🔴አዲስ ዝማሬ "አርጋኖነ ድንግል"

Описание к видео 🔴አዲስ ዝማሬ "አርጋኖነ ድንግል"

#like #Share #Subscribe @arganon

አርጋኖነ ድንግል

"ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ?!የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ?! የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ?!"

"በእግዚአብሔር ስም አምነን ይህንን አርጋኖን የሚባል በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የእመቤታችንን ምስጋና እንጀምራለን"

ድንግልን አድንቀን እኛ እንዘምራለን
ማሪሃም ለተባለች በዕብራይስጥ ልሳን

የፍጥረቱ ያ'ርነት ጦማር የተጻፈብሽ ጽሌ
አንቀጸ ሥጋኪ ኅቱም ንሱግ በድንጋሌ
አንደበታችን መሰንቆ ከንፈራችን ይሁን በገና
ለድንግልናሽም ክብር እኑር ደጅ ስንጠና
°
ከመቃብር መውጣት መግባት በዝግ ቤቱ
አምሳያ አላቸው ለእኒህ ለክልዔቱ
በኅቱም መውለድሽ ነው ምክንያት አልቦቱ
(በጭብጨባ)👇
ከመቃብር መውጣት መግባት በዝግ ቤቱ
አምሳያ አላቸው ለእኒህ ለክልዔቱ
በኅቱም መውለድሽ ነው ምክንያት አልቦቱ

°
አዘቅተ በረከት አንቲ የሕይወት ውኃ መቅጃ
ደቦሉን የታቀፍሽ ነሽ ንጽሕቷ ጥጃ
አንቺ የደወል ደንጊያ መርስዔ ሰቆቃ
ክርስቲያን እንባል በምጽአት ስነቃ

ድንግልን አድንቀን እኛ እንዘምራለን
ማሪሃም ለተባለች በዕብራይስጥ ልሳን
                      ፨፨፨
የመናው መሥፈሪያ ነሽ አንቲ የወርቅ ጎሞር
ከአፈ አንበሳ የተቀዳሽ ወለላ ማር
እንበለ ዘር በቃል የጸነስሽ ሰፈፍ
የሆድሽ ፍሬ ደም አለ ሲንጸፈጸፍ
°
ደመ አቤል ናቡቴ የኦሪቱም መሥዋዕት
ፈሰው ነው የቀሩት አልሰጡንም ሥርየት
በልጅሽ ደም ማሪሃም አግኝተናል ሕይወት
(በጭብጨባ)👇
ደመ አቤል ናቡቴ የኦሪቱም መሥዋዕት
ፈሰው ነው የቀሩት አልሰጡንም ሥርየት
በልጅሽ ደም ማሪሃም አግኝተናል ሕይወት
°
የልጅሽ ደሙ መፍሰሱ እንዳይቀር በከንቱ
ዘወትር የሚቀዳው ከፈሳሽነቱ
ተግተሽ ለምኝልን ማሪሃም በነፍስ እንዳንሞት
የለም አንዳች ጊዜ አንቺን የተውንበት

ድንግልን አድንቀን እኛ እንዘምራለን
ማሪሃም ለተባለች በዕብራይስጥ ልሳን
                          ፨፨፨
እስክትወልድህ ድረስ ክብሯን ዮሴፍ አላወቀ
የቤትህም ቅናት በላን ስድባቸው ወደቀ
በእናትህ ድንግል ጸሎት የጽድቅንም ፍሬ እናፍራ
የባህርይ ሕይወትህ መንፈስ በነፍሳችን ያብራ
°
ቢገኝ አዳም ከምድር ሔዋንም ከር'ሱ ጎን
ቃየልም ቢወለድ ምን ከ'ርሷ ማኅፀን
ያንቺ መውለድ እንጂ እኒህ መች ጠቀሙን
(በጭብጨባ)👇
ቢገኝ አዳም ከምድር ሔዋንም ከር'ሱ ጎን
ቃየልም ቢወለድ ምን ከ'ርሷ ማኅፀን
ያንቺ መውለድ እንጂ እኒህ መች ጠቀሙን
°
እውነተኛ አምላክ ነው የራቀ መዓቱ
በስምሽ ስንለምነው አይዘገይ ምሕረቱ
የተመረጥሽ ድንግል ማሪሃም  እናቱ የሆንሽ 
አንቺ ከወደድሽን አይጠላንም ልጅሽ
                        ፨፨፨
የቅድስት ሥላሴ ማሪሃም ያንቺም በረከት
ይኑር ለዘለዓለም በእውነት ያለ ሐሰት ።
አሜን
"እመቤቴ ሆይ ይህ ሁሉ በጸሎትሽ ኃይል ተደረገ"

ግጥም እና ዜማ
ማይኪራህ

ዳይሬክተር
ናትናኤል ማርቆስ

ክራር ዲ.ን ዘላለም ታከለ
መሰንቆ ዲ.ን ያሬድ ግርማ
ዋሽንት የአብስራ ዘሪሁን

ድምጽ ቀረጻ ፡ ዘጎላ ሪከርድስ

ምስል ቀረጻና ቅንብር
ቃለአብ ሽታዬ
ቅዱስ ገዛኸኝ
ጳውሎስ ገዛኸኝ

ንባብ
ዲ.ን ዘላለም ፀሐይ

ልዩ ምስጋና
ዲ.ን ብሩክ ሽታዬ
ዲ.ን አቤል ሰሎሞን
ዲ.ን ዘማሪ አማን ኡርጌሳ
ኪዳኔ ኪሮስ
ወ/ሮ ቤተልሔም አሰፋ

‪@arganon‬ ‪@Deaconzelalemtakele‬ @maykirah


Any way of reproducing, reposting & reusing of this mezmur video is prohibited by ARGANON.

©አርጋኖን ሚድያ - Arganon Media - ፍልሰታ 2015|2023

Комментарии

Информация по комментариям в разработке