አቡነ ኪሮስ መዝሙር፣ አባ ኪሮስ መዝሙር፣ የአቡነ ክሮስ መዝሙር | Abune Kiros Mezmur [New Ethiopia Orthodox Tewahdo Mezmur]

Описание к видео አቡነ ኪሮስ መዝሙር፣ አባ ኪሮስ መዝሙር፣ የአቡነ ክሮስ መዝሙር | Abune Kiros Mezmur [New Ethiopia Orthodox Tewahdo Mezmur]

#Abune_Kirose_Mezmur
Abune Kiros
#የአቡነ_ኪሮስ_መዝሙር
አቡነ ክሮስ መዝሙሮች
#አባ_ኪሮስ_መዝሙር
አባታችን አባ ኪሮስ

አቡነ ኪሮስ ረድኤት በረከት አይለየን🙏🏽

ስንቶቻችን ነን ስለ አባ ኪሮስ ታሪክ የምናውቀው?

አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡

ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ተወለዱ፡፡

አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡ በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡

ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።

ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጅ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመታቸው ሐምሌ 8 አርፈዋል።

ከቅዱሳን ሁሉ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን አሳድርብን፡፡ በድፍረት፣ በትዕቢት በመናቅም በቅዱሳን ላይ የሚናገሩ የሽንገላ አንደበት ዲዳ ይሁኑ መዝሙር 30፡18 አንዳንዶችን በቅዱሳን ላይ ተነስቷልና ይቅር ይበላቸው፤ ልቦና ይስጣቸው መድሃኒትዓለም የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው ያለው ጌታ ይቅር ይበላቸው፡፡ …እንግዲህ እግዚአብሔር የመረጠውን ማን ይከሳል። ሮሜ 8፡28-31 “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል እናንተን የጣለ እኔን ይጥላል እኔን የጣለ የላከኝን ይጥላል።” ሉቃ. 10፡16

“ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ መዝሙር” 111፡6

+++…ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል… እውነት እላችዃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም…+++። ማቴ.10፡40-42

ሼር በማረግ ላላወቁ እናሳዉቅ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке