ትንቢተ ዮናስ - እግዚአብሔር መሐሪ ነው! (እንደ ዮናስ አንሁን!!)

Описание к видео ትንቢተ ዮናስ - እግዚአብሔር መሐሪ ነው! (እንደ ዮናስ አንሁን!!)

የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ማእከላዊ ጉዳይ የእግዚአብሔርን መሐሪነት በማሳየት እና እንደ ዮናስ እንዳንሆን ማስተማር ነው። ነቢዩ ዮናስ ወደ ነነዌ ሲላክ ወደ ተርሴስ የኮበለለበት ምክንያት ለነነዌ ሕዝብ ከሰበከና ሕዝቡ በንስሐ ከተመለሰ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለው በመረዳቱ ነበር (ዮናስ 4÷2)። ነነዌ የአሦራውያን ዋና ከተማ ስትሆን አሦራውያን የእግዚአብሔርን ሕዝብ በተለያዩ መንገዶች በድለዋል፤ ከቦ በማስጨነቅ፣ በመበዝበዝ፣ በመግደል፣ በመማረክ፣ ወዘተ. ሕዝቡን በብዙ ጎድተዋል። ከዚህም የተነሳ የእስራኤል ሕዝብ በዚህ ሕዝብ ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እንዲገለጥ ይፈልጋል። ዮናስም ለዚህ ሕዝብ ለመስበክ ፈቃደኛ ያልሆነበት ምክንያት ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው። ዮናስ ስለ ማንነቱ እና ስለሚያመልከው እግዚአብሔር ያለው መረዳት አስገራሚ ነው። ይህ መረዳቱ ግን ስለ ሌሎች ያላውን አመለካከት እና ከሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነት አልቀየረም። ስለ ጎዱን ሰዎች፣ ስላሳዘኑን እና በብዙ ስለ በደሉን ሰዎች ስናስብ ቶሎ ወደ ልባችን የሚመጣው ምን ይሆን? በቀል ወይስ ምሕረት? ይህ መጽሐፍ እንደ ዮናስ እንዳንሆን ያስተምረናል። ይህቺን አጭር ቪድዮ በመመልከት የመጽሐፉን ማእከላዊ ሐሳብ ይገንዘቡ።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке