#ሚስኩን

Описание к видео #ሚስኩን

ከ ጭማሪ ግጥሞች ጋር,,,,,,

//ዑስታዝ ሰዒድ አህመድ//

በመልክም በሃል በፈድል በእጣ
ተገዳዳሪ የለው ባላንጣ
     ባህሪው ለጉድ ወደርን ቢያጣ
  ልሙት ለርሱ አለ ሊገል የመጣ
   ።።።።
አየ ጉድ ጠባይ አጀብ ኹሉቁ
  እንዴት አስውቦ ሰራዎት ሃቁ
  ጠላነው ያሉት ሸሽተው በሩቁ
  ተግሩ ስር ዋሉ ቀርበውት ሲያውቁ
።።።።።

የኔ መብሰልሰል መሞቅ መብረዴ
መጥበቅ መላላት መውጣት መውረዴ
ላንቱ መሆኑን አያውቁም እንዴ
በክፉ አነሶት ሳልገባ ለህዴ



አየ ሶሃቦች ሴት በለው ወንዱ
መገን ዑመሩ መገን ኻሊዱ
ያንቱን መነካት አውቀው በነበር
ሳይቀሉ አንገቱን አትጠልቅም ጀንበር



ሊገድሉት ሲሉ ሰይፍን ሲመዙ
ሊያጠፉት ቆርጠው ስጋም መረዙ
በቀል ሳያቅት በሃይል መያዙ
ከዝነት ሰገባ ረህመት ሚመዙ

ክብሬ እኮ ነበር ቢሆን ወደኔ
መንገላታትሁ ስቃዮት ለኔ
ቁስሎት ላካሌ እንባዎት ላይኔ
ቆሜ መሄዴ ባንቱ አይደል ዘይኔ

ያ የዝነት ጥጉ የጀነት ቁልፉ
አሏህ ያለዎት ረሂም ረኡፉ
ለኛው በኖሩ ለኛው በለፉ
ለምን ስላንቱ ይሰማል ክፉ

ለበድር ባልዘምት ባካል ብርቅም
ወይ የኸንደቅ ለት አፈር ባልዝቅም
ቅዋየ ቢላሽ ወዜ ቢደርቅም
አንቱ ተነክተሁ ዝምታ አላውቅም


ከናትም ራርተው በዝነት በኖሩ
ሌላን ለማብላት ድንጋይ ባሰሩ
ባንድነት ገመድ ባስተሳሰሩ
ለምን በክፉ ተነሱ አንዋሩ

እንኳን ሙስጦፋን የርስዎን ግድም
  በእጅሁ የነኩት ሊነካ አልፈቅድም
   ሃብት ንብረቴን ነፍሴንም እንካ
    ዘይኔን ተውልኝ ማይሆን አትንካ

በጭፍን ወቃሽ መሆኑን ትተህ
   ላንዴ እንኳን የርሱን ታሪኩን ከፍተህ
  ጥቂት ብትሰልል የሆኑ ያሉትን
   ነቢን ከመንካት ባስበለጥክ ሞትን

የሚቻል መስሎት አጉል ያለመ
ፀሃይን በጣት ሊጋርዳት ቆመ
ውበቷን አይሽር ጥቅሟን አይቆርሰው
ፀሃይ የለችም ቢልም እውር ሰው


« እፍ » ሲል ቢውል ሊያጠፋት ወዶ
የሻማ ልምዱን ፀሃይ ላይ ወስዶ
«ትል» ታይቶ አያውቅም ተራራን ንዶ
የማይሆን ላይሆን ትርፉ ነው ባዶ

ማር የመረረው ነክቶ ሲቀምሰው
ከንብ ይጣላል እንኳንስ ከሰው
አሏህ አጥምሞት ዞላም ካመሰው
ፅልመት ነው ለርሱ ኑር ብታለብሰው

።።።።

ዘይኔን በመጥፎ ለሚያነሳሱ
ሶብርም አይኖረው ሙሂብ እንደሱ
እሱማ አዛኝ ነው ለጠላት ቤትም
ፍቅር ኮ ነው ለሚጠሉትም

ጉድለት ባይቀርበው የሳቸው ጠባይ
ለከፋባቸው ናቸው ይቅር ባይ
ግን ወዳጆቹ ነፍስን ሰውተው
እረፍት አያውቁም ሐቢብ ተነክተው

🌟🌟🌟🌟🌟ሙዓዝ ሀቢብ ነኝ እወዳችኋለሁ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке