//ሙዓዝ ሀቢብ//ያ-ነቢና አዲስ ነሺዳ ||MUAZ HABIB ||NEW NESHIDA Ya nebina ﷺ القمر اهشيم

Описание к видео //ሙዓዝ ሀቢብ//ያ-ነቢና አዲስ ነሺዳ ||MUAZ HABIB ||NEW NESHIDA Ya nebina ﷺ القمر اهشيم

ይህ ነሺዳ ወይም መድሀነቢ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ ከሆኑት ከሱዳን ማዲሆች ፊርቀሰህዋ ወይም ቀመር አል ሀሺሚይ ፍቃድ ተጠይቆ የተሰራ ሲሆን ቆየት ካሉ መድሆች ውስጥ አንዱ ነው ተጋበዙልኝ አመሰግናለሁ
ሙዓዝ ሀቢብ ነኝ ለአሏህ ስል እወዳችኋለሁ ❤

//ሙዓዝ ሀቢብ//ያ-ነቢና አዲስ ነሺዳ ||MUAZ HABIB ||NEW NESHIDA Ya nebina ﷺ القمر ا...
   • //ሙዓዝ ሀቢብ//ያ-ነቢና  አዲስ ነሺዳ ||MUAZ HABI...  


ግጥም ዑስታዝ ሰዒድ

ውሎ አድሮ ሚብሰው፣ ናፍቆቱ እንደገና
ሳትጠግበው አለፈች፣ እናቱ እንኳ አሚና
  
እንዴት ልቋቋመው፣ ታዲያ ምስኪኑ እኔ
ብትናፍቁኝ ነው፣ መንሰፍሰፍ መብከኔ
  መች እሽን ያውቅና፣ ልረፍ ስለው ጎኔ
አቁም ብል ላያቆም፣ ግንፍል ይላል አይኔ


ብትርቡኝ ነው አንቱ፣ ብትናፍቁኝ ነቢና
በልቼ እዬጠጣሁ፣ የማልሆነው ደህና
  ኑሮም ኑሮ አልሆነኝ፣ ካልገባሁ መዲና      
   ።።።

ጥፋቴ ቢበዛም፣ ባጎድልም አማና  
በዝነት አይንሁ እዩኝ፣ ነገ እንዳልቀር መና
   ካንቱ በቀር አዛኝ፣ ሰው የለኝምና
።።።።።።

መች መላ አለው ለኔ፣ ዱንያ ሃብት ዝና
ሙሐመድ ሲባል ነው፣ የማገኘው ጤና
  ያያችሁኝ ለታ፣ ስደፋ ስቃና
ጥሩልኝ የሱን ስም፣ አፊያ እንድሆን ደህና
።።።
ባይችልም መናገር፣  አፍን አላውሶ
ተንሰቅስቋል ግንዱ፣ ሊሰነጠቅ ደርሶ
      ያለ ተቀናቃኝ፣ ልባችን ላይ ነግሶ
    ሲወደድ የሚኖር፣ ማን አለና እንደርሶ
።።

ቢነሳ ሂጃቡ ፣እግር ከጅ ያሰረኝ
መዲና እንዳልመጣ፣ ያሰነካከረኝ
ሃርፍ እየተጥፋፋ፣ ቃልም እያጠረኝ
ላንቱ የማዋዬው፣ ስንት ጉድ ነበረኝ
።።።

መፍሰዴ እስከ መች ነው፣ ርቆ መብከንከኔ
የወንጀል ትብትቢያው፣ ይልቀቅ እንጂ ከኔ
ይብቃው ይባልና፣ ይቅረብ አንቱን ጎኔ
  በዞርኩበት ግድም፣ እንዳያጣሁ አይኔ
።።።

ካቅሟ በላይ ወዳ፣ ናፍቆት ተሸክማ  
   እንዳትጠፋ ነፍሴ ደክማ ተስለምለልማ
     መቼም አዛኝ ኖት፣ አውቃለሁ ነብዬ
    ባልጣራ አትቀሩም እንኳን ኑልኝ ብዬ
።።።።

አብሰልስሎኝ ፍቅርሁ በናፍቆት መንምኜ
  ጤና ነኝ ስል ህመም፣ ታመምኩ ስል ድኜ
ባይተዋር አድርጌ ከሌላው መንኜ
እኔ እዎዶታለሁ ሀበሻ ላይ ሆኜ
።።።።።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке