"ያኸይረል አናም" | YAKHEIREL ANAM | ARHIBU NEBI | AMIR HUSSEN

Описание к видео "ያኸይረል አናም" | YAKHEIREL ANAM | ARHIBU NEBI | AMIR HUSSEN

Full lyrics
አርሂቡ ነቢ ያ ኸይረል አናም
✦ ✦ ✦ ✦ ✦ ✦ ✦ ✦ ✦
አርሂቡ ነቢ ያ ኸይረል አናም
አርሂቡ ነቢ ያ ኸይረል አናም
ዐለይከ ሶላት ወሰላም
በዐሪፎች ጀሰድ ላይ ተጠምጥማ፣
በሷ እያዜሙ ስንቱ ሰው ደማ፣
ልቤን ወሰደች እቺ መንዙማ፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
አልሐምዱሊላህ ረቢዕ ዘለቀ፣
የዊላዳው ወር አሸበረቀ፣
እውነት ሐቀቀ ከፋው ሸይጧንም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
ማን እንደ አሚና ወርቅ ልጅ ወልዶ፣
የፋርሱን እሳት ያጠፋው ማልዶ፣
ታዬ ተንዶ ወድቆ ጣኦቱም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
ቀስት አስወንጭፎ ወግቶኝ ትዝታ፣
ናፍቆት ነካክቶኝ ሄደ በማታ፣
የእርሶን ትዝታ ግድ ሆኗል ማለም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
የአሏህ ፊት ወደድ (ያ ያማረ) አሽከር፣
ፊቱ ያበራል መስሎ ከጀንበር፣
የፋጢማ አባት ደግሞም የቃሲም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
ሐበሻ ሆኖ ጭኖኝ ሙሐባ፣
ሹመትን ለብሶ ልቅና ካባ፣
ሸርቀን ወቐርባ ይሄዳል ሱለም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
አይኔም በስሞ ትንሰቅሰቅ ታንባ፣
ፍቅር በረደኝ አልብሱኝ ካባ፣
ነብሴ ተከባ በዱንያ አለም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
በሌላም አይደል ነው'ኮ ባንቱ፣
እንባዬ ፈሶ ቢደርቅ ቋቱ፣
ነው ባንደበቱ ማጣቱ ከላም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤

ካላገኘሆት እንዲህ ጓጉቼ፣
ነቢ ያላንቱ ቢሆን ነው ሞቼ፣
አንቱን አጥቼ መኖር አልችልም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
ሸልጎ ይዞኛል ዱንያ አካቦ፣
በጠና ሐጃ እኔን ሸብቦ፣
ልወሰልቦ ልክ እንደ አደም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
የጫሎች ወዳጅ የነ አንይ፣
ስሙ አሕመድ ነው የኔ ደስታዬ፣
ማጣፈጫዬ የህይወት ቅመም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
ሌላው ቀርቶብኝ ልመዘን ባንቱ፣
አይሆንልኝም አንቱን ማጣቱ፣
በሰፊ እዝነቱ ከጥፋት 'ሚያርም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
አፈረች አይታ ኑሩ ቢብላላ፣
የኛን የውዱን የረሱለሏህ፣
ከአድማስ ጥላ ቀረች ፀሀይዋም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
በል ታገስልኝ ቻለው ቀለሜ፣
የሙሐባው ምስጥ በልቶኝ በቁሜ፣
አለቀ ደሜ አሳጣኝ አቅም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
ነቢ ባንቱ ነው ሚሽር ህመሜ፣
ደምግባቴ ኖት የኔ ሰላሜ፣
ይቆረጥ ጥሜ በፍቅሮ ዘምዘም፣
ዐለይከ ሶላት ወሰላም፤
ካልዘለቅኩማ ከናንተ ግቢ፣
ካልሆንኩኝማ ላንቱ ተገቢ፣
ያኔ ነው ነቢ ቀኑ ሚጨልም፣
አለይከ ሶላት ወሰላም፤
አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢዬ
አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢዬ
አርሂቡ ነቢ አሰላሙ ዐለይኩም
አርሂቡ ነቢ ሙሐመድ ምስጉኑ፣
አርሂቡ ነቢ ግዛቱን መለከው
አርሂቡ ነቢ ሹመቱ ስልጣኑ፣
አርሂቡ ነቢ በግሩ የረገጠው
አርሂቡ ነቢ ይሰብታል አማኑ፣
አርሂቡ ነቢ ዐፍያው ሁሉ ሙሉ
አርሂቡ ነቢ ያዬው ሰው በአይኑ፤
አርሂቡ ነቢዬ ሶላትናሰላም
አርሂቡ ነቢዬ ይከታተልቦ፣
አርሂቡ ነቢዬ በራሕመት ዳመና
አርሂቡ ነቢዬ 'ማያባራ ዘንቦ፤
አርሂቡ ነቢ በረቢዕ ጨረቃ
አርሂቡ ነቢ በመውሊዱ ጮራ፣
አርሂቡ ነቢ ፅልመቱ ገለጠው
አርሂቡ ነቢ ሰማያችን ጠራ፣
አርሂቡ ነቢ ሰብላችን አበበ
አርሂቡ ነቢ ፍሬውም አፈራ፣
ወርቄዋ ነቢ በስማችሁ በርከት
አርሂቡ ነቢ ሞላልን ጎተራ፤
አርሂቡ ነቢዬ የሄደ (ይፈረጅ)
አርሂቡ ነቢዬ ስምሁን ሲጣራ፣
አርሂቡ ነቢዬ አቤት ለቤክ በሉት
አርሂቡ ነቢዬ ያ ሰይደል ወራ፤
አርሂቡ ነቢ ለኛማ ሰርክ አዲስ
አርሂቡ ነቢ ንጋት ኖት ማለዳ፣
አርሂቡ ነቢ ንጉስ የንጉስ ልጅ
አርሂቡ ነቢ 'ሚናፈቅ እንግዳ፣
አርሂቡ ነቢ ንጉስ ነገሰ አሉ
አርሂቡ ነቢ በጠይባ ከተማ፣
ወርቄዋ ነቢ አለም እስኪገረም
ወለላው ነቢ ሁሉም እስኪሰማ፤
አርሂቡ ነቢዬ መንገሱ አይቀርም
አርሂቡ ነቢዬ ባይሆን መቆየቱ፣
አርሂቡ ነቢዬ ትላቸው ነበረ
አርሂቡ ነቢዬ አሚናት እናቱ፤
አርሂቡ ነቢ የቁረይሽ እንስቶች
አርሂቡ ነቢ በሞላ ጠቅላላ፣
አርሂቡ ነቢ በላጭ ነው የኔ ልጅ
አርሂቡ ነቢ ከእናንተ ጨቅላ፣
አርሂቡ ነቢ ሶብሮ ተቀምጦ
አርሂቡ ነቢ አስከ'ርባ አመቱ፣
አርሂቡ ነቢ ሂጃዛ ቢሰጠው
አርሂቡ ነቢ የነቢይነቱ፤
አርሂቡ ነቢዬ ለካስ እውነት ነበር
አርሂቡ ነቢዬ ያለችው እናቱ፣
አርሂቡ ነቢዬ ንጉስ የንጉስ ልጅ
አርሂቡ ነቢዬ በናትም ባ'ባቱ፤
አርሂቡ ነቢ ካባም የማይሻ
አርሂቡ ነቢ ልቅናው ሹመቱ፣
አርሂቡ ነቢ ተሹሞ በአዘል
አርሂቡ ነቢ ከ'ሏህ ከሶመድ፣
አርሂቡ ነቢ ንግስትናም አይሻ
አርሂቡ ነቢ ጌጥም ቢሆን ዘውድ፤
አርሂቡ ነቢዬ ፍቅሬም እስኪጠና
አርሂቡ ነቢዬ ልቤ እስኪሆን ላንቱ፣
አርሂቡ ነቢዬ ይድፋው እንጂ ወስዶ
አርሂቡ ነቢዬ ባፍጢም በደረቱ፣
አርሂቡ ነቢ ይለቅ እንጂ እንዲሁ
አርሂቡ ነቢ አይቀንስ ናፍቆቱ፣
አርሂቡ ነቢ ሰኮንድም ደቂቃ
አርሂቡ ነቢ ግዚያትም ሰአቱ፣
አርሂቡ ነቢ ፊዳ ይሁንሉህ
አርሂቡ ነቢ ተደምሮ ላንቱ፣
አርሂቡ ነቢ እንዴት ያለ ነቢ
አርሂቡ ነቢ አወዬው ፅናቱ፤
አርሂቡ ነቢዬ እንዴት ያለ ነቢ
አርሂቡ ነቢዬ አወዬው ፅናቱ፣
አርሂቡ ነቢዬ ለራሱም አይሻ
አርሂቡ ነቢዬ ጭንቀት ለኡመቱ፤
አርሂቡ ነቢ ሚቀምሰው የሌለው
አርሂቡ ነቢ ዲንጋይ ተሸክሞ፣
አርሂቡ ነቢ ቀኑን ሙሉ ፁሞ፣
አርሂቡ ነቢ ለይሉን ሙሉ ቁሞ፣
አርሂቡ ነቢ እንደሰው ያልበላ
አርሂቡ ነቢ ከወተት ከማሩ፣
አርሂቡ ነቢ ቀኑን ሙሉ ቢፆም
አርሂቡ ነቢ አንድ ቴምር ፊጥሩ፣
አርሂቡ ነቢ በጨለማ ፅልመት
አርሂቡ ነቢ የኖረ በቤቱ፣
አርሂቡ ነቢ ጎጆው እሳት ሳይነድ
አርሂቡ ነቢ ያልፋሉ ወራቱ፣
ወርቄዋ ውዴዋ ለማረፍ ቢመኙ
አርሂቡ ነቢዬ ሚተኙበት ፍራሽ፣
አርሂቡ ነቢዬ በጭድ የተሞላ
አርሂቡ ነቢዬ የማይመች ጭራሽ፤
አርሂቡ ነቢ በጀሰድ ባካሉ
አርሂቡ ነቢ ሲያወጣ ሰንበር፣
አርሂቡ ነቢ አካሉ ሲደማ
አርሂቡ ነቢ ያ ጥርሱ ሲሰበር፤
አርሂቡ ነቢዬ አንደበትም ቃላት
አርሂቡ ነቢዬ የማይገልፀው ክቦ፣
አርሂቡ ነቢዬ ምላስ ልትናገር
አርሂቡ ነቢዬ ይይዛል ሸብቦ፤
አርሂቡ ነቢ አንጀቱ ተቋጥሮ
አርሂቡ ነቢ ልቡ ተሸብቦ፣
አርሂቡ ነቢ በማይሽር በሽታ
አርሂቡ ነቢ ሆነበት ተስቦ፤
አርሂቡ ነቢዬ ጀሰዱም እንደጧፍ
አርሂቡ ነቢዬ አብርቶ ይቀልጣል፣
አርሂቡ ነቢዬ ጅማትና ክሩ
አርሂቡ ነቢዬ ደም‐ስሩን በልቶታል፤
አርሂቡ ነቢ በሩሕ እያኖረ
አርሂቡ ነቢ በናፍቆቱ ሙቷል፣
አርሂቡ ነቢ በስሙ ገርገራ
አርሂቡ ነቢ ጀማሉ ናፍቆታል፣
አርሂቡ ነቢ ከላፈውም ኋላ
አርሂቡ ነቢ ከመጪውም ፊቱ፣
አርሂቡ ነቢ ካ'ለማት ጠቅላላ
አርሂቡ ነቢ ከሩህካኢናቱ፣
አርሂቡ ነቢ እዲያ ሹመቱ፣
አርሂቡ ነቢ ተቆንጥሮ ካንቱ፣
አርሂቡ ነቢ ለወዳጁ ሁላ
አርሂቡ ነቢ ሁኗል መስታወቱ፣
አርሂቡ ነቢ አባቱ ማለደ
አርሂቡ ነቢ ሳይታይም ዛቱ፤
አርሂቡ ነቢዬ ያ'ደም የጅስም ልጅ
አርሂቡ ነቢዬ የሩሑ አባቱ፣
አርሂቡ ነቢዬ ያ'ደም የጅስም ልጅ
አርሂቡ ነቢዬ የሩሑ አባቱ፤
አርሂቡ ነቢ የምር የወደዱ
አርሂቡ ነቢ ያፈቀሩ ለታ፣
አርሂቡ ነቢ ምላሱን ሸልጎ
አርሂቡ ነቢ በፍቅር ትንታ፣
አርሂቡ ነቢ ልቡን ሲያቃጥለው
አርሂቡ ነቢ ፍም ሁኖ ትዝታ፣
አርሂቡ ነቢ ጨርቅንም ያስጥላል
አርሂቡ ነቢ እንባም አይገታ፤
አርሂቡ ነቢዬ ይሰማል ጩኸቱ
አርሂቡ ነቢዬ የፍቅር ሁካታ፣
አርሂቡ ነቢዬ ከምድርም አልፎ
አርሂቡ ነቢዬ ከሰማዩ ዋልታ፤
አርሂቡ ነቢ ሙሾም እያስሟሸ
አርሂቡ ነቢ ደረት እያስመታ፣
አርሂቡ ነቢ እሷን ለመዘየር
አርሂቡ ነቢ ነፍሱ ተንከራታ፣
አርሂቡ ነቢ ሰብታበት ሙሐባ
አርሂቡ ነቢ ከገደሉ ገብታ፣
አርሂቡ ነቢ ዳገት ቁልቁለቱ
አርሂቡ ነቢ አይገታው ኮረብታ፤
አርሂቡ ነቢዬ በመውደዱ ቃና
አርሂቡ ነቢዬ በመውደዱ ሽታ፣
አርሂቡ ነቢዬ ተይዞ በፍቅር
አርሂቡ ነቢዬ በማይድን በሽታ፣
ወርቄዋ ነቢዋ ሐለቱን አድርጎት
አርሂቡ ነቢዬ እንደብርቅርቅታ፤
አርሂቡ ነቢ ሲያዝን ሲተክዝ
አርሂቡ ነቢ ደግሞም በደስታ፣
አርሂቡ ነቢ አርግዞ በሆዱ
አርሂቡ ነቢ የሙሐባ መንታ፣
አርሂቡ ነቢ
ከፊቱ ወጣበት
አርሂቡ ነቢ የመውደዱ ሽታ፣
አርሂቡ ነቢ በሶብርም አይቆይም
አርሂቡ ነቢ በስፍራ በቦታው፤
አርሂቡ ነቢዬ እንዲያው ይኖረዋል
አርሂቡ ነቢዬ ፍቅሮ ሲያንገላታው፣
አርሂቡ ነቢዬ በሱብሒ ላይ ዋሽንት
አርሂቡ ነቢዬ በለይሉ እንቢልታ፣
አርሂቡ ነቢዬ በጠራ ጨረቃ
አርሂቡ ነቢዬ ሳለ በፀጥታ፤
አርሂቡ ነቢ እሱ ለብሶ ኖሮ
አርሂቡ ነቢ የሙሐባን ኩታ፣
አርሂቡ ነቢ ያወርዳል ሰለዋት
አርሂቡ ነቢ ያቀርባል ሰላምታ፣
አርሂቡ ነቢ የምር የወደዱ
አርሂቡ ነቢ ያፈቀሩ ለታ፣
አርሂቡ ነቢ ቀብድ እያስከፈለ
አርሂቡ ነቢ የፍቀሩ ውለታ፤
አርሂቡ ነቢዬ የምር የወደዱ
አርሂቡ ነቢዬ ያፈቀሮ ለታ፣
አርሂቡ ነቢዬ ቀብድ እያስከፈለ
አርሂቡ ነቢዬ የፍቅሮ ውለታ፣
አርሂቡ ነቢ እሩሑ በኒካሕ
አርሂቡ ነቢ ከርሱ ጋር ተጋብታ፣
አርሂቡ ነቢ ከሰውነት አለም
አርሂቡ ነቢ (አደቡ) ተጣልታ፣
አርሂቡ ነቢ ይሄዳል ይጓዛል
አርሂቡ ነቢ በለሊት በማታ፣
አርሂቡ ነቢ የጠራችው ሰአት
አርሂቡ ነቢ በጠራችው ቦታ፤
አርሂቡ ነቢዬ በናንተ ስም ጥሪ
አርሂቡ ነቢዬ የኛ ወንጀል ታጥቦ፣
አርሂቡ ነቢዬ ብታጠጡን ብለን
አርሂቡ ነቢዬ ከውዴታው ገንቦ፣
አርሂቡ ነቢ ከሐድራቹ አበባ
አርሂቡ ነቢ ልባችን አብቦ፣
አርሂቡ ነቢ ተነድፈን ባረፍን
አርሂቡ ነቢ በናንተዋ ንቦ፣
አርሂቡ ነቢ ተነድፈን ባረፍን
አርሂቡ ነቢ በናንተዋ ንቦ፣
አርሂቡ ነቢዬ ማሬ ወለላዬ፣
አርሂቡ ውዴዋ አርሂቡ ነቢዬ
አርሂቡ ነቢዬ አርሂቡ ነቢዬ፣

Комментарии

Информация по комментариям в разработке