Reyot Kin, Reminiscing Tesfaye Kasa ተስፋዬ ካሳ ሲተዘት፡፡ ቴዎድሮስ ጸጋዬ፡፡

Описание к видео Reyot Kin, Reminiscing Tesfaye Kasa ተስፋዬ ካሳ ሲተዘት፡፡ ቴዎድሮስ ጸጋዬ፡፡

ለተስፋዬ እንደካሳ፣ ተስፋዬ ካሳ ሲተዘት፡፡
ቴዎድሮስ ጸጋዬ፡፡
በጠራራ ቀትር፣ ከሞቃታማው ነፋስ ጋር እየታገልኩ፣ የጠዋቱን ብርድ ለማምለጥ የደረብኩትን ጃኬት መጣያ አጥቼ እየተጨነቅሁ፣ በእግረኛው መረማመጃ ላይ ጥጉን ይዤ አዘግማለሁ፡፡ ደክሞኛል፣ ታክቶኛል፡፡ ከትምህርት ቤት የጠዋት ፈረቃ ትምህርቴን ጨርሼ ወደቤት እየሄድኩ ነው፡፡
እንዲያ በመታከት ስጓዝ የመንገዱን ዳር ይዤ የተከፈቱትን የልብስ መሸጫዎች፣ ካፌዎች፣ የጌጣጌጥ መደብሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሱቆች፣ ጭማቂ ቤቶች ወዘተ አልፌ ከ፣ አንድ ሙዚቃ ቤት አጠገብ ደረስኩ፡፡ ያኔ የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ነኝ፡፡ ድንገት እሙዚቃ ቤቱ በር ላይ ከተቀመጠው ትልቅ ማጉያ SPEAKER የሚወጣ፣ ከነበርኩበት ድካም መንጭቆ የሚያወጣ ድምጽ ሰማሁ፡፡
ይህ በማጉያው ደመቅ ብሎ የተሰማኝ ድምጽ አዋጅ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም እምብዛም የማልሰማው ወይም ያልሰማሁት አይነት አዋጅ፡፡ እሙዚቃ ቤቱ በር ላይ ለ5 ደቂቃ ያህል የቆምኩ ይመስለኛል፡፡ በሰማሁት ስለተደሰትኩም ስለተገረምኩም ወደውስጥ ዘለቅሁና ከመስታወቱ ባንኮኒ ጀርባ የቆመውን ሰው ጠየቅሁት፡፡ “ይኼ የምሰማው ነገር ምንድነው?” ብዬ፡፡ እርሱም የተስፋዬ ካሳ አዲስ የቀልድ ክር መሆኑን ነገረኝ፡፡
ወጥቼ፣ ወበቁን እየሰነጠቅሁ ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡ ወደቤቴ፡፡ በማግስቱ፣ ከወንድሜ 7 ብር ተበድሬ፣ እዚያችው ሙዚቃ ቤት ሄጄ ቅጂ ካሴት ገዛሁ፡፡ ቅጂ ስል ኦሪጅናል ያይደለ ማለቴ ነው፡፡ ያቺም ካሴት ከወንድሜ ተበድሬም ቢሆን እኔው እራሴ የገዛኋት፣ በእኔ ንብረትነት የተመዘገበች የመጀመሪያዋ ካሴት ሆነች፡፡
ነገሩን ጥቂት አስፈጋጊ የሚያደርገው ግን ካሴቱን የገዛሁት ቴፕ ሳይኖረኝ መሆኑ ነው፡፡ ያኔ ግን ይኼ አስቂኝም አሳሳቢም አልነበረም፡፡ ምክንያቱም፣ ሙዚቃ ማዳመጥ ባሰኘኝ ጊዜ ከቤታችን 2 ግቢ ብቻ አልፌ፣ እትዬ መብራት ቤት ገብቼ፣ በእርሳቸው ቴፕ ከልጆቻቸው ጋር መስማት እችል ስለነበር ነው፡፡ ከወራት በኋላ የግል ማጫወቻዬን እስክገዛ ድረስ የሆነው እንዲያ ነው፡፡ በእኔ የካሴት፣ በእነርሱ የቴፕ መዋጮ ፍላጎታችን ይሰምራል፡፡ ሳንነጋገር፣ ሳንወያይ የምንተዳደርበት ማህበራዊ ውል ሳይሆን ይቀራል? እናማ ኮሜዲያን ተስፋዬ ካሳን…
በርእዮት ኪን ተስፋዬ ካሳን እንተዝታለን፡፡
ተስፋዬካሳ ኮሜዲያንተስፋዬካሳ #TESFAYEKASA #Ethiopiancomedy

Комментарии

Информация по комментариям в разработке