Nega "ነጋ" by Dawit Getachew

Описание к видео Nega "ነጋ" by Dawit Getachew

Nega "ነጋ" by Dawit Getachew

ነጋ ሌሊቱ አለፈና
ዳግም ቆምኩኝ እኔም ለምስጋና
እነዚያ ቀናቶች አለፉ
እግዚአብሄር ከልሎኝ ከክፉ
እነዚያ ሌሊቶች አለፉ
ምህረቱ ሸሽጎኝ ከክፋ

በጨነቀኝ ግዜ ወደ አምላኬ ጮህኹኝ
ጩኸቴንም ሰምቶ ፈጥኖ ደረሰልኝ
በእኔ እና በሞት አንድ እርምጃ ሲቀር
የምህረት እጁ ነው የያዘኝ በፍቅር
ያወጣኝ በፍቅር
እንዴት እሆን ነበር ባይደርስልኝ ከገኔ
ጠላት በዋጠኝ በጠፋሁኝ ነበር ያኔ
እንዴት እሆን ነበር ዞር ብዬ እያሰብኩኝ
ለአዳነኝ ፀጋ መስጋናን እሰዋለሁኝ


የምህረቱ ብዛት በህይወት አቆመኝ
እንጂ በእራሴማ ትናንትን ባልኖርኩኝ
ዛሬን ባላየሁኝ
ለነገም ተስፋዬ እግዚአብሔር ነውና
ስሙን እባርካለሁ በብዙ ምስጋና

የማያልፍ ከሚመስል የህወቴ ሌሊት
ፈጥኖ የታደገኝ ሰው ከማይደርስበት
እግዚአብሔር ነው የህይወቴ ብርሀን
የእንደገና አምላክ የሰጠኝ ሌላ እድልን

በክንፎቹ መሀል አዝሎ አሻገረኝ
ብቻውን እየመራ እዚህ አደረሰኝ
ተጠነቀቀልኝ እንደ አይኑ ብሌን
ጸጋና ምህረቱን አብዝቶ ያለመጠን

አምላክ አለኝ የሚራራልኝ
ገና ሳልነግረው የሚረዳኝ
አይኑ እንዳየ የማይፈርድ
ለዘላለምም የሚወድ
ባለቀስኩበት ቀናት ፈንታ
ልቤን ሞላው በእልልታ
የዘወትር ዋና ስራዬ
ምስጋናው ሆኗል የጌታዬ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке