እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እምነት - ጳውሎስ ፈቃዱ

Описание к видео እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እምነት - ጳውሎስ ፈቃዱ

የእምነት ግቡ ምንድን ነው?
ሁሉስ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል?
ታዲያ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው እምነትስ የትኛው ነው?
ዕብራውያን 11 የእምነት አባቶችንና እናቶችን ግለ ታሪክ በየፈርጁ እየዘረዘረ እግዚአብሔርን ስለሚያስደስተው እምነት ምንነት ማስረጃና ድንቅ ትንታኔ ያቀርባል።
ዘመናችን በእምነት ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ በርካታ እሳቤዎች በየቤተ ክርስቲያኑ ምስባክ ሲሰራጩ ይገጥመናል፤ በዚህ ዐይነቱ ሁናቴ ውስጥ የዕብራውያን 11ኛ ምዕራፍ አስደናቂ መልእክት አለው።
እምነት ሲተነተንና ሲተገበር ምን እንደሚመስል ከዚህ ስብከት ባሻገር ተጨማሪ ትምህርት ለማግኘት ቢሹ፣ “የእምነት ኀይል” በሚል በጳውሎስ ፈቃዱ ወደ አማርኛ የተመለሰውን መጽሐፍ ቢያነቡ ይጠቀማሉ። ይህንንም መልእክት እዚያ ውስጥ ያገኙታል።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке