይ ነው ኑሮዬ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке