የኦንሊ ጂሰሶች አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አረዳድ በቢሾፕ ተክለማርያም እንዴት ተብራራ? መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል? Trinity vs Oneness Ep 14

Описание к видео የኦንሊ ጂሰሶች አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አረዳድ በቢሾፕ ተክለማርያም እንዴት ተብራራ? መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል? Trinity vs Oneness Ep 14

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በተለምዶ ኦንሊጂሰስ በመባል የሚታወቀው ቤተእምነት በጣም አደገኛ እና መፅሀፍቅዱስን የሚፃረር የሀሰት እምነት ነው:: ኢየሱስ ኢየሱስ ይላሉ ግን የመፅሀፍ ቅዱሱን ኢየሱስ ፈፅሞ አይቀበሉም:: በወንጌል የሚያምኑ ይመስላሉ ግን የአዲስኪዳንን ወንጌል ፈፅሞ ወደጎን በማለት የራሳቸውን ሰው ሰራሽ ዶክትሪን እና ሀይማኖታዊ ህግጋቶቻቸውን ከመፅሀፍ ቅዱስ በላይ የሚያምኑ ወገኖች ናቸው:: ምእመኖቻቸውም መፅሀፍ ቅዱስን እያነበቡ ስለ አምላካቸው ከማወቅ ይልቅ ድርጅቱ እና የድርጅቱ አስተማሪዎች የሚሉትን ብቻ እንዲቀበሉ ይገደዳሉ:: ኢየሱስን መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚለው በቅጡ ሳያምኑ እና ሳይቀበሉ የውሀ ጥምቀት የዘላለም ህይወት ያስገኛል ብለውም ያምናሉ::

በአጭሩ መፅሀፍ ቅዱስን ያለአግባብ በአውዱ እና በስርአቱ ካለማንበብ እና ካለመረዳት የተነሳ የተፈጠረ ድርጅት "CULT” ነው:: ከዚህም የተነሳ የኢየሱስ ማንነት ላይ እጅግ በጣም ስተዋል!

ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የወልድ እና የመንፈስቅዱስን መለኮታዊነትን የሚክድ ቤተእምነት ነው:: አንዱ እግዚአብሔር ወይም አንዱ መለኮት በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስቅዱስ ተገልጦ እንደሚኖር አያምኑም::

በኦንሊጂሰስ አስተምሮ በስጋ የተገለጠው ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ሳይሆን እግዚአብሔር አብ ነው:: ኦንሊጂሰሶች የወልድን ዘላለማዊነትም ይክዳሉ:: የእግዚአብሔር ልጅ ለነሱ ከድንግል ማርያም የተወለደ የስጋ ሰውነት ብቻ ነው:: ስጋውንም ሰማያዊ ወይንም መለኮታዊ ከሰማይ የመጣ ስጋ ነው እንጂ የዳዊትን ዘር በስጋ ተካፈለ ብለው አያምኑም:: (ሮሜ 1:3, ሮሜ 9:5, ዕብ 2:14, ራእይ 22:16)

ልጁ ከዘላለም ጀምሮ የነበረ የምድር እና የሰማይ ፈጣሪ መሆኑን ይክዳሉ (ዩሀ 1:3, ዕብ 1:2, ዕብ 1:10, ቆላስያስ 1:16) የእግዚአብሔር ልጅ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ከአባቱ ጋር ይኖር የነበረ መሆኑንም አያምኑም (ዮሀ 1:1, ዮሀ 6:38, ዮሀ 16:28, ዮሀ 17:5)

ኦንሊጂሰሶች እባካችሁ ለእግዚአብሔር ቃል ለመፅሀፍ ቅዱስ ስልጣን ሰጥታችሁ ለህሊናችሁ ታማኝ በመሆን ቃሉን ካነበባችሁት ሳታውቁት የወደዳችሁት የመፅሀፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በሙላት ይገለጥላቹሀል:: የኢየሱስ ማንነት ላይ መሳሳት ከዘላለም ህይወት መጉደልን ያስከትላል:: 1ኛ ዮሀ 5:12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። እባካቸሁ ከቃሉ ጋር እግዚአብሔር እየተማፀናችሁ ጊዜ አሳ ልፉ:: እግዚአብሔር እውነቱን ይግለጥላችሁ ወዳጆቼ!

Комментарии

Информация по комментариям в разработке