Hayelom Debash - Nereaya - ሓየሎም ደባሽ - ንርአያ New Ethiopian Raya Music 2024 ( Official Video )

Описание к видео Hayelom Debash - Nereaya - ሓየሎም ደባሽ - ንርአያ New Ethiopian Raya Music 2024 ( Official Video )

" #ንርአያ " ድምፃዊ ሓየሎም ደባሽ / Hayelom Debash

በልጅነት ዕድሜው በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈው በዕድሜ ትንሹ ድምፃዊ ሓየሎም ደባሽ ለረዥም ዓመታት ከሙዚቃው አርት ጠፍቶ እንደነበር ይታወቃል ። በጣም ከመጥፋቱ የተነሳ ከዚህ በፊት በሶሿል ሚድያ በህይወት የለም የሚሉ ሀሰተኛ ወሬዎች ሲሰራጩ እንደነበር ሁላችሁም የምታውቁት እውነት ነው ።

እኔም በግዜው በሶሿል ሚድያ ሲሰራጭ የነበረውን ነገር እውነት እንዳልሆነ ስለማውቅ ሓየሎም ያለበትን ሁኔታ ለመጠየቅ ተወልዶ ያደገበት ቦታ ድረስ በመሄድ በህይወት እንዳለ ለማሳወቅ ኢንተርቪው አድርጌለት ነበር ። ብዙዎችም ያንን ኢንተርቪው ካዩ ቡኋላ በሶሿል ሚድያ ሲሰራጭ የነበረው ሓየሎም በህይወት የለም የሚል ሀሰተኛ መረጃ እውነት እንዳልሆነ ማረጋጥ ችለዋል ።

ሓየሎም የ 14 ዕድሜ ልጅ እያለ ወደ ህዝብ ያደረሰው ራያ ዓደይ - Raya Adey የሚል ነጠላ ዜማው በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት አትርፏል ።

አሁን ደግሞ ከረዥም ዓመታት ቡኋላ እጅግ በጣም ብዙ የተለፋበት ብዙዎች ይወዱታል ተብሎ የሚጠበቀው #ንርአያ የተሰኘው አዲስ ነጠላ ዜማ ይዞልን መጥቷል !

ከዚህ በፊት ሓየሎም በህይወት የለም ተብሎ በሶሿል ሚድያው የሀሰት ወሬ ሲናፈስ በነበረበት ግዜ በራያ አላማጣ ልዩ ስሙ ላዕላይ ዳዩ በመባል የሚታወቀው የሓየሎም የትውልድ ቦታ ድረስ በመሄድ ያደረግነው ኢንተርቪው ከስር ያለው ሊንክ በመጫን ቭድዮውን እንድትከታተሉ ጋብዘናል !

ሊንኩ 📲⏬    • 🛑በአለም ዙርያ ሞተ ተብሎ ሲወራለት የነበረው በእድሜ ትንሹ...  

Комментарии

Информация по комментариям в разработке