ልንበርከክ ሁሉን ልንገረው Linberkek Hulun Lingerew ንግስት ተ ማሪያም እና ቄስ ብርሃኑ ባልቻ

Описание к видео ልንበርከክ ሁሉን ልንገረው Linberkek Hulun Lingerew ንግስት ተ ማሪያም እና ቄስ ብርሃኑ ባልቻ

Gospel song by singers Nigist T/Mariam and Rev Birhanu Balcha.

ልቤ ተሰብሮብኝ ሳቃስት
መንፈሴ ሲሞላ በጭንቀት
መፍትሔ ከሰው አልሻ
ጌታዬ እያለ ወገሻ
ከእግሩ ስር ወድቄ አነባለሁ
ኋላ በፈውስ እመለሳለሁ /2

ልንበርከክ ሁሉን ልንገረው
ልገስግስ ውስጤን ላሳየው
መሰውያዬ ስር ነውና
ነገሬ ሁሉ የሚያልቀው /2

የተቀጠቀጠን ሸንበቆ
ሳይሰብር የሚጠግን አለኮ
ማንም የማይዘጋው በር አለኝ
ላራግፍ ገብቼ ሸክሜን
ስለእኔ የሚሰማው ኢየሱስ ነው
በጸሎት ነገሬን ላጫውተው /2

ልንበርከክ ……

ለኑሮዬ ትርጉም ሲጠፋ
ሲጨላልምብኝም ተስፋ
በመጠበቂያዬ ላይ ሆኜ
መጠበቅ አውቃለሁ ታምኜ
ሁሉንም ያደርጋል ለበጎ
ብዙ አሳልፎኛልኮ /2

ልንበርከክ ….

የነፍሴ የስጋዬንም ቀንበር
ሰብሮ ይጥለዋል እግዚአብሔር
ቃሉ አይሻርም እውነት ነው
ትላንትና ዛሬም ሕያው ነው
ጌታ ከችግሬ በላይ ነው /2

ልንበርከክ …

“ልንበርከክ ሁሉን ልንገረው”
በዘማሪያን ንግስት ተ/ማሪያም እና ቄስ ብርሃኑ ባልቻ

እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ
ወ/ም ሶካ
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

Комментарии

Информация по комментариям в разработке