ነብዩ ኤልያስ እና ሄኖክ መምጣት፣ ኢይዝራኤላውዊ ናቡቴ በግፍ መገደል

Описание к видео ነብዩ ኤልያስ እና ሄኖክ መምጣት፣ ኢይዝራኤላውዊ ናቡቴ በግፍ መገደል

1ኛ ነገሥት 20
¹ ለኢይዝራኤላዊውም ለናቡቴ በሰማርያ ንጉሥ በአክዓብ ቤት አጠገብ የወይን ቦታ ነበረው።
² አክዓብም ናቡቴን፦ በቤቴ አቅራቢያ ነውና የአትክልት ቦታ አደርገው ዘንድ የወይን ቦታህን ስጠኝ፤ ስለ እርሱም ከእርሱ የተሻለ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ወይም ብትወድድ ግምቱን ገንዘብ እሰጥሃለሁ ብሎ ተናገረው።
³ ናቡቴም አክዓብን፦ የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ አለው።
⁴ ኢይዝራኤላዊውም ናቡቴ፦ የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም ብሎ ስለ ተናገረው አክዓብ ተቈጥቶና ተናድዶ ወደ ቤቱ ገባ። በአልጋውም ላይ ተጋድሞ ፊቱን ተሸፋፈነ፥ እንጀራም አልበላም።
⁵ ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ መጥታ፦ ልብህ የሚያዝን እንጀራስ የማትበላ ስለምንድር ነው? አለችው።
⁶ እርሱም፦ ኢይዝራኤላዊውን ናቡቴን፦ የወይንህን ቦታ በገንዘብ ስጠኝ ወይም ብትወድድ በፋንታው ሌላ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ ብዬ ተናገርሁት እርሱ ግን፦ የወይን ቦታዬን አልሰጥህም ብሎ ስለ መለሰልኝ ነው አላት።
⁷ ሚስቱም ኤልዛቤል፦ አንተ አሁን የእስራኤልን መንግሥት ትገዛለህን? ተነሣ እንጀራም ብላ፥ ልብህም ደስ ይበላት የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ አለችው።
⁸ በአክዓብም ስም ደብዳቤ ጻፈች፥ በማኅተሙም አተመችው፤ በከተማው ወደ ነበሩትና ከናቡቴም ጋር ወደ ተቀመጡት ሽማግሌዎችና ከበርቴዎች ደብዳቤውን ላከች።
⁹ በደብዳቤውም፦ ስለ ጾም አዋጅ ንገሩ፥ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀምጡት፤
¹⁰ ሁለትም ምናምንቴ ሰዎች በፊቱ አስቀምጡና፦ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው ይመስክሩበት አውጥታችሁም እስኪሞት ድረስ ውገሩት ብላ ጻፈች።
¹¹ በከተማውም የተቀመጡት የከተማው ሰዎችና ሽማግሌዎች ከበርቴዎችም ኤልዛቤል እንዳዘዘቻቸውና ወደ እነርሱ በተላከው ደብዳቤ እንደ ተጻፈ እንዲሁ አደረጉ።
¹² የጾም አዋጅ ነገሩ፥ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀመጡት።
¹³ ሁለቱም ምናምንቴ ሰዎች ገብተው በፊቱ ተቀመጡ፤ ምናምንቴዎቹ ሰዎችም በሕዝቡ ፊት፦ ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው በናቡቴ ላይ መሰከሩ። የዚያን ጊዜም ከከተማ አውጥተው እስኪሞት ድረስ ወገሩት።
¹⁴ ወደ ኤልዛቤልም፦ ናቡቴ ተወግሮ ሞተ ብለው ላኩ።
¹⁵ ኤልዛቤልም ናቡቴ ተወግሮ እንደ ሞተ በሰማች ጊዜ ኤልዛቤል አክዓብን፦ ናቡቴ ሞቶአል እንጂ በሕይወት አይደለምና በገንዘብ ይሰጥህ ዘንድ እንቢ ያለውን የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን ቦታ ተነሥተህ ውረስ አለችው። #ተዋህዶ #ethiopia #habesha #መዝሙር #duet #love #ኦርቶዶክስ_መዝሙር #arbaminch #ወንጌል

Комментарии

Информация по комментариям в разработке