Logic Freshman Chapter 2 Types of Argument በ አማርኛ ተብራርቶ የቀረበ

Описание к видео Logic Freshman Chapter 2 Types of Argument በ አማርኛ ተብራርቶ የቀረበ

📗 Chapter Two

📕 Basic Concepts of Logic

🎈 Types of Argument

✏️There are two types of Argument:

Deductive_Argument
Inductive_Argument


እሺ ለማንኛውም ዛሬ የምንማረው ስለ Inductive argument ነው።
📍Inductive argument - is an argument in which the conclusion is claimed to follow only probably from the premises.

📍Inductive argument - is an argument that involves probabilistic reasoning.

😊 እሺ አሁን ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት እንሞክር።

Inductive argument የ argument አይነት ነው። argument ማለት ደግሞ ማስረጃዎችን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት ነው። ታዲያ🤔

🤗ማስረጃዎቹ( #premises ድምዳሜውን(conclusion) በአብዛሀኛው(80% ወይም 90% ምናምን) ዋስትና የሚሆኑት ከሆነ Inductive argument ይባላል። 🤔ይህ ማለት ደግሞ

Inductive argument ላይ ያሉት premises(የቀረቡት ማስረጃዎች) እውነት ናቸው ብለን በአምሮኣችን assume እናደርጋለን። ታዲያ እውነት ናቸው ብለን assume ያደርግናቸው premises(ማስረጃዎች) ለ ድምዳሜው(conclusion) 80 ምናምን ፐርሰንት ወይ ደግሞ 90 ምናምን ፐርሰንት ዋስትና ስለሚሆኑት ፡ ድምዳሜው ውሸት የመሆን ዕድል አይኖረውም ወይም ውሸት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ነው(improbable)::
ተመልከቱ👇

🔶 Deductive argument ላይ ማስረጃዎቹ(premises) ለ ድምዳሜው(conclusion) ሙለ በሙሉ(100%) ዋስትና ናቸው።

🤗 ስለዚህ ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ከሆኑ ድምዳሜውም(conclusion) እውነት ነው(100%) ወይም ውሸት መሆን አይችልም(impossible)::

👆 ማስረጃዎቹ ደግሞ በ ነባራዊው አለም እውነት ቢሆኑም ውሸት ቢሆኑም እኛ በ አምሮኣችን እውነት ናቸው ብለን ነው assume የምናደርገው።

🔶 Inductive argument ላይ ደግሞ ማስረጃዎቹ(premises) ለድምዳሜው(conclusion) 80% ወይ ደግሞ 90% ምናምን ነው ዋስትና የሚሆኑት።

🤗 ስለዚህ ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ከሆኑ ድምዳሜው(conclusion) እውነት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው(80% or 90% ምናምን)። በሌላ አባባል ውሸት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ነው(improbable)::

👆ታዲያ ማስረጃዎቹ(Premises) በ ነባራዊው አለም እውነትም ይሁኑ ውሸትም ይሁኑ እኛ በአምሮኣችን እውነት ናቸው ብለን assume እናደርጋለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ናቸው፡ ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው ድምዳሜው(conclusion) ውሸት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ከሆነ(improbable) ፡ በሌላ አባባል እውነት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ከሆነ ፡ Inductive argument ይባላል።

🙌 ተወዳጆች ሆይ እስቲ ምሳሌዎችን እንመልከት😘።

🌀Example 1

Argument I👇
All women are beautiful.
Hana is a woman.
Thus, Hana is beautiful.

Argument II
Most women are beautiful.
Hana is a woman.
Thus, Hana is beautiful.

👆 አያችሁ አይደል ሁለቱን argument 🥺::

😤የትኛው ነው Deductive argument? የትኛው ነው Inductive argument?

🙋‍♂🙋‍♀ እስቲ ማነው የሚመልስ? ጫላ እጁን አውጥቷል። ጫላ እስቲ ና ውጣ ና አስረዳን። ቾክ እዛጋ አለልህ ማርከር እንካ🖍።
😡ሽሽሽ አትረብሹ። ምንድን ነው የሚያስቃችሁ አያስቅም😂። አቦ ሳቁልኝ። እሺ ጫላ ቀጥል ፡ አስተምር። "እድሉ ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ" ብሎ ጫላ ማስረዳቱን ቀጠለ።

አንድ argument Deductive ወይም Inductive መሆኑን ለማወቅ መጀመሪያ የምናደርገው ነገር

🌷Step 1
ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ናቸው ብለን በአምሮኣችን assume እናደርጋለን። በ ትክክለኛው አለም እውነትም ውሸትም ሊሆኑ ይችላሉ። እኛ አያገባንም ዝም ብለን እውነት ነው ብለን assume እናደርጋለን።

🌷step 2k
ስለዚህ ማስረጃዎቹ(premise) እውነት ናቸው። ታዲያ ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው ድምዳሜውም(conclusion) እውነት ከሆነ ወይም ውሸት መሆን የማይችል ከሆነ argument ቱ Deductive argument ይባላል። በአንፃሩ ደግሞ

ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው ድምዳሜው(conclusion) እውነት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ከሆነ ወይም ውሸት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ከሆነ argument ቱ Inductive argument ይባላል። ስለዚህ ምሳሌውን እስቲ እናብራራው :

Argument I (የመጀመሪያው argument)👇

All women are beautiful.Hana is a woman.Thus, Hana is beautiful.

All women are beautiful የሚለው እና Hana is a woman የሚለው ማስረጃዎች(premises) ናቸው። ስለዚህ እውነት ናቸው ብለን በአምሮአችን assume እናደርጋለን። ከዛ

"ሁሉም ሴቶች ቆንጆ ከሆኑ ፡ ሀና ሴት ከሆነች ስለዚህ ሀና ቆንጆ ናት።" ስለዚህ

"ሀና ቅንጆ ናት" የሚለው ድምዳሜ(conclusion) እውነት ነው ምክንያቱም ማስረጃዎቹ ለድምዳሜው ሙሉ ዋስትና ስለሚሆኑት። ስለዚህ Deductive argument ነው።

🌷Argument I- Deductive
🌷Argument II- Inductive

😊ልዩነቱ በደምብ እንዲገባችሁ ብዬ ነው ነው እንጂ Deductive argument ን ባለፈው ተምረናል። ዛሬ የምንማረው Inductive argument ን ነው።

argument Inductive argument መሆኑን ለማወቅ የሚረዱን መለያ ዘዴዎችን ነው። ሶስት መለያ ዘዴዎች አሉ።

1) The actual strength of the inferential claim between the premises and the conclusion.

2) Indicator words.

3) character or form of argument.

ሶስቱንም ዘዴዎች በደምብ እንመልከታቸው😊።

1) The actual strength of the inferential claim between the premises and the conclusion.

ይህ ዘዴ ቅድም የነገርኳችሁ ነው። ማለትም ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው ብለን በአምሮኣችን assume እናደርጋለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው። ታዲያ ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው ፡ ድምዳሜው ውሸት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ከሆነ(improbable) ወይም ዕውነት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ከሆነ Inductive argument ይባላል።

2) 🌹Indicator words

አንድ argument Inductive መሆኑን ለማወቅ ከምንጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ indicator words ን መጠቀም ነው።

🎈Inductive argument ማለት ማስረጃዎቹ ለ ድምዳሜው በአብዛሀኛው(80% 90%) ዋስትና የሚሆኑበት ሒደት ነው። ታዲያ ማስረጃዎቹ ለድምዳሜው በአብዛሀኛው ዋስትና መሆናቸውን ለማመልከት ጠቋሚ ቃላትን እንጠቀማለን። እነዚህ ጠቋሚ ቃላት Inductive indicator words ይባላሉ። ታዲያ እነዚህ ጠቋሚ ቃላት ምን ምን ናቸው🤔?

🔥Inductive indicator words👇

📍Probably(probable)
📍Improbably(improbable)
📍Plausibly(plausible)
📍Implausibly(implausible
📍Likely
📍Unlikely
📍Reasonable to conclude

ስለዚህ እነዚህን👆ጠቋሚ ቃላት ድምዳሜው(conclusion) ላይ የሚጠቀም argument Inductive argument ይባላል።

3) 🌹Character or form of argument.

አንድ argument Inductive መሆኑን ከምናውቅባቸው ዘዴዎች አንዱ form of argument ነው። form of argument ማለት ደግሞ argument ቱ የሚመሰረትበት ወይም የሚቀርብበት መንገድ ነው።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት Form of argument በሙሉ Inductive argument ናቸው ናቸው።👇

🎈 A) Prediction.

🎈 B) Inductive Generalization.

🎈 C) Casual inference.

🎈 D) Argument based on sign.

🎈 E) Argument from authority.

🎈 F) Argument from Analogy.

Комментарии

Информация по комментариям в разработке