Zema for Christ - ዜማ ለክርስቶስ - Meskelihin Ayalehu | መስቀልህን አያለሁ - 2020/2012

Описание к видео Zema for Christ - ዜማ ለክርስቶስ - Meskelihin Ayalehu | መስቀልህን አያለሁ - 2020/2012

ይህ መዝሙር አይናችንን እና ትኩረታችንን በመስቀሉ ላይ ስለማድረግ ነው፡፡
This song is about putting our eyes and focus on the Cross!


አይኖቼን ከመስቀልህ አንስቼ.......የመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሀ መዘምራን
ለሰው አላወራም........ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ)
መስቀልህን አያለሁ .........ኬነሳ ቡላ


ዓይኖቼን ከመስቀልህ አንስቼ
ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ርቄ (2)

የሕይወቴ ሰላም ሁሌ የሚፈልቅበት
ከጭንቀትም ሁሉ ልቤ የሚያርፍበት
ሐዘን ከኔ ርቆ ደስታን የማገኘው
ዓይኖቼን አንስቼ መስቀልህን ሳይ ነው

ዓይኔን የጣልኩበት ከመስቀልህ ሌላ
ዘለቄታ የሌለው ጠፊ ነው በኋላ
ዓለሙም ምኞቱም ሁሉም ያልፋልና
እርዳኝ የኔ ጌታ ባንተ እንድፀና

ዓይኖቼን ከመስቀልህ...

የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ
ትካዜዬን ሁሉ ባንተ ላይ እጥላለሁ
የመድሐኒቴ አምላክ ተስፋ አደርግሀለሁ/2/

ሰላም እረፍት መታደስን የማገኝበት
ስብራቴም የሚጠገንበት
አይኖቼን ወዳንተ አነሳለሁ
መስቀልህን አያለሁ

ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ርቄ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке