DW Amharic የሕዳር 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና

Описание к видео DW Amharic የሕዳር 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና

የህዳር 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና
ከትላንት ጀምሮ በበርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ታውቋል። የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ የተከሰተው በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በደረሰ እክል እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጸል።

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በደረሰ የከባድ መሣሪያ ድብደባ 28 ሰዎች መገደላቸውን ከአካባቢው የወጡ የሕክምና ምንጮች አረጋገጡ። ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችም መቁሰላቸውን ታውቋል።

የሶሪያው ፕዴዚደንት ባሽር አልአሳድ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሐገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን እየጠየቁ ነው። ነፍጥ አንግበው የበሽር አልአሳድን መንግስት ሲዋጉ የነበሩ ተቃዋሚዎች የሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆን ዛሬ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ሕዝቡ ወደ አደባባዮች በመውጣት ደስታውን ሲገልጽ ተስተውሏል።

የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በውልደት የሚገኘውን የአሜሪካ ዜግነት እሰርዛለሁ አሉ። ከዚህም ሌላ ትራምፕ የኔቶ አባል ሀገራት የሚጠበቅባቸውን መዋጮ የማይከፍሉ ከሆነ ሀገራቸው ከጥምረቱ የምትወጣበት መንገድ እንደሚያስቡበትም አስጠንቅቀዋል። ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬይን አስቸኳይ የተክስ አቁም ስምምነት እንዲደረስም ጥሪ አቀርበዋል።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке