Tsedenia G/Markos - Himemie (Lyrics) - Ethiopian Music

Описание к видео Tsedenia G/Markos - Himemie (Lyrics) - Ethiopian Music

🎵 Tsedenia G/Markos - Himemie (Lyrics) - Ethiopian Music

🎥 Official Music Video:    • Tsedenya G/Markos - Himemie New clip ...  

❤ Be a family of 7clouds by subscribing here:    / 7cloudset  

🎤 Lyrics 🎤

እጅህ ይዳብሰኝ ዞሮ ከወገቤ
ይወገዳል ጭንቄ ይርቃል ሃሳቤ
ልበልህ ሐኪሜ ልበልህ ፈዋሼ
ሰላም የሰጠኸኝ ጤናዬ ዳባሼ
የተባረከ እጅ ባምላክ የተቀባ
ቢታቀፉት ፍቅር ቢያሸቱት አበባ
ያምላክ ቀባ ቅዱስ የቸርነት ጥበብ
በእጅም ይገለጣል በሰው በሰበብ
ነካካው ገላዬን አካሌን ደባብሰው
በመዳፍህ አይደል የልቤ የሚደርሰው
ታከምኩኝ በጆችህ ሆንኩኝ በመዳፍህ
እራኩኝ ከህመሜ በገላ በእቅፍህ
ማነው ያስተማረህ እንዲህ ያለ ጥበብ
በእጅ እየነኩ በጤና መሰብሰብ
በሐኪም በፀበል መላ የጠፋለት
በእጆችህ መዳፍ ዳንኩኝ እንደዘበት
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
እንደ ጀምበር ሞክቁት እጁን እንደ ፀሐይ
የመዳፉን ብርሃን ለማንም ሳላሳይ
አልተክል አበባ ቤቴን እንዲያደምቀው
እጁ ይበቃኛል መዓዛ የሚያፈልቀው
ሀርና ሱፉ ነኝ ለጅ እና መዳፉ
ነፍሴን እያሞቃት ሰብስቦ ከእቅፉ
አንድም ተፈወስኩኝ አንድም ተደገፍኩ
በእጁ በመዳፉ ስንቱን ተሻገርኩ
እንዳማረ ሸማ እንዳማረ ፈትል
ይደምቃል ገላዬ ከሱ ጋራ ስውል
ማን አለ በምድር እንደኔ የረታ
በወዳጁ መዳፍ ህልሙ የተፈታ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ

#TsedeniaGMarkos #Himemie #EthiopianMusic

Комментарии

Информация по комментариям в разработке