በገናችንን እራሳችን እንዴት ማሰር እንችላለን? ክፍል አንድ(1) (how to tie our Begena ourselves_EXPLAINED!) - PART ONE (1)

Описание к видео በገናችንን እራሳችን እንዴት ማሰር እንችላለን? ክፍል አንድ(1) (how to tie our Begena ourselves_EXPLAINED!) - PART ONE (1)

የበገና አስተሳሰር ክፍል አንድ (1) - HOW TO TIE BEGENA - PART ONE (1)

ብዙዎቻችሁ በፌስቡክ እና በቴሌግራም እንዲሁም በዩቲዩብ ቻናላችን ላይ በተደጋጋሚ በጠየቃችሁን መሰረት በገና ገዝታችሁ ነገር ግን ማሰርና መቃኘት ባለመቻላችሁ ምክንያት ለተቸገራችሁ ሁሉ ይህ ቪዲዮ በገናችሁን ራሳችሁ እንዴት ማሰር እና መቃኘት እንደምትችሉ (በተለይም ስለ በገና አስተሳሰር) በጥልቀት የሚያሳይ ቪዲዮ ነው።

በተለይም በዚህ ክፍል ፡ አውታር እንዴት እንደሚቋጠር ?
ከተቋጠረ በኋላ እንዴት ሸምቀቆ እንደሚሰራ?
የተቋጠረው እና የተሸመቀቀው የአውታር ጫፍ እንዴት መቃኛ ላይ እንደሚታሰር?
ሌላኛው የአውታር ጫፍ እንዴት መወጠሪያ ውስጥ ገብቶ እንደሚታሰር?
መቃኛው ቀንበሩ ላይ እንዴት እንደሚታሰር
የአውታሩ አጠማጠም እንዴት መሆን እንዳለበት እና ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችን የምናይበት ክፍል ነው።

ይህ ክፍል በገናን ለማሰር መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን የምናይበት በመሆኑ በጥንቃቄና በትኩረት ልናየው የሚገባ ክፍል ነው። በትምህርቱ ውስጥ ያልተረዳችሁት ወይም ያልገባችሁ ቦታ ካለ እንደተለመደው ከስር ባለው አስተያየት መስጭ ሳጥን ውስጥ ይጻፉልን። ቀጣዩን ክፍል በክፍል ሁለት የምናቀርበው መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን።

ከዚህ በፊት በቻናላችን የተላለፉ ተከታታይ የበገና ትምህርቶች ሊንካቸውን እነሆ

የበገና ትምህርት ክፍል 1
   • የበገና ትምህርት: ክፍል - 1 ... How to Learn ...  

የበገና ትምህርት ክፍል 2
   • የበገና ትምህርት - ክፍል 2 : ሰላምታ ቅኝት (BEGENA...  

የበገና ትምህርት ክፍል 3
   • የበገና ትምህርት - ክፍል 3 ፡ የጣት መልመጃ (BEGENA...  

የበገና ትምህርት ክፍል 4
   • የበገና ትምህርት: ክፍል  4 - [ ድምጽና ዜማን እንዴት ...  

ማስታወሻ፡
ክፍል 5 አና ቀጣይ ክፍሎች ይህ የበገና አስተሳሰር ክፍል 3 ቪዲዮ ካለቀ በኋላ የሚቀጥል መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነው። እስከዛው ድረስ ከክፍል 1 - 4 ያሉትን ትምህርቶች እና የጣት ልምምዶች በሚገባ እየተለማመዱ በቀጣይ ቀጣታ ወደ መዝሙር ጥናት ለምናደርገው ጉዙ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁን በአክብሮት እናሳስባለን።

አምላከ ቅዱስ ዳዊት አገልግሎታችንን ይባርክልን!

Комментарии

Информация по комментариям в разработке